Saturday, April 20, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ኪንና ባህልለኢትዮጵያ ባለውለታ አሜሪካዊ የቆመው መታሰቢያ

ለኢትዮጵያ ባለውለታ አሜሪካዊ የቆመው መታሰቢያ

ቀን:

በፋሺስት ጣሊያን ወረራ ጊዜ፣ ከኢትዮጵያ ጎን ሆነው አየር ኃይሉን ሲመሩ በነበሩት ባለውለታ አሜሪካዊ ጆን ሲ ሮቢንሰን ስም በቅድስት ማርያም ዩኒቨርሲቲ የእንግሊዝኛ ቋንቋን ጨምሮ ትምህርታዊ ድጋፍ የሚሰጥ ጥግ (ኮርነር) ተቋቋመ፡፡ በአዲስ አበባ የአሜሪካ ኤምባሲ ጉዳይ ፈጻሚ አምባሳደር ትሬሲ ጃኮብሰንና የቅድስት ማርያም ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ወንድወሰን ታምራት (ዶ/ር) ተቋሙን ግንቦት 15 ቀን 2015 ዓ.ም. በይፋ ከፍተዋል። በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ በላከው መግለጫ እንደገለጸው፣ ጥጉ የተሰየመላቸው አፍሪካ አሜሪካዊው ኮሎኔል ጆን ሲ ሮቢንሰን፣ በ1928 ዓ.ም. በሁለተኛው የኢትዮጵያና የጣሊያን ጦርነት ወቅት በአብራሪነትና በአሠልጣኝነት አዲሱን አየር ኃይል ይመሩ ነበር፡፡ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ምሥረታ ላበረከቱት አስተዋጽዖ አየር መንገዱ ከቦይንግ ጄቶች አንዱ ለእሳቸው ክብር መሰየሙ ይታወሳል። ከሰባት ዓመት በፊት በብሔራዊ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት ኤጀንሲ በአንደኛው ጥግ፣ በአሜሪካ ኤምባሲ ትብብር በኮሎኔል ጆን ሮቢንሰን ስም ለተማሪዎችና ተመራማሪዎች አገልግሎት የሚሰጥ የቴክኖሎጂ ማዕከል ማዕከል መቋቋሙ ይታወሳል፡፡ ፎቶው የአሜሪካ ኤምባሲ ጉዳይ ፈጻሚና የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ጥጉን በመረቁበት ወቅት የነበረውን ገጽታ ያሳያል፡፡

– ፎቶ የአሜሪካ ኤምባሲ

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ሰላማዊ የፖለቲካ ትግልና ፈተናው

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) የፖለቲካ ኦፊሰር የአቶ በቴ ኡርጌሳን...

አበጀህ ማንዴላ! አበጀሽ ደቡብ አፍሪካ!

በአየለ ት. የፍልስጤም ጉዳይ የዓለም አቀፍ ፖለቲካንም ሆነ የተባበሩት መንግሥታትን...

የውጭ ባለሀብቶች ለኢትዮጵያውያን ብቻ በተፈቀዱ የንግድ ዘርፎች እንዲገቡ የመወሰኑ ፋይዳና ሥጋቶች

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አዓመድ (ዶ/ር) የውጭ ኩባንያዎች በጅምላና ችርቻሮ...