Saturday, April 20, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊበኦሮሚያ ክልል አራት ሺሕ ማምረቻ ተቋማት የአካባቢ አሉታዊ ተፅዕኖ ግምገማ ተደርጎላቸው እንደማያውቅ...

በኦሮሚያ ክልል አራት ሺሕ ማምረቻ ተቋማት የአካባቢ አሉታዊ ተፅዕኖ ግምገማ ተደርጎላቸው እንደማያውቅ ተረጋገጠ

ቀን:

በኦሮሚያ ክልል አራት ሺሕ የማምረቻ ተቋማት የአካባቢ አሉታዊ ተፅዕኖ ግምገማ ተደርጎላቸው እንደማያውቅ በኦዲት ግኝት ተገለጸ፡፡

የኦዲት ግኝቱ ይፋ የተደረገው ግንቦት 16 ቀን 2015 ዓ.ም. የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግሥት ወጪ አስተዳደር ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ፣ በአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን የኤሌክትሮኒክስ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድን በተመለከተ በነበረው ውይይት ነው፡፡

የቋሚ ኮሚቴው ምክትል ሰብሳቢ ወ/ሮ አረሬ ሞገስ፣ የአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን በአዋጅ የተሰጠው ሥልጣን፣ ተቋማት በአካባቢ ላይ የሚያስከትሉትን አሉታዊ ተፅዕኖ መገምገም መሆኑን ገልጸዋል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

ይሁን እንጂ ባለሥልጣኑ በኦሮሚያ ክልል አራት ሺሕ ያህል የማምረቻ ተቋማት፣ በአካባቢ ላይ የሚያስከትሉት ጉዳትና የተቋማቱ የቆሻሻ አወጋገድ ግምገማ አለማድረጉን ተናግረዋል፡፡

የባለሥልጣኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ፍሬነሽ መኩሪያ በበኩላቸው፣ በኦሮሚያ ክልል አራት ሺሕ ተቋማት በአካባቢ ላይ የሚያስከትሉት ጉዳት ግምገማ ሳይደረግላቸው የሚለው ሐሳብ፣ ከኤሌክትሮኒክስና ከኤክትሮኒክ ቆሻሻዎች ጋር የሚያያዙ አይደለም ብለዋል፡፡

የፌዴራል ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት ምክትል ዋና ኦዲተር አቶ አበራ ታደሰ፣ በአሮሚያ ክልል ለአራት ሺሕ የማምረቻ ተቋማት ባለሥልጣኑ ፈቃድ እንደሰጣቸው ገልጸዋል፡፡

ይሁን እንጂ የማምረቻ ተቋማቱ በአካባቢ ላይ ለሚያሳድሩት አሉታዊ ተፅዕኖ ግምገማ ተደርጎላቸው ፈቃድ የተሰጣቸው አይደሉም ሲሉ በኦዲት ጊዜ የተገኘውን ግኝት አቶ አበራ አስረድተዋል፡፡

ለዚህም በወቅቱ ባለሥልጣኑ በጉዳዩ ላይ የሰጡት ምላሽ ተፅዕኖ የመገምገም ሪፖርት የሚቀርበው ከመመሥረታቸው በፊት እንደነበር በመግለጽ፣ አሁን ግን የአካባቢ ዕቅድ ፕላን መስጠት እንዳለበት መተማመን ላይ መድረሱን ምክትል ዋና ኦዲተሩ ገልጸዋል፡፡

ባለሥልጣኑ ለቋሚ ኮሚቴው ስለማምረቻ ተቋማቱ የሰጠው ምላሽ ከኦዲት ግኝቱ ጋር የማይቀራረብ ነው ሲሉም ከዚህ ቀደም የነበረውን ግኝት ጠቁመዋል፡፡

የተራዘመ የአምራች ኃላፊነት ሥርዓት ባለመዘርጋቱ በተለይ ኢትዮ ቴሌኮም የሚወገዱ ወደ ስድስት ሚሊዮን ብር የሚያወጡ 3,979 ያህል መሣሪያዎች ተከማችተው እንደሚገኙ፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 7,796 ያህል መወገድ ያለባቸው ቁሶች እንደተከማቹ በኦዲት ተገኝቷል ብለዋል፡፡

ባለሥልጣኑ ፈቃድ የመስጠት፣ ቁጥጥርና ክትትል የማድረግ ሥልጣን እንዳለው የገለጹ አንድ የቋሚ ኮሚቴው አባል፣ እነዚህ ሥራዎች ለሙስናና ለብልሹ አሠራር የተጋለጡ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

የመንግሥት ግዥ አገልግሎትን ወክለው በውይይቱ ላይ የተገኙት አንድ ባለሙያ፣ በዘርፉ ውስጥ የሚሠሩ ተቋማት ውስን መሆናቸውን እንደ ችግር አንስተዋል፡፡ በዘርፉ ውስጥ የሚገኙ ተቋማት ቁጥራቸው ዝቅተኛ በመሆኑ ጨረታ ሲመጣ  ተወዳዳሪ አለማግኘትም አንዱ ማነቆ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ጌታሁን ጋረደው (ዶ/ር)፣ ‹‹በኦዲት ግኝቱ ላይ የታዩ ችግሮችን በሒደት እንፈታለን፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በአገር ውስጥ መወገድ የማይችሉ እንደ ዲዲቲና ሌሎች ኬሚካሎችን በዓለም አቀፍ ስምምነት መሠረት እንዲወገዱ ይደረጋሉ፤›› ብለዋል፡፡

በዚህ አወጋገድ ሥርዓት እንደገና ከፍተኛ ወጪ የሚጠይቁ መሆናቸውን ገልጸው፣ ካለው ከእውነታ አንፃር የኤሌክትሮኒክስ ቆሻሻዎችን ማስወገድ ላይ የሚንቀሳቀሱ ሦስት ተቋማት ብቻ ናቸው ብለዋል፡፡ በኦሮሚያ ክልል አራት ሺሕ የማምረቻ ተቋማት ከኤሌክትሮኒክስ ጋር የሚያያዙ ሳይሆኑ፣ የአካባቢና ማኅበራዊ ተፅዕኖ ዳሰሳ ሳይሠሩ ሥራ የጀመሩ ናቸው በማለት አብራርተዋል፡፡

በኦሮሚያ ክልል ከአንድ መቶ ያላነሱ የማምረቻ ተቋማት የአካባቢ ማኔጅመንት ፕላን አውጥተው እየተገበሩ ናቸው ሲሉ ዋና ዳይሬክተሩ አስረድተዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ሰላማዊ የፖለቲካ ትግልና ፈተናው

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) የፖለቲካ ኦፊሰር የአቶ በቴ ኡርጌሳን...

አበጀህ ማንዴላ! አበጀሽ ደቡብ አፍሪካ!

በአየለ ት. የፍልስጤም ጉዳይ የዓለም አቀፍ ፖለቲካንም ሆነ የተባበሩት መንግሥታትን...

የውጭ ባለሀብቶች ለኢትዮጵያውያን ብቻ በተፈቀዱ የንግድ ዘርፎች እንዲገቡ የመወሰኑ ፋይዳና ሥጋቶች

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አዓመድ (ዶ/ር) የውጭ ኩባንያዎች በጅምላና ችርቻሮ...