Saturday, April 20, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊአዲስ አበባን ጨምሮ በተደረገ የዳሰሳ ጥናት 43 ቶን የኤሌክትሮኒክስ ቆሻሻዎች ክምችት እንዳለ...

አዲስ አበባን ጨምሮ በተደረገ የዳሰሳ ጥናት 43 ቶን የኤሌክትሮኒክስ ቆሻሻዎች ክምችት እንዳለ ተረጋገጠ

ቀን:

የኢትዮጵያ አካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን፣ አዲስ አበባ፣ ድሬዳዋ፣ ሐዋሳ፣ አዳማና ባህር ዳርን ጨምሮ በሌሎች አካባቢዎች በባለሙያዎች በተደረገ የዳሰሳ ጥናት ከ43 ቶን በላይ የኤሌክትሮኒክና የኤሌክትሪክ ቆሻሻዎች ክምችት መኖሩን አረጋግጫለሁ አለ፡፡

ባለሥልጣኑ የዳሰሳ ጥናት ግኝቱን ያስታወቀው ግንቦት 16 ቀን 2015 ዓ.ም.፣ በኤሌክትሮኒክና ኤሌክትሪክ ቆሻሻዎች አወጋገድ የ2014/15 በጀት ዓመት የክንዋኔ ኦዲት ሪፖርቱ ላይ ለመወያየት በተጠራ ስብሰባ ነው፡፡

በተደረገው የዳሰሳ ጥናት መሠረት አምስት ከተሞችን ጨምሮ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በሚገኙባቸው አካባቢዎች፣ ከፍተኛ የኤሌክትሮኒክና የኤሌክትሪክ ቆሻሻ አመንጪ ተብለው መለየታቸውን፣ የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ጌታሁን ጋረደው (ዶ/ር) አስረድተዋል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

የባለሥልጣኑ ባለሙያዎች ባደረጉት የዳሰሳ ጥናት ከ43 ቶን በላይ የኤሌክትሮኒክና የኤሌክትሪክ ቆሻሻዎች ክምችት መኖሩ መረጋገጡን የገለጹት ደግሞ፣ የባለሥልጣኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ፍሬነሽ መኩሪያ ናቸው፡፡

በተለይ ዳሰሳ በተደረገባቸው ከተሞች የተገኙት ቆሻሻዎች በአብዛኛው የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ውስጥ እንደሚገኙ፣ እነሱን ለማስወገድ ፈታኝ የሆነው ደግሞ እንደ ንብረት መታየታቸው ነው ሲሉ ዋና ዳይሬክተሩ አስረድተዋል፡፡

ጥቅም ላይ የማይውሉ የኤሌክትሮኒክና የኤሌክትሪክ ቆሻሻዎችን ከአገር ለማስወጣት በሚደረገው ሒደት፣ በሁለት ዓመታት ውስጥ 127 ቶን ወደ ውጭ መላክ እንደተቻለ ገልጸዋል፡፡

እንደ ዋና ዳይሬክተሩ ገለጻ፣ ጥቅም ላይ የማይውሉና የተከማቹ የኤሌክትሮኒክስና የኤሌክትሪክ ቆሻሻዎች በማኅበረሰቡ ዘንድ እንደ ንብረት በመታየታቸው፣ ለሽያጭ ሲቀርቡ እንኳን ከ20 እስከ 30 ሺሕ ብር የዋጋ ተመን ይወጣላቸዋል፡፡

በዳሰሳ ጥናቱ ከተረጋገጡት ከአምስቱ ከተሞች ከፍተኛው ክምችት የሚገኘው በአዲስ አበባ ከተማ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ የሚወገዱት የኤሌክትሮኒክስና የኤሌክትሪክ ቆሻሻ ክምችቶች የሚተመንላቸው ዋጋ ከፍተኛ መሆኑን ገልጸው፣ መልሰው ጥቅም ላይ ለሚያውሉ አካላት እንደሚወደድባቸው ተናግረዋል፡፡

ገበያ ውስጥ አንድ ኮምፒዩተር 70 እና 80 ሺሕ ብር እየተሸጠ ስለሆነ በሚል ሰበብ፣ ምንም ዓይነት አገልግሎት የማይሰጥ ኮምፒዩተር 20 እና 30 ሺሕ ብር ያወጣል ስለሚባል በፍጥነት ለማስወገድ አስቸጋሪ ሆኗል ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

ምክትል ዋና ዳይሬክተሯ ደግሞ ከአምስቱ ከተሞች በተጨማሪ ሁለተኛ ደረጃ በሚባሉ ከተሞች ላይ ጥናት ለማድረግ በሒደት ላይ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ በኦዲት ግኝት ከደቡብ ክልል የአካባቢ ደንና የአየር ንብረት ለውጥ ቁጥጥር ባለሥልጣን ዲላ፣ አርባ ምንጭ፣ ሆሳዕናና ወላይታ ሶዶ በተደረገው የዳሰሳ ጥናት በ12 የኤሌክትሮኒክስ ጥገና በሚሰጡ ተቋማት ላይ ችግር መታየቱን አክለዋል፡፡

በእነዚህ የጥገና ተቋማት መርዛማና አደገኛ የሆኑ ቆሻሻዎች መኖራቸውን፣ እንደ ማናቸውም ጥቅም የማይሰጡ ዕቃዎች እየተወገዱ መሆናቸው በኦዲት ግኝት ተረጋግጧል ብለዋል፡፡

የቆሻሻ ክምችቱ በአካባቢና በሰዎች ጤና ላይ ችግር ሊፈጥር ይችላል ያለው ቋሚ ኮሚቴው፣ ባለሥልጣኑ ለዚህ ጉዳይ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ መሥራት እንዳለበት አሳስቧል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ሰላማዊ የፖለቲካ ትግልና ፈተናው

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) የፖለቲካ ኦፊሰር የአቶ በቴ ኡርጌሳን...

አበጀህ ማንዴላ! አበጀሽ ደቡብ አፍሪካ!

በአየለ ት. የፍልስጤም ጉዳይ የዓለም አቀፍ ፖለቲካንም ሆነ የተባበሩት መንግሥታትን...

የውጭ ባለሀብቶች ለኢትዮጵያውያን ብቻ በተፈቀዱ የንግድ ዘርፎች እንዲገቡ የመወሰኑ ፋይዳና ሥጋቶች

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አዓመድ (ዶ/ር) የውጭ ኩባንያዎች በጅምላና ችርቻሮ...