Wednesday, June 7, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናበቢሾፍቱ ስለተገደሉ የፖሊስ አባላት ጉዳይ ምርመራ መጀመሩን የከተማው ከንቲባ አስታወቁ

በቢሾፍቱ ስለተገደሉ የፖሊስ አባላት ጉዳይ ምርመራ መጀመሩን የከተማው ከንቲባ አስታወቁ

ቀን:

በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ሸዋ ዞን ቢሾፍቱ ከተማ በታጣቂዎች ስለተገደሉት አራት የፖሊስ አባላት ጉዳይ ምርመራ መጀመሩን፣ የቢሾፍቱ ከተማ ከንቲባ ለሪፖርተር ገለጹ፡፡

በታጠቁ ኃይሎች ስለተገደሉት የፖሊስ አባላት ምርመራ እየተደረገ መሆኑን፣ የቢሾፍቱ ከተማ ከንቲባ አቶ ዓለማሁ አሰፋ ተናግረዋል፡፡

በታጣቂዎች ደርሷል የተባለውን የሞትና የመቁሰል ጥቃት በተመለከተ ማብራሪያ እንዲሰጡ ከሪፖርተር ጥያቄ የቀረበላቸው የቢሾፍቱ ከተማ ከንቲባ አቶ ዓለማየሁ፣ ጥቃት አደረሱ በተባሉት ታጣቂዎች ላይ፣ ‹‹ምርመራ ላይ ስለሆንን ስለጉዳዩ ብዙ መረጃ መስጠት አንፈልግም፤›› የሚል ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ በታጣቂዎች ማንነት ላይ እየተደረገ ያለው ምን ዓይነት ምርመራ እንደሆነ ሲጠየቁም፣ ‹‹እሱ ላይም ምንም ዓይነት መረጃ አልሰጥም፡፡ ገና ነው፡፡ መጣራት አለበት፤›› ብለው ጉዳዩን በሒደት እንደሚያስታውቁ ገልጸዋል፡፡

ታጣቂዎች በቢሾፍቱ ከተማ ሰንሻይን ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ ላይ እሑድ ግንቦት 6 ቀን 2015 ዓ.ም. እኩለ ሌሊት ላይ ተኩስ መክፈታቸውን፣ በተኩስ ጥቃቱም በፖሊስ ጣቢያው የነበሩ አራት አባላት መገደላቸውን፣ በአንድ የፖሊስ አባል ላይ ደግሞ ከፍተኛ የመቁሰል አደጋ መድረሱ ታውቋል፡፡

ታጣቂዎች አደረሱት በተባለው የግድያና የማቁሰል አደጋ ምን ምላሽ እንዳላቸው ሪፖርተር ጥያቄ ያቀረበላቸው የኦሮሚያ ክልል የኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ኃይሉ አዱኛ፣ ጉዳዩን በተመለከተ የቢሾፍቱ ከተማ ከንቲባ ማብራሪያ መስጠት እንዳለበት ጠቁመው፣ ደረሰ ስለተባለው ጥቃት ምላሽ ከመስጠት ተቆጥበዋል፡፡

ታጣቀዎቹ ጥቃቱን ያደረሱት እሑድ ከሌሊቱ ስድስት ሰዓት መሆኑን፣ ይህን ጥቃት ከማድረሳቸው ከቀናት በፊት በቢሾፍቱ ከተማ ልዩ ስሙ ‹‹አድላላ›› በሚባለው አካባቢ ተኩስ ከፍተው እንደነበር የገለጹት የአካባቢው ነዋሪዎች፣ ከዚህ የከፋ ጥቃት ይደርሳል የሚል ሥጋት እንዳደረባቸውና መንግሥትም ለጉዳዩ ትኩረት እንዲሰጥ መጠየቃቸውን ተናግረዋል፡፡

ደረሰ የተባለውን ጥቃት በተመለከተ ማብራሪያ እንዲሰጡ ሪፖርተር በስልክ ጥያቄ ያቀረበላቸው የኦሮሚያ ክልል አስተዳደርና የሰላምና ፀጥታ ቢሮ ምክትል ኃላፊ ኮሎኔል አበበ ገረሡ፣ ጉዳዩን አስመልክቶ ‹‹የደረሰኝ መረጃ የለም›› ብለዋል፡፡

በቢሾፍቱ የተፈጸመውን ጥቃት አድርሰዋል የተባሉት ታጣቂዎች ራሱን የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ብሎ የሚጠራው በሽብርተኝነት የተፈረጀው ኦነግ ሸኔ አባል ናቸው ቢባልም፣ ቢሾፍቱ ላይ ደረሰ ስለተባለው ጥቃት የገለጸው ነገር ባይኖረም፣ በምዕራብ ሸዋ ሜታ ወልቂጤ አሉኝ ባላቸው ይዞታዎች ላይ የመንግሥት ኃይሎች ጥቃት እንዳደረሱበት በትዊተር ገጹ አስታውቆ ነበር፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

አወዛጋቢው የሕገ መንግሥት ማሻሻያ ጉዳይ

በኢትዮጵያ የሕገ መንግሥት ማሻሻል ጉዳይ ከፍተኛ የፖለቲካ ውዝግብ የሚቀሰቀስበት...

 መፍትሔ  ያላዘለው  የጎዳና  መደብሮችን  ማፍረስ

በአበበ ፍቅር ያለፉት ስድስት ዓመታት በርካቶች በግጭቶችና በመፈናቀሎች በከፍተኛ ሁኔታ...

የተናደው ከቀደምቱ አንዱ የነበረው የአዲስ አበባ ታሪካዊ ሕንፃ

ዳግማዊ አፄ ምኒልክ በ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ መናገሻ ከተማቸውን...

የአከርካሪ አጥንት ሕክምናን ከፍ ያደረገው ‘ካይሮፕራክቲክ’

በአፍሪካ ከጀርባ ሕመም ጋር በተያያዘ በርካታ ሰዎች ለከፍተኛ የአካል...