Tuesday, October 3, 2023
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

የሲቪል ማሕበረሰብ ድርጅቶች ድጋፍ ፕሮግራም የ15 ሚሊዮን ፓውንድ ድጋፍ ማድረጉን አስታወቀ

ተዛማጅ ፅሁፎች

በብሪቲሽ ካውንስል በሚመራ የለጋሾች ጥምረት አማካይነት ተግባራዊ እየተደረገ ያለው ሁለተኛው የሲቪል ማኅበራት ድጋፍ ፕሮግራም፣ ባለፉት አምስት ዓመታት የ15 ሚሊዮን ፓውንድ ድጋፍ ኮንትራቶችን እንደፈረመ አስታወቀ፡፡

የተለያዩ የቴክኒካል፣ የተቋም ግንባታና የፋይናንስ ድጋፎችን 173 ለሚሆኑ በኢትዮጵያ የሚሠሩ የሲቪል ማኅበራት የተሰጡ ሲሆን፣ ይህንን ድጋፍ ያገኙ ድርጅቶችም የአቅም ማጎልበቻ ድጋፍ 4,734 የሚሆኑ ሌሎች የሲቪል ሰርቪስ ማኅበራትን ማሳደግ ችለዋል፡፡

ባለፈው ግንቦት 22 እና 23 ቀን 2015 ዓ.ም. ‹‹ወደ ተሻለ የሲቪክ ምኅዳር ዕድሎችና ተግዳሮቶች›› በሚል መሪ ቃል፣ በኃይሌ ግራንድ ሆቴል ፕሮግራሙን በሚመለከት ኮንፈረንስ የተካሄደ ሲሆን፣ የመንግሥት ባለድርሻ አካላት፣ የአካባቢው ሲቪል ማኅበራትና ቡድኖች በተገኙበት ነው የተካሄደው፡፡

ከሁለተኛው የሲቪል ማኅበራት ድጋፍ ጋር አብረው የሠሩ የሲቪክ ማኅበራት፣ በኮንፈረንሱ ላይ በተለያየ መርሐ ግብር ተገኝተው የነበረ ሲሆን፣ የገበያ ቦታ ላይም ለኅብረተሰቡ ያበረከቱትን አስተዋጽኦ ለማሳየት ችለዋል፡፡

የሲቪክ ማኅበራት ድርጅቶች ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ጂማ ዲልቦ፣ በተጨማሪም የባለሥልጣኑ የቦርድ ሰብሳቢና የፕላንና ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ነመራ ማሞ (ዶ/ር)ን ጨምሮ የተለያዩ የመንግሥትና የሲቪክ ማኅበራት ድርጅት ኃላፊዎች በኮንፈረንሱ ተገኝተዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች