Thursday, September 28, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናየአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ በሽግግር ፍትሕና ተጠያቂነት ላይ ለመነጋገር ኢትዮጵያ ሊመጡ ነው

የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ በሽግግር ፍትሕና ተጠያቂነት ላይ ለመነጋገር ኢትዮጵያ ሊመጡ ነው

ቀን:

የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ማይክ ሐመር (አምባሳደር)፣ የሽግግር ፍትሕና ተጠያቂነትን ለማስፈን የሚደረጉ ጥረቶች የደረሱበትን ደረጃ በሚመለከት ለመነጋገር ኢትዮጵያ ሊመጡ ነው፡፡

ከረቡዕ ከዛሬ ግንቦት 23 ቀን 2015 ዓ.ም. ጀምሮ ለሰባት ቀናት በጂቡቲና በኢትዮጵያ ጉብኝት የሚደርጉት ልዩ መልዕክተኛው ከጂቡቲ በማስቀጠል በኢትዮጵያ ከፌዴራል መንግሥት ኃላፊዎች ጋር በአዲስ አበባ ከተማ፣ እንዲሁም ከትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ጋር ደግሞ በመቀሌ ውይይት እንደሚያደርጉ ነው የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ትናንት ማክሰኞ ባወጣው መግለጫ ያስታወቀው፡፡

ማይክ ሐመር በኢትዮጵያ ቆይታቸው ፌዴራል መንግሥትና ሕወሓት ከስድስት ወራት በፊት በደቡብ አፍሪካ በፕሪቶሪያ ያደረጉትን የግጭት ማቆም ስምምነት አጠቃላይ አፈጻጸም በሚመለከት ውይይት እንደሚያደርጉ፣ በተጨማሪም የስምምነቱን አተገባበርን አስመልክቶ ከአፍሪካ ኅብረት ኃላፊዎች ጋር ተጨማሪ ውይይት እንደሚኖራቸው ተገልጿል፡፡

ልዩ መልዕክተኛው የአሜሪካ ጦር ኃይል የአፍሪካ ዕዝና የአፍሪካ ቀንድ የጋራ ግብረ ኃይል በጂቡቲ በሚያዘጋጁት የምሥራቅ አፍሪካ ሴኩሪቲ ፎረም ላይ ለመሳተፍ ወደ ጂቡቲ እንደሚያቀኑ ነው የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ያስታወቀው፡፡

በጂቡቲ መቀመጫውን ካደረገው የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት ድርጅት (ኢጋድ) ዋና ጸሐፊ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) ጋር የድርጅቱን ሥራዎች የሚመለከቱ ሲሆን፣ ከጂቡቲ መንግሥት ባለሥልጣናት ጋርም በጋራ ትብብርና ቀጣናዊ ጉዳዮች ዙሪያ እንደሚወያዩ ተገልጿል፡፡

የኢጋድ ዋና ጸሐፊ ቃል አቀባይ ኑር መሐመድ ልዩ መልዕክተኛው ከወርቅነህ (ዶ/ር) ጋር ስለሚኖራቸው ውይይት ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ልዩ መልዕክተኛው የኢጋድን በዲፕሎማሲ ላይ ያለውን ዋና ሚና ‹‹ሊያደንቁ እንደሚፈልጉ›› ተናግረዋል፡፡

ኢጋድ በቀጣናው ላይ የሚጫወተውን የሰላምና ደኅንነት፣ እንዲሁም የኢኮኖሚ ትስስር ሚና አሜሪካ ዕውቅና እንደምትሰጥና ከድርጅቱም ጋር በእነዚህ ዙሪያዎች ላይ ትብብር እንደምታደርግ ‹‹ግልጽ እንዳደረገች›› ቃል አቀባዩ ገልጸዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የአማራ ክልል ወቅታዊ ሁኔታ

እሑድ ጠዋት መስከረም 13 ቀን 2016 ዓ.ም. የፋኖ ታጣቂዎች...

ብሔራዊ ባንክ ለተመረጡ አልሚዎች የውጭ አካውንት እንዲከፍቱ ለመጀመሪያ ጊዜ የፈቀደበት መመርያና ዝርዝሮቹ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪ አጠቃቀምንና ተያያዥነት ያላቸው ጉዳዮችን...

እነ ሰበብ ደርዳሪዎች!

ከሜክሲኮ ወደ ዓለም ባንክ ልንጓዝ ነው። ሾፌርና ወያላ ጎማ...