በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኘው፣ አዲሱ የሳይንስ ሙዚየም ውስጥ የተዘጋጀው የግብርና ሳይንስ ዓውደ ርዕይ በኅብረተሰቡ እየተጎበኘ ነው፡፡ ‹‹ከቤተ ሙከራ ወደ አዝመራ›› በሚል ርዕስ የተዘጋጀው የግብርና ዓውደ ርዕይ ምርትና ምርታማነት የሚጨምሩ የምርምርና ፈጠራ፣ የቴክኖሎጂዎች ውጤቶች ለዕይታ ቀርበውበታል። የፓርላማ እንደራሴዎችን ጨምሮ የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች እየጎበኙት ያለው ዓውደ ርዕይ፣ እሑድ ሚያዝያ 29 ቀን 2015 ዓ.ም. የተከፈተ ሲሆን፣ እስከ ሰኞ ግንቦት 28 ቀን ድረስ ለተመልካቾች ክፍት ሆኖ ይቆያል፡፡
- ፎቶ ታምራት ጌታቸው