Wednesday, June 7, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
- Advertisement -

ፌርማታ ፅሁፎች

የጎርፉና የሐይቁ ሽማግሌዎች

ትኩስ ፅሁፎች

ወቅቱ የዝናብ ወቅትና በጣም ብዙ የሚዘንብበት ጊዜ ስለሆነ ብዙ የጎርፍ አጋጣሚዎች ነበሩ፡፡ ጎርፉም እያደር በየቦታው በመዳረስና በየአካባቢው እየተዥጎደጎደ ዛፎችን በመገንደስ፣ እንስሳትን እየጠራረገ እያደር ጉልበቱ እየበረታ ሄደ፡፡

በኃያልነቱም ምክንያት በጣም፣ በጣም ትምክህተኛ ስለሆነ በታሪክ ታላቁ ጎርፍ የሆነ መሰለው፡፡

ጎርፉም አንድ በጣም ቆንጆ ወንድ ልጅ ነበረውና ልጁን ሊድረው ፈልጎ ሐይቁ ደግሞ በጣም፣ በጣም ቆንጆ ሴት ልጅ ነበረውና ጎርፉ ልጁ ይህችን የሐይቁን ልጅ እንዲያገባት ፈለገ፡፡

እናም በባህሉ መሠረት ጎርፉ ያገር ሽማግሌዎችን ወደ ሐይቁ ቤት በመላክ ልጁን እንዲድርላቸው አስጠየቀው፡፡ ሽማግሌዎቹም ወደ ሐይቁ ቤት ሄደው ልጁን ለጋብቻ ጠየቁት፡፡

በዚህ ጊዜ ሐይቁ እጅግ በጣም ተቆጥቶ ‹‹ይህ ጊዜያዊና ነገ የሚያልፍ ወቅታዊ ክስተት እንዴት ልጄን ለጋብቻ ይጠይቃል?›› ብሎ በመቆጣት በንዴት ጥያቄውን አሻፈረኝ ብሎ ሊመልስ ሲል ከእርሱ ወገን ያሉት ያገር ሽማግሌዎች ‹‹ቆይ፣ ጎርፉን አሁን ልታሳዝነው አይገባም፡፡ እስኪ ጉዳዩን እንያዘውና ከራሳችን ጋር እንማከር፤›› ብለው አረጋጉት፡፡

ከዚያም የሐይቁ ሽማግሌዎች የጎርፉን ሽማግሌዎች ‹‹ተመልከቱ፣ እኛ ስለሙሽራው፣ ስለ አባቱና ስለዘመዶቹ ብዙ ነገር ማወቅ እንፈልጋለንና በባህላችን መሠረት ቀጠሮ እንስጣችሁና በቀጠሮው ቀንም ሁላችሁም ትመጡና ተቀባይነት ካገኛችሁ ልጃችንን ልንሰጣችሁ እንችላለን፤›› አሏቸው፡፡

የጎርፉም ሽማግሌዎች በዚህ ተስማምተው የሐይቁም ሽማግሌዎች እንዲህ አሏቸው፣ ‹‹እንግዲያው ቀጠሮአችን በፓርሱስ 26 ቀን እንዲሆን ቆርጠናል፤›› የፓርሱስ ወር በደረቁ ወቅት አማካይ ላይ የሚውል ወር ሲሆን፣ በዚህ ወር ምንም ዝናብ የለም፡፡ ስለዚህ በግልፅ ማየት እንደሚቻለው ይህ ወር ሲገባ ምንም ዓይነት ጎርፍም ሆነ ዝናብ ስለማይኖር ማንም ሰው በቀጠሮው ቀን አልመጣም፡፡

የዚህ ታሪክ መልእክትም በጊዜያዊ ስኬት መታበይ እንደሌለብንና ሁሉም ጊዜውን እንደሚጠብቅ የሚያሳይ ነው፡፡

  • ይስሐቅ አልዳዴ ‹‹የወላይታ ተረት››
- Advertisement -
- Advertisement -

ተጨማሪ ለማንበብ

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች