ከሰማንያ ሰባት ዓመት በፊት፣ ከፋሺስት ጣሊያን ሠራዊት ጋር እየተካሄደ የነበረው ጦርነት በሚያዝያ መገባደጃ አዲስ አበባ ከተማ ይደርሳል። አስቀድሞ ግን የኢትዮጵያ መንግሥት ጀርመናዊውን ፓይለት ሉድቪግ ዌበርን ‹‹ደሴ›› የተባለችውን ‘ጀንከርስ ደብሊው 33ሲ’ ትንሽ አውሮፕላንን (ጢያራ) ይዞ ወደ ሱዳን እንዲበር ያዘዋል። አብራሪው ሚያዝያ 25 ቀን 1928 ዓ.ም. ደኅንነቱ የተጠበቀ ነው ወደ ተባለው የብሉ ናይል ግዛት ያየር ማረፊያ፣ ኤር ሮዝሬስ ቢቃረብም በሰላም ለማረፍ አልታደለም። ነዳጅ በማለቁና ሞተሩ በመጥፋቱ አብራሪው ድንገተኛ ለማረፍ ቢሞክርም ከኤር ሮዝሬስ በስተደቡብ በሚገኝ በረሃ አካባቢ
ከመከስከስ ግን አልተረፈም። አብራሪው ምንም ጉዳት ባይደርስበትም አውሮፕላኗ ግን ከጥቅም ውጭ በመሆኗ የሮያል አየር ኃይል በአካባቢው ለሚገኝ ቆራሌው ሽጧታል።
– ምንጭ፣ ቢሮ ኦቭ ኤርክራፍት አክሲደንትስ አርካይቭስ