የታሪክ ተመራማሪና የምሥራቅ አፍሪካ ቀጣናዊ ጉዳዮችን የሚከታተሉት መሀመድ ሀሰን (ፕሮፌሰር)፣ የሱዳንን ወቅታዊ ጉዳይ በተመለከተ ለዲደብሊው የተናገሩት፡፡ በሱዳን ወታደራዊ ኃይሎች መካከል የተፈጠረውን ግጭት ለማስቆም የሁለቱም ወገኖች ተወካዮች፣ በሳዑዲ ዓረቢያ ጂዳ እየተነጋገሩ መሆኑን ተከትሎ ለሚዲያው አስተያየታቸውን የሰጡት ፕሮፌሰሩ፣ ተፋላሚዎቹ በሱዳን ታሪክ ላይ ግጭትም ሆነ በዚያ ላይ ትርክት የላቸውም ያሉ ሲሆን፣ ግጭቱ በቶሎ መፍትሔ እንደሚያገኝ ተስፋ እንዳላቸውም ጠቁመዋል።