Tuesday, October 3, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊኢሰመኮ በዩኒቨርሲቲዎች የአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ጉዳይ የሚመራበት የጽሑፍ ፖሊሲ አለመኖሩን አስታወቀ

ኢሰመኮ በዩኒቨርሲቲዎች የአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ጉዳይ የሚመራበት የጽሑፍ ፖሊሲ አለመኖሩን አስታወቀ

ቀን:

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች በአምስቱ ላይ ባደረገው ክትትል፣ ሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች የአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ጉዳይ የሚመራበት የጽሑፍ ፖሊሲ እንደሌላቸው ማረጋገጡን አስታወቀ፡፡

ኮሚሽኑ በነሐሴ 2014 ዓ.ም. አጋማሽና መባቻ  በጎንደር፣ ሐረማያ፣ ሐዋሳ፣ጂማና በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲዎች የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት፣ ለአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ያላቸውን የተደራሽነትና አካታችነት ሁኔታ በተመለከተ ያከናወነውን የሰብዓዊ መብቶች ክትትል ሪፖርት ይፋ አድርጓል፡፡

የኢሰመኮ የአካል ጉዳተኞችና የአረጋውያን መብቶች ኮሚሽነር ርግበ ገብረ ሐዋሪያ  ‹‹ክትትሉ በአምስት ዩኒቨርሲቲዎች ላይ የተከናወነ ቢሆንም፣ የግኝቶቹን ምክረ ሐሳቦች፣ አካል ጉዳተኛ ተማሪዎችን የሚያስተናግዱ የትምህርት ተቋማት ሁሉ ሊተገብሯቸውና የአካል ጉዳተኞችን ትምህርት የማግኘት መብት ሊያረጋግጡ ይገባል፤››ብለዋል፡፡

ኢሰማኮ የሰነዶችን ግምገማ ጨምሮ ባደረገው የመስክ ምልከታ፣ የቡድን ውይይትና ልዩ ልዩ ቃለ መጠይቆች ክትትሉን ባደረገባቸው  ዩኒቨርሲቲዎች ተቋማዊ ተደራሽነትን በተመለከተ በሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች የአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ጉዳይ የሚመራበት የጽሑፍ ፖሊሲ አለመኖሩን፣ የአካል ጉዳተኞች ጉዳይ በዋና ዕቅድ ውስጥ ተካቶ አለመሠራቱን፣ እንዲሁም የአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች በተፈጥሮ ሳይንስ ትምህርት ውስጥ ያላቸው ተሳትፎ ዝቅተኛ መሆኑን አስታውቋል። 

በዩኒቨርቲዎቹ ለልዩ ልዩ አገልግሎቶች የሚውሉ  ሕንፃዎችና መዳረሻ መንገዶች  ለአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ምቹና ተደራሽ  አለመሆናቸው፣ አካል ጉዳተኞችን ታሳቢ ያደረጉ በቂ መፀዳጃ ቤቶች አለመኖራቸውን፣ መስማት ለተሳናቸው ተማሪዎች በምልክት ቋንቋ አስተርጓሚ እጥረት ምክንያት በቋንቋው የሚሰጥ የትምህርት አቅርቦት ውስን መሆኑን፣ እንዲሁም ለሴት አካል ጉዳተኛ ተማሪዎች የሚደረገው ምክንያታዊ ማመቻቸት (Reasonable Accommodation) ዝቅተኛ መሆኑን በክትትል ግኝቱ ሪፖርት ቀርቧል፡፡

በሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች የተለያየ አገልግሎት የሚሰጡ ቢሮዎች ደረጃውን የጠበቀ የተሽከርካሪ ወንበር መወጣጫና አሳንሰር በሌለበት ሁኔታ ፎቅ ቤቶች ላይ መሆናቸውን፣ ተደራሽ የሆኑ በቂ መፀዳጃና መታጠቢያ ቤቶች አለመኖራቸውን፣ የሕክምና መስጫ ክሊኒኮች ተደራሽ መንገድ የሌላቸው መሆኑንና በሕንፃዎች ውስጥና ውጭ ግልጽ አቅጣጫ ጠቋሚ ምልክቶች አለመኖራቸውን በክትትሉ ታይቷል ተብሏል፡፡

ዩኒቨርስቲዎች አካታች የሴኔት ደንብ፣ ሕግና ሥርዓተ-ትምህርት መንደፍ እንዲሁም በረቂቅ ደረጃ የሚገኙትን አካታች ፖሊሲዎችን አጠናቅቀው ማፅደቅና ተግባራዊ ማድረግ እንዳለባቸው የተገለጸ ሲሆን፣ ለአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ተደራሽ የሆኑ በቂ የመፀዳጃና የመታጠቢያ ክፍሎች፣ አሳንሰርና የተሽከርካሪ ወንበር መወጣጫ ያላቸው የመማሪያ ክፍሎች፣ ቢሮዎች፣ ቤተ-መጻሕፍት፣ ካፍቴሪያዎችና የመዝናኛ ቦታዎች እንዲያዘጋጁ ምክረ ሐሳብ አቅርቧል፡፡

ኢሰመኮ አክሎም  አካል ጉዳተኛ ተማሪዎችን የሚያስተናግዱ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት  ከባቢያዊ፣ ተቋማዊ፣ የመረጃና ተግባቦት እንዲሁም ከአመለካከት ጋር ከተያያዙ ተግዳሮቶች ነፃ መሆን እንዳለባቸው አስታውቋል፡፡ 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ተመድንና ዓለም አቀፋዊ ሕግን ከእነ አሜሪካ አድራጊ ፈጣሪነት እናድን!

በገነት ዓለሙ በእኔ የተማሪነት፣ የመጀመርያ ደረጃ ተማሪነት ጊዜ፣ የመዝሙር ትምህርት...

የሰላም ዕጦትና የኢኮኖሚው መንገራገጭ አንድምታ

በንጉሥ ወዳጅነው ፍራንክ ቲስትልዌይት የተባሉ አሜሪካዊ ጸሐፊ ‹‹The Great Experiment...

ድህነት የሀብት ዕጦት ሳይሆን ያለውን በአግባቡ ለመጠቀም አለመቻል ነው

በአንድነት ኃይሉ ድህነት ላይ አልተግባባንም፡፡ ብንግባባ ኖሮ ትናንትም ምክንያት ዛሬም...