Monday, April 15, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናበጋምቤላ የተከሰተው ግጭት ቢቆምም የነዋሪዎች መፈናቀል እንዳልቆመ ክልሉ አስታወቀ

በጋምቤላ የተከሰተው ግጭት ቢቆምም የነዋሪዎች መፈናቀል እንዳልቆመ ክልሉ አስታወቀ

ቀን:

  • በግጭቱ ዘጠኝ ሰዎች መገደላቸውን አረጋግጧል

በጋምቤላ ክልል በኢታንግ ልዩ ወረዳ በሁለት ቀበሌዎች በከተሰተው ግጭት የተኩስ ልውውጡን ማስቆም ቢቻልም፣ የልዩ ወረዳው ነዋሪዎች ወደ አጎራባች ወረዳዎች ለመፈናቀል መገደዳቸውን የክልሉ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ለሪፖርተር ገለጸ፡፡

ነዋሪዎቹ በልዩ ወረዳው ዙሪያ በሚገኙ አጎራባች ወረዳዎችና ወደ መሀል ከተማም ጭምር ለመፈናቀል እንደተገደዱ፣ የክልሉ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ኦቶው ኦኮት ተናግረዋል፡፡

ምክትል ኃላፊው ይህን ያሉት በክልሉ በተከሰተው ግጭት ምን ያህል ሰዎች እንደተገደሉ፣ በሰዎች ላይ ምን ያህል ከባድና ቀላል ጉዳት እንደደረሰ፣ ፀጥታው በምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ፣ በቤትና በንብረት ላይ ምን ያህል ውድመት እንደደረሰና ተመሳሳይ ችግር እንዳይፈጠር ምን እየተደረገ እንደሆነ ሪፖርተር ማብራሪያ እንዲሰጡት ላቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ ሲሰጡ ነው፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

የደረሰውን የሞት መጠን ሲገልጹም፣ ‹‹በተፈጠረው ግጭት ዘጠኝ ሰዎች ሞተዋል፡፡ ወደ 17 ሰዎች ደግሞ ከባድና ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል፤›› ብለዋል፡፡

የኢታንግ ልዩ ወረዳ ነዋሪዎች እንደተፈናቀሉ ያስረዱት አቶ ኦቶው፣ የክልሉ መንግሥት የፀጥታ ኃይሉን በማቀናጀት፣ ግጭት በነበረባቸው ቦታዎች እንዳሰማራና ከግንቦት 16 ቀን 2015 ዓ.ም. ጀምሮ ተኩስ ማስቆም ስለመቻሉም ተናግረዋል፡፡

ከኢታንግ ልዩ ወረዳ ምን ያህል ሰዎች እንደተፈናቀሉ ዝርዝር ምላሽ እንዲሰጡ ለቀረበላቸው ጥያቄም፣ የክልሉ አደጋ መከላከል ሥራ አመራር ኮሚሽን መረጃውን በማሰባሰብ ላይ በመሆኑ፣ ትክክኛውን የተፈናቃዮች ቁጥር ለመግለጽ እንደማይቻል፣ ኮሚሽኑ መረጃውን አሰባስቦ ሲያጠናቅቅ ብዛታቸውን እንደሚያሳውቁ ገልጸዋል፡፡

በመኖሪያ ቤት፣ በነዋሪዎች ንብረትና በእንስሳት ላይ የደረሰውን ጉዳት ማወቅ የሚቻለውም ኮሚሽኑ በሚያሰባስበው መረጃ ነው ብለዋል፡፡

ከግንቦት 16 ቀን 2015 ዓ.ም. ጀምሮ ግጭቱን ማስቆም በመቻሉ ነዋሪዎችን የማረጋጋት ሥራ እየተሠራ መሆኑን፣ የሰዎች ሰላማዊ እንቅስቃሴ እንደተጀመረ፣ በግጭቱ ምክንያት ተዘጋግተው የነበሩ የንግድ ቤቶች፣ ሱቆችና ቢሮዎች እንደተከፈቱ፣ ተቋርጦ የነበረው የትራንስፖርት አገልግሎት እንደተጀመረም ምክትል ኃላፊው አስረድተዋል፡፡

ለግጭቱ መቀስቀሱን ራሱን የጋምቤላ ሕዝብ ነፃ አውጪ ግንባር (ጋሕነግ) ብሎ የሚጠራው ታጣቂ ቡድን ተሳታፊ መሆኑን ነዋሪዎቹ ቢገልጹም፣ የፀጥታ ቢሮው ግን ታጣቂዎቹ ተሳትፈዋል ስለመባሉ ማብራሪያ ከመስጠት ተቆጥቧል፡፡

የግጭቱ መነሻ ምንና ማን እንደነበር እንዲያብራሩ የተጠየቁት አቶ ኦቶው፣ ‹‹በመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ከተላለፈው መረጃ መረዳት ይቻላል፤›› ብለዋል፡፡ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ግጭቱ የተቀሰቀሰው አንድ የሚሊሻ አባል በመገደሉ ምክንያት መሆኑን፣ በአኙዋና በኑዌር ብሔረሰቦች መካከል ተኩስ በመከፈቱ ከመሆኑ ውጪ የሰጠው ማብራሪያ የለም፡፡

በልዩ ወረዳው ተፈጠረ የተባለውን የፀጥታ ችግር ለመፍታት የክልሉ መንግሥት ከሚመለከታቸው የክልሉ ኃላፊዎች ጋር፣ ዓርብ ግንቦት 18 ቀን 2015 ዓ.ም. ውይይት እያደረገ እንደነበር አስታውቋል፡፡

ኢታንግ ልዩ ወረዳ 23 ቀበሌዎች እንዳሉትና በዘጠኙ ቀበሌዎች የኑዌር፣ በ11 ቀበሌዎች የአኙዋ፣ በቀሪዎቹ ደግሞ የኮሞና የኡፖ ብሔረሰቦች ተሰባስበው እንደሚገኙበት መረጃዎች ያሳያሉ፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ቪር ጀነራል ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማኀበር የጨረታ ማስታወቂያ

ቪር ጀነራል ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማኀበር በገቢ እና በውጭ ንግድ እንዲሁም...

ያልተቃናው የልጆች የንባብ ክህሎት

አንብቦና አዳምጦ መረዳት፣ የተረዱትን ከሕይወት ጋር አዋህዶ የተቃና ሕይወት...

እንስተካከል!

ሰላም! ሰላም! ውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ እንዲሁም የሰው ዘር በሙሉ፣...

የሙዚቃ ምልክቱ ሙሉቀን መለሰ ስንብት

የኢትዮጵያ ዘመናዊ ሙዚቃ በ1950ዎቹ እና በ1960ዎቹ በኪነ ጥበባትም ሆነ...