በካራማራው የኢትዮጵያና ሶማሊያ ጦርነት ጀብዱ የፈጸሙ ኢትዮጵያውያን ጀግኖች ታሪክን የካራማራ ግራሮች በሚል ርዕስ የጻፈችው መቅደስ ዓቢይ፣ ሻለቃ ባሻ ዓሊ በርኬን የገለጸችበት ዓረፍተ ነገር፡፡ ዜና ዕረፍታቸው ግንቦት 29 ቀን 2015 ዓ.ም. የተሰማው ሻለቃ ባሻ ዓሊ፣ ከ45 ዓመት በፊት የወራሪውን የሶማሊያ ሠራዊት ታንኮች በማቃጠላቸው ከኢትዮጵያ መንግሥት የጦር ሜዳ ጀብዱ ኒሻን ተሸላሚ ሆነዋል፡፡