Wednesday, June 7, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ኪንና ባህልቱሪዝሙን ያበረታታል የተባለው ዓውደ ርዕይ

ቱሪዝሙን ያበረታታል የተባለው ዓውደ ርዕይ

ቀን:

በአበበ ፍቅር

የቱሪዝም ኢንዱስትሪው ያለበትን ደረጃ ለማሳየትና ዜጎች ቱሪዝም ትልልቅ የሥራ ዕድል የሚፈጠርበት መሆኑን እንዲያውቁ ምቹ ሁኔታን የሚፈጥር የመስተንግዶና የክህሎት ሳምንት ኤግዚቢሽን (ዓውደ ርዕይ) ተካሂዷል፡፡

የቱሪዝም ዘርፉ ከሁሉም የተለየ ተልዕኮ የተሰጠውና ከሌላው ዘርፍ የተለየ ዕድል ያለው ዘርፍ ነው ሲሉ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በኤግዚቢሽኑ መክፈቻ ላይ ንግግር አድርገዋል፡፡

ዕድሉን ለመጠቀም በክህሎት የበለፀገ የሰው ኃይል ለዘርፉ የምርጫ ጉዳይ አይሆንም ያሉት ሚኒስትሯ፣ ‹‹ክህሎት ለተወዳዳሪነት›› በሚል አሥረኛው የመስተንግዶና የክህሎት ሳምንት ግንቦት 8 ቀን 2015 ዓ.ም. በተጀመረበት ወቅት ነው፡፡

‹‹ክህሎት ለተወዳዳሪነት›› ሲባል በዘርፉ ውስጥ ተወዳዳሪነትን በማረጋገጥ ኢኮኖሚውን መደገፍ የሚያስችል ባለ ድርብ ተልዕኮ ነውም ብለዋል፡፡ ተቀራርቦ በመሥራት ረገድ የተሠራው ሥራ በቂ ባለመሆኑ በተለይ ደግሞ የግል ሴክተሩ ከዚህ በላይ መሥራት ይጠበቅበታል ብለዋል፡፡

የመንግሥት አካላትም ከዚህ በፊት ከነበረው ተነሳሽነት በላቀ ሁኔታና ቁርጠኝነት መሥራትን ይጠይቃል ሲሉ ሚኒስትሯ ተናግረዋል፡፡

ቱሪዝም ‹‹አኩራፊ የሚባል ዘርፍ ነው፤›› ያሉት ደግሞ የቱሪዝም ማሠልጠኛ ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ገዛኸኝ አባተ ናቸው፡፡

‹‹በጣም በትንሽ ነገር የሚቆጣ፣ ሰላም ሲኖር ፍሰቱ የሚጨምር፣ ሰላም ሲጠፋ ደግሞ አብሮ የሚጠፋ፣ እንዲሁም ከሰው ሠራሽና ከተፈጥሮ አደጋ ጋር አብሮ የሚረበሽ ዘርፍ ነው፤›› ብለዋል፡፡

ይህንን አኩራፊ የሆነ ኢንዱስትሪ ማሻሻል የሚቻለው በአገር ውስጥ ጎብኝዎች ላይ ትኩረት በማድረግ ነው ብለዋል ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ፡፡

በቱሪዝም ማሠልጠኛ ኢንስቲትዩት የሚማሩና ተመርቀው የወጡ ወጣቶች የራሳቸውን ሥራ በመፍጠር ውጤታማ እንዲሆኑ ያግዛቸዋል ያሉት አቶ ገዛኸኝ፣  የአስጎብኚ ድርጅቶችና የሆቴል አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ሥራቸውን ያሳዩበት፣ እንዲሁም አዳዲስ ሠልጣኞች ከሆቴልና ቱሪዝም ዘርፍ ከተሰማሩ ቀጣሪ መሥሪያ ቤቶች የሚገናኙበት ዓውደ ርዕይ ነው ብለዋል፡፡

በተቋሙ ተምረውና በግላቸው ተደራጅተው በቱሪዝም ዘርፍ ለሚሰማሩ ሥራ ፈጣሪዎች ከሙያዊ ሥልጠና ባሻገር የመኪናና ሌሎች ድጋፎችን እንደሚያደርጉ ተናግረዋል፡፡

ነገር ግን ይህ ድጋፍ ዘላቂ አይሆንም ያሉት አቶ ገዛኸኝ፣ ይልቁንስ ከሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ጋር በመሆንና ኢንተርፕሪነር በማቋቋምና ሥልጠና በመስጠት ወጣቶች ተቀጣሪ ሳይሆኑ ሥራ ፈጣሪ እንዲሆኑ እያበረታታን ነው ብለዋል፡፡

በዓውደ ርዕዩ ከቀረቡት መካከል በሆቴሎች ላይ የሚታየውን የእንግዳ አቀባበል፣ የባህላዊ ምግብና መጠጦች፣ እንዲሁም የዳቦ አቀራረብና የተለያዩ የኢትዮጵያን ገጽታ የሚያሳዩ ፎቶዎች ቀርበዋል፡፡

በሌላ በኩል በቱሪዝም ዘርፉ ተሠማርተው ከሚሠሩ ድርጅቶች መካከል ሪፖርተር ያነጋገራቸው የሙሉ ኢኮሎጅ የጮቄ ተራራ ኢኮ ቱሪዝም መሥራች የሆኑት አቶ ዓብይ ዓለሙ ‹‹ቢሮክራሲው አላሠራኝ ብሏል›› ሲሉ ቅሬታቸውን ገልጸዋል፡፡

ሙሉ ኢኮሎጅ አርሶ አደሩንና ቱሪስቱን በማገናኘት በተለይ ደግሞ በገጠራማው የኢትዮጵያ ክፍል ያለውን የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ የሚያስተዋውቅ አስጎብኚ ድርጅት ነው፡፡

በሥራቸው የአማራ ክልልም ሆነ የኢትዮጵያ ቱሪዝም ቢሮ ድጋፍና ማበረታታት እያደረጉልኝ አይደለም ያሉት አቶ ዓብይ፣ ከዚህ ይልቅ በመንግሥት በኩል የሚጠናቀቁ ጉዳዮችን ለማግኘት በጣም አዳጋች እንደሆነባቸው ተናግረዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ሒዩማን ራይትስዎች ያወጣው ሪፖርት የዕርቅና የምክክር ሒደቱን እንደሚያደናቅፍ መንግሥት አስታወቀ

በትግራይ የሰላም ስምምነት ተግባራዊ በሚደረግበት ወቅት የዘር ማፅዳት እየተካሄደ...

የመጪው ዓመት አገራዊ በጀት ሁለት በመቶ አድጎ ለፓርላማ ተመራ

የሚኒስትሮች ምክር ቤት የ2016 ዓ.ም. በጀት እየተጠናቀቀ ካለው በጀት...

አገር አጥፊ ድርጊቶች በአገር ገንቢ ተግባራት ይተኩ!

ኢትዮጵያ ውስጥ በስፋት የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት በመንስዔዎች ላይ መግባባት...

በትግራይ ተቋርጦ የነበረው የምግብ ዕርዳታ እንዲጀምር አቶ ጌታቸው ጥያቄ አቀረቡ

የዓለም ምግብ ፕሮግራምና የአሜሪካ ዓለም አቀፍ የልማት ተራድዖ ድርጅት...