Thursday, June 1, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትዋሊያዎቹ በአሜሪካ ጉዟቸው የሚገጥሙት ብሔራዊ ቡድን ታውቋል

ዋሊያዎቹ በአሜሪካ ጉዟቸው የሚገጥሙት ብሔራዊ ቡድን ታውቋል

ቀን:

  • ብሔራዊ ቡድኑ ጨዋታ የሚያደርግበት ቀን ቅሬታ አስነስቷል

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን (ዋሊያዎቹ) ወደ አሜሪካ ተጉዞ የሚገጥመውን ብሔራዊ ቡድን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል፡፡ ብሔራዊ ቡድኑ በክረምት በሚያደርገው የወዳጅነት ጨዋታ የሚገጥመው የካሪቢያን እግር ኳስ ማኅበር አባል የሆነውን የጉያን ብሔራዊ ቡድንን ነው፡፡

ብሔራዊ ቡድኑ የመጀመርያ ጨዋታውን ሐምሌ 1 ቀን 2015 ዓ.ም. በፊላደልፊያ ሱባሩ ፓርክ ያደርጋል፡፡ እንደ ፌዴሬሽኑ ማብራሪያ ከሆነ የሰሜንና የመካከለኛው አሜሪካ እንዲሁም የካሪቢያን እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን አባል ከሆነችው አገር ጋር ለሚደረገው ጨዋታ የትኬት ሽያጭ እንዲያከናውን ‹‹ሲጄኤ›› ከተባለ ድርጅት ጋር ተስማምቷል፡፡ የዋሊያዎቹ ሙሉ ወጪ በድርጅቱ እንደሚሸፈንና በቆይታቸውም ከተለያዩ ቡድኖች ጋር የወዳጅነት ጨዋታ እንደሚያደርጉም ተገልጿል፡፡

በአንፃሩ ብሔራዊ ቡድኑ የወዳጅነት ጨዋታ የሚያደርግበት ቀን የሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያውያን ስፖርትና ባህል ማኅበር ዓመታዊ ውድድሩን የሚያጠናቅቅበት ዕለት በመሆኑ ቅሬታ አስነስቷል፡፡

በዚህም መሠረተ ሐምሌ 1 ቀን የሰሜን አሜሪካ የእግር ኳስ ውድድር የዋንጫ ጨዋታ በዳላስ፣ ቴክሳስ የሚያደርግበት ቀን እንደሆነና ኢትዮጵያውያን 40ኛ ዓመታቸውን የሚያከብሩበት ቀን በመሆኑ፣ ዋሊያዎቹ ተመልካች ሊያገኙ እንደማይችሉ ተነስቷል፡፡

በሌላ በኩል የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን የሚመሩትን ዋና አሠልጣኝ ይፋ ማድረጉ ይታወሳል። ከአሠልጣኝ ውበቱ አባተ ጋር ውሉን ያቋረጠው ፌዴሬሽኑ፣ ቡድኑን በጊዜያዊነት የሚመሩ አሠልጣኞች ስም ይፋ አድርጓል።

ፌዴሬሽኑ ብሔራዊ ቡድኑን ላለፉት ሁለት ዓመታት ሲመሩ ከቆዩት አሠልጣኝ ውበቱ አባተ ጋር በስምምነት ከተለያየ በኋላ፣ ቀጣዩን አሠልጣኝ ለመምረጥ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ባደረገው ውይይት፣ በቴክኒክ ዳይሬክተርነት እየሠሩ የሚገኙት ኢንስትራክተር ዳንኤል ገብረ ማርያም በጊዜያዊ ዋና አሠልጣኝነት ቀጣይ ጨዋታዎችን እንዲመሩ ከውሳኔ መድረሱን አስታውቋል።

ዋሊያዎቹ ወደ አሜሪካ የሚያደረጉትን ጉዞ በጊዜያዊ አሠልጣኞቹ እንደሚመሩም ታውቋል፡፡

ኢንስትራክተር ዳንኤልን እንዲያግዙ በፕሪሚየር ሊጉ በመሥራት ላይ የሚገኙና በወቅታዊ ውጤታማነትም የተሻሉ ሆነው የተገኙት የባህር ዳር ከተማ አሠልጣኝ ደግአረገ ይግዛው ምክትል አሠልጣኝ ሆነው እንዲሠሩ ከውሳኔ መድረሱን ፌዴሬሽኑ ገልጿል።

ከዚህም ባሻገር ፌዴሬሽኑ ለአሠልጣኙና ለክለባቸው ባህር ዳር ከተማ ጥያቄ አቅርቦ ፈቃደኛ በመሆናቸው፣ ምክትል አሠልጣኝ ሆነው ተሾመዋል ሲል ገልጿል። በሌላ በኩል በቅርቡ በተሰናበቱት የበረኛ አሠልጣኝ ደሳለኝ ገብረ ጊዮርጊስ ምትክ  የቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ የግብ ጠባቂዎች አሠልጣኝ ውብሸት ደሳለኝን ሆነው መሾማቸው ይታወሳል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የአዛርባጃንን ብሄራዊ ቀን በአዲስ አበባ በድምቀት ተከበረ

የአዛርባጃን ኤምባሲ  የአዛርባጃንን ብሄራዊ ቀን በትላንትናው ዕለት አከበረ። ሰኞ...

የመንግሥትና የሃይማኖት ልዩነት መርህ በኢትዮጵያ

እንደ ኢትዮጵያ ባሉ አገሮች የሃይማኖት ተቋማት አዎንታዊ ሚና የጎላ...

ሐበሻ ቢራ ባለፈው በጀት ዓመት 310 ሚሊዮን ብር የተጣራ ትርፍ ማግኘቱን አስታወቀ

የአንድ አክሲዮን ሽያጭ ዋጋ 2,900 ብር እንዲሆን ተወስኗል የሐበሻ ቢራ...