Tuesday, September 26, 2023
Homeስፖንሰር የተደረጉየአዛርባጃንን ብሄራዊ ቀን በአዲስ አበባ በድምቀት ተከበረ

የአዛርባጃንን ብሄራዊ ቀን በአዲስ አበባ በድምቀት ተከበረ

Published on

- Advertisment -

የአዛርባጃን ኤምባሲ  የአዛርባጃንን ብሄራዊ ቀን በትላንትናው ዕለት አከበረ። ሰኞ ግንቦት 21 ቀን 2015 ዓም በስካይ ላይት ሆቴል በተከበረው በዚሁ በዓል ላይ በርካታ አምባሳደሮችና ሌሎች ዲፕሎማቶች እንዲሁም ታዋቂ ሰዎችና የሚዲያ ባለሞያዎች ተገኝተዋል።

የአዛርባጃንን ብሄራዊ ቀን በአዲስ አበባ በድምቀት ተከበረ | Ethiopian Reporter | ሪፖርተር

የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአዛርባጃን የኤምባሲ ጉዳዮች ኃላፊ የሆኑት ሚ/ር ሩስላን ናሲቦቭ ሃገራቸው ከሶቪዬት አገዛዝ ነጻ የወጣችበትን ወቅት ርስበርስ የምትታመስ፣ የኢኮኖሚ ጫና የበዛባት፣ አንዳንድ የውስጥ ኃይሎች ለጠላት ሃገሮች ፍላጎት ሲሉ ሃገራቸውን የሚወጉበት፣ እንዲሁም ከ1/3ኛ በላይ የሆነው ግዛቷ የተወረረባት በአጠቃላይ ለመክሰም የተቃረበች የነበረች መሆኗን አውስተው ፣ የአዛርባጃን የቁርጥ ቀን ልጅና ብሄራዊ ጀግና የሆኑት ፕረዝዳንት ሃይደር አሊየቭ በህዝብ ጥያቄ ወደስልጣን ከመጡ በኋላ ግን ነገሮች ሁሉ መልክ መልክ በመያዝ ሃገሪቱ የነበረችበት ሁኔታ በፍጥነት መቀየሩን አስታውሰዋል።

ህዝቧ በድህነት ሲማቅቅባት የነበረችው ሃገር ብሄራዊ ጀግናዋ ድንቅ የውጭ ፖሊሲውን በመቀመርና የክፍለ ዘመኑ ምርጥ ውል እየተባለ የሚገለጸውን ስምምነት ከተለያዩ  ዓለም አቀፍ አጋሮች ጋር በመፈራረም የአዛርባጃንን መመንደግ ያስጀመሩ ሲሆን ይህው የእድገት ጎዳና ቀጥሎ ሃገሪቱ በአጁኑ ሠዓት ከዓለም አቀፍ ተራድኦ አቅራቢ ሃገራት ተርታ እንድትሰለፍ አስችሏል።

እንደ ሚ/ር ሩስላን ገለጻ  በአሁኑ ሰዓት በአዛርባጃን የድህነት መጠን ከ5 ፐርሰንት በታች ነው። አስር ሚሊዮን ህዝባ  ያላት ሃገር ወደ ኢኮኖሚው ኢንቨስት የተደረገባት ገንዘብ 300 ቢሊዮን ዶላር በላይ ነው። ካዝናዋ ውስጥ ያለው የውጭ ምንዛሬ ከ65 ቢሊዮን ዶላር ይበልጣል። ይህ ደግሞ ካለባት የውጭ  እዳ 10 እጥፍ ነው። ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት የተገነቡ በርካታ መሠረተ ልማቶች የምዕራቡን ከምስራቁን ፣ የሰሜኑን ከደቡቡ ዓለም የሚያገናኙ ድልድዮች በመሆን እያገለገሉ ነው። ሃገሪቱ በ30 ዓመታት ብቻ ከእርጥባን ፈላጊነት ወደ ርዳታ ሰጭነት ተቀይራለች።

የአዛርባጃንን ብሄራዊ ቀን በአዲስ አበባ በድምቀት ተከበረ | Ethiopian Reporter | ሪፖርተር

ሚ/ር ሩስላን አዛርባጃን ከኢትዮጵያ ጋር ያላት የዲፕሎማሲግንኙነት ከ30 ዓመት በላይ እንደሆነው እና ግንኙነቱም ደረጃ በደረጃ እያደገ እየመጣ እንደሆነ፣ ሃገራቸው በኢትዮጵያ ኤምባሲዋን የከፈተችው እኤአ በ2014  ዓም እንደነበረ እና  ከ2000 በላይ ለአፍሪካውያን ተማሪዎች ከተሰጠ የትምህር ዕድል አብዛኛው ለኢትዮጵያውያን የተሰጠ እንደነበረ  ለታዳሚዎች ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ፌዲራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የሆኑት አቶ ደመቀ መኮንን በቅርቡ አዛርባጃንን መጎብኘታቸውን እና በባኩ ከተማ በተደካሄደውና በርካታ የሁለትዮሽ ውይይቶች በተደረጉበት የድህረ-ኮቪድ 19 ማገገሚያ ጉባኤ ላይ መሳተፋቸውንም አስታውሰዋል።

የቅርብ ጊዜ መጣጥፎች

በቀይ ባህር ፖለቲካ ላይ በመከረው የመጀመሪያ ጉባዔ ለዲፕሎማቲክና ለትብብር አማራጮች ትኩረት እንዲሰጥ ጥሪ ቀረበ

ሰሞኑን በአዲስ አበባ ለመጀመርያ ጊዜ በቀይ ባህር ቀጣና የፀጥታ እንቅስቃሴ ላይ በመከረው ጉባዔ፣ ኢትዮጵያ...

የቤት ባለንብረቶች የሚከፍሉትን ዓመታዊ የንብረት ታክስ የሚተምን ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጀ

በአዋጁ መሥፈርት መሠረት የክልልና የከተማ አስተዳደሮች የንብረት ታክስ መጠን ይወስናሉ በ1968 ዓ.ም. የወጣውን የቦታ ኪራይና...

እንደ ንብረት ታክስ ያሉ ወጪን የሚያስከትሉ አዋጆች ከማኅበረሰብ ጋር ምክክርን ይሻሉ!

የመንግሥትን ገቢ በማሳደግ ረገድ አስተዋጽኦ እንዳላቸው የሚታመኑት የተጨማሪ እሴት ታክስ መሻሻያ አዋጅና የንብረት አዋጅ...

ለዓለምም ለኢትዮጵያም ሰላም እንታገል

በበቀለ ሹሜ ያለፉት ሁለት የዓለም ጦርነቶች በአያሌው የኃያል ነን ባይ አገሮች ጎራዊ ግጥሚያዎች ነበሩ፡፡ በእነዚህ...

ተመሳሳይ

በአፍሪካ የገንዲ በሽታ ስርጭትን ለመግታት የሚያስችሉ መፍትሄዎች ላይ በጋራ ለመስራት ስምምነት ላይ ተደረሰ

የአፍሪካ እንስሳት ትራይፓኖሶሚያሲስ (AAT) በመባል የሚታወቀው የገንዲ በሽታ ከሰሃራ በታች ባሉ አፍሪካውያን የእንስሳ እርባታ...

ታምሪን ሞተርስ አዲስ ያስመጣዉን ሱዙኪ ኢኮ ቫን ሞዴል በደማቅ ሁኔታ አስመረቀ

ለአካባቢ ሥነ ምህዳር ምቹ የሆኑ ተሽከርካሪዎችን ከሚያመርተው እና በዓለም ታዋቂ ከሆነው የሱዙኪ ኩባንያ ጋር...

የላይፍላይን አዲስ የቤት ለቤት ጤና እንክብካቤ አገልግሎት ድርግጅት በጤናው ዘርፍ የቁርጥ ሥራ (ጊግ) ኢኮኖሚን የመገንባት ጉዞ

ዶ/ር ሰለሞን ደሳለኝ  ከቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ በሕክምና የተመረቀው በ2009 ዓ.ም. ማብቂያ...