Wednesday, June 7, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናቁሕዴፓ ፓርቲ አባላቱ ከታሰሩ ከሰባት ወራት በኋላ ክስ እንደተመሠረተባቸው ገለጸ

ቁሕዴፓ ፓርቲ አባላቱ ከታሰሩ ከሰባት ወራት በኋላ ክስ እንደተመሠረተባቸው ገለጸ

ቀን:

የቁጫ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ቁሕዴፓ) 28 አባላቱ ከታሰሩ ከሰባት ወራት በኋላ ግንቦት 10 ቀን 2015 ዓ.ም.  ክስ እንደተመሠረተባቸው አስታወቀ፡፡

‹‹ቁሕዴፓን ደግፋችሁ የብልፅግና ፓርቲን ነቅፋችኋል›› የተባሉ ከ35 በላይ የሚሆኑ በወቅቱ ታስረው የነበሩ ቢሆንም 28ቱ አባላት ግን ከጥቅምት ወር 2015 ዓ.ም. እስከ ሚያዝያ ወር 2015 ዓ.ም. አባላቱ ለሰባት ወራት ታስረው እንደሚገኙና ከሰባት ወራት በኋላ ለመጀመርያ ጊዜ ክስ እንደተመሠረተባቸው የፓርቲው ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ በቀለ አበራ ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡

በእስር ላይ ከሚገኙት 35 አባላቱ መካከል ሰባቱ የምክር ቤት አባልና አመራሮች መሆናቸውን የገለጹት አቶ በቀለ፣ በወረዳ ፍርድ ቤት ተከሰው የተፈረደባቸው ቢሆንም ለዞን ፍርድ ቤት ይግባኝ ብለው እየተከራከሩ መሆናቸውን አስረድተዋል፡፡

ከ35 የፓርቲው አባላት መካከል 28 ያህሉ በጥቅምት ወር 2015 ዓ.ም. ቢታሰሩም እስከ ሚያዝያ ወር ፍርድ ቤት እንዳልቀረቡ፣ ከሰባት ወራት ቆይታ በኋላ ግንቦት 10 ቀን 2015 ዓ.ም. ፍርድ ቤት ቀርበው እያንዳንዳቸው 11 ዓይነት ክሶች እንደተመሠረተባቸውም አክለዋል፡፡

ከ28ቱ የፓርቲው አባላት ውስጥ 16 ተማሪዎች ሲሆኑ፣ 12 ደግሞ ነጋዴና አርሶ አደር የፓርቲው አባላት መሆናቸውንና ይህን ያህል ጊዜ ሲቆዩ ፍርድ ቤት ባለመቅረባቸው ፓርቲው ለኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽንና ለተለያዩ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች አቤቱታ ካቀረበ በኋላ ክስ ተመሥርቶባቸዋል ብለዋል፡፡

የፓርቲው ፕሬዚዳንት አቶ ተስፋዬ ፈልሃ በበኩላቸው፣ የፓርቲው አባላትና ደጋፊዎች በአርባ ምንጭ ማረሚያ ቤት ታስረው እንደሚገኙ  ለሪፖርተር አስረድተዋል፡፡

የፓርቲው አመራሮችና ደጋፊዎች በ2013 ዓ.ም. ምርጫ ወቅት ሕዝቡን በከተፍኛ ሁኔታ አነቃቅታችኋል ተብለው በብልፅግና ፓርቲ ካድሬዎች እስራትና ድብደባ እየደረሰባቸው መሆኑን አክለዋል፡፡

በፓርቲው አባላት ላይ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እየተፈጸመ መሆኑን የጠቀሱት ፕሬዚዳንቱ፣ ለኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን፣ ለኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ጉባዔና ለሌሎች የሚመለከታቸው የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች እንዳሳወቁ ገልጸዋል፡፡

አንድ ተጠርጣሪ በ48 ሰዓት ውስጥ ፍርድ ቤት መቅረብና የተጠረጠሩበትን ጉዳይ ማወቅ  እንዳለበት ገልጸው፣ የፓርቲው አባላት በማረሚያ ቤት ታጉረው ለወራት እንደቆዩ፣  ፓርቲው የታሰሩ ሰዎችን ለማስፈታት አቤቱታ ቢያሰማም እስካሁን ጉዳዩ ገና በሒደት ላይ እንደሆነ አቶ ተስፋዬ አስረድተዋል፡

በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቁጫ ምርጫ ክልል ሕዝብ ተወካይ ገነነ ገድሉ (ረዳት ፕሮፌሰር)፣ ‹‹የቁጫ ወጣት በመንግሥት አካላት ታስሯል፣ ተደብድቧል፡፡ የምታጠባ እናት ከልጆቿ ፊት ተወስዳ ተገርፋለች፡፡ አርሶ አደሩ ከእርሻው ተጎትቶ በመደበኛ የፖሊስ ኃይል እስኪቆስል ድረስ ተደብድቧል፡፡ እስከ ወር ድረስም የታሰሩበት አጋጣሚ ነበር፤›› ሲሉ ገልጸዋል፡፡

‹‹ቁጫ ውስጥ እስርና ድብደባ ያልቀመሰ ሰው የለም፤›› ያሉት ገነነ (ረዳት ፕሮፌሰር)፣ በነጋዴዎች ላይ ደረሰ ያሉትን በደል ሲገልጹም፣ ‹‹በደበቡብ ክልል የሕዝብ ምክር ቤት አባላት የንግድ ቤታቸው፣ ሆቴላቸውና የመድኃኒት መደብራቸው በፖሊሶች በጉልበት ተዘግቶባቸዋል፤›› ብለዋል፡፡

በጥቅሉ የቁጫ ሕዝብ ታፍሶ እስከ አምስት ወራት ድረስ እንደታሰረ፣ አሁንም ቢሆን ከፓርቲው አመራሮች በተጨማሪ 28 የፓርቲው ደጋፊዎች በአርባምንጭ ማረሚያ ቤት ታስረው እንደሚገኙ አስረድተዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ኢሰመኮ በዩኒቨርሲቲዎች የአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ጉዳይ የሚመራበት የጽሑፍ ፖሊሲ አለመኖሩን አስታወቀ

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች...

ንግድ ባንኮች በከፍተኛ የገንዘብ እጥረት ውስጥ መሆናቸው ተገለጸ

‹‹የገንዘብ እጥረት የሚገጥመው ያለውን ሀብት የማስተዳደር ችግር ስላለ ነው›› የኢትዮጵያ...

ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከ2,700 በላይ ሰዎች በትራፊክ አደጋ ሕይወታቸውን ማጣታቸው ተገለጸ

ከ1.7 ቢሊዮን ብር በላይ የንብረት ጉዳት ደርሷል በአበበ ፍቅር ባለፉት ዘጠኝ...