Tuesday, October 3, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትየ10 ሺሕ ሜትር የመለያ ውድድር በስፔን እንደሚከናወን ታወቀ

የ10 ሺሕ ሜትር የመለያ ውድድር በስፔን እንደሚከናወን ታወቀ

ቀን:

በዘንድሮ የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያን በ10 ሺሕ ሜትር የሚወክሉ አትሌቶችን ለመለየት ውድድሩን ስፔን ለማድረግ መወሰኑ ታወቀ፡፡

የመለያ ውድድሩን በኔዘርላንድ ሄንግሎ ሲያደርግ የነበረው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን፣ ውድድሩን በስፔን ኔርጃ ከተማ ሰኔ 16 ቀን 2015 ዓ.ም. ለማድረግ መወሰኑ ተገልጿል፡፡

የማሟያ ውድድሩን በሐዋሳ ሊያደርግ እንደነበር ሲነገር ቢቆይም፣ ፌዴሬሽኑ በጉዳዩ ዙሪያ ከአሠልጣኞችና ከሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው ጋር ከመከረ በኋላ ሐሳቡን መቀልበሱ ተጠቁሟል፡፡

ከዚህ ቀደም በማናጀር ሄርመንስ አማካይነት በሄንግሎ ሲደረግ የነበረው የማሟያ ውድድሩ፣ ዘንድሮ በተመሳሳይ የማጣሪያ ውድድር ማድረግ ባለመቻሉና በስፔን የሚገኙ ማናጀሮች ጥያቄ ማቅረባቸውን ተከትሎ ውሳኔ መወሰኑ ተጠቅሷል፡፡

በዚህም መሠረት ከስፔን የመጣው ጥያቄ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው ውይይት ካደረገበት በኋላ ከውሳኔ መድረሱ ታውቋል፡፡

በቡዳፔስት የሚስተናገደው የዘንድሮ የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና አትሌቶች በ10 ሺሕ ሜትር ርቀት ለመካፈል ሴቶች 30፡40፡00 ማምጣት የሚገባቸው ሲሆን፣ ወንዶች 27፡10፡00 መግባት ይጠበቅባቸዋል፡፡

ሰዓቱ ያላቸው አትሌቶች ቢኖሩም ወቅታዊ አቋም ለቅድመ ዝግጅቱ ስለሚያስፈልግ የመለያ ውድድሩን ማድረግ ግዴታ ነው፡፡ በመለያ ውድድሩ የዓለም ሻምፒዮናዋ ለተሰንበት ግደይ፣ የኦሊምፒክ ሻምፒዮናው ሰለሞን ባረጋና በሪሁ አረጋዊ ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ተመድንና ዓለም አቀፋዊ ሕግን ከእነ አሜሪካ አድራጊ ፈጣሪነት እናድን!

በገነት ዓለሙ በእኔ የተማሪነት፣ የመጀመርያ ደረጃ ተማሪነት ጊዜ፣ የመዝሙር ትምህርት...

የሰላም ዕጦትና የኢኮኖሚው መንገራገጭ አንድምታ

በንጉሥ ወዳጅነው ፍራንክ ቲስትልዌይት የተባሉ አሜሪካዊ ጸሐፊ ‹‹The Great Experiment...

ድህነት የሀብት ዕጦት ሳይሆን ያለውን በአግባቡ ለመጠቀም አለመቻል ነው

በአንድነት ኃይሉ ድህነት ላይ አልተግባባንም፡፡ ብንግባባ ኖሮ ትናንትም ምክንያት ዛሬም...