Thursday, April 18, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
- Advertisement -

ፌርማታ ፅሁፎች

ናፍቆት የሚያሳድረው አገር

ትኩስ ፅሁፎች

አገር በታሪክ በቋንቋ በሃይማኖት  በልማድ  በተስፋ  በደስታና በመከራ ተሳስሮ የሚኖር አንድ ወገን  የሆነ  ሕዝብ  የሚኖርበት  የዓለም  ክፍል  ነው፡፡

አገር ማለት  አያት ቅድመ አያት የተወለዱበት አድገውም በጀግንነት ከውጭ ጠላት እየተከላከሉ ለሕዝብና ለመንግሥት የሚጠቅም ሥራ ሠርተው ዕድሜያቸው ሲደርስም  ልጆቻቸውን  ተክተው የተቀበሩበት ጉድጓድ ነው፡፡

በመወለድ ዕትብት በመሞት አካል ከአፈሩ ጋራ ስለሚዋሀድ የአገሩ አፈር ሕዝቡ በላዩ የሚኖርበት ማለት ነው፡፡

እግዚአብሔር ከምድርዋ ፍሬ ሕይወት እንዲገኝባት በማድረጉ አገር እያጠባች  የምታሳድግ ፍቅርዋ በአጥንት በሥጋ ገብቶ የማይደመሰስ የሆነች እናት  ማለት ነው፡፡

ከልጅነት ጀምሮ ወንዙን ተራራውን ሜዳውን ቆላውንና ደጋውን በማየት ስለ ማደግ አባቶች በሕይወትና በአገር እስካሉ ሲታይ በስደት ሲሆኑ ሲታሰብ ፍቅርና በሞት የሠሩበት  ደግ ሥራ በአዕምሮ ታትሞ ስለቀረ ናፍቆት የሚያሳድር አገር ነው፡፡

አገር አባት እናት ዘመድ ምግብ ጌጥና ሀብት በመሆኑ ድህነትና ጥቃት በመጣ  ቁጥር  እስከ ሞት ድረስ እንዲሠራበት ከአያት ከቅድመ አያትና ከአባቶች በጥብቅ የተሰጠ ያደራ  ገንዘብ ነው።

  • ከበደ ሚካኤል ‹‹የቅኔ ውበት››
- Advertisement -
- Advertisement -

ተጨማሪ ለማንበብ

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች