Friday, June 2, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ኪንና ባህልበኢትዮጵያና ኢንዶኔዥያ ምሁራን የተዘጋጀው መጽሐፍ

በኢትዮጵያና ኢንዶኔዥያ ምሁራን የተዘጋጀው መጽሐፍ

ቀን:

በአዲስ አበባ የሚገኘው የኢንዶኔዥያ ኤምባሲ፣ በኢትዮጵያና ኢንዶኔዥያ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ የሚሠሩ ምሁራን የተሳተፉበት ጥራት ያለው አስተሳሰብን የሚያንፀባርቅ፣ ‹‹ኳሊቲ ቲንኪንግ በ21ኛው ክፍለ ዘመን›› የተሰኘ መጽሐፍ መሰንበቻውን ይፋ አድርጓል፡፡

በአምስት ኢትዮጵያውያንና በሁለት ኢንዶኔዥያውያን ምሁራን በትብብር የተጻፈው ይህ መጽሐፍ፣ በዋነኛነት ለ21ኛው ክፍለ ዘመን ችግሮች ጊዜውን የሚመጥን መፍትሔ ያመላከተ ሲሆን፣ በተለይም በሁለቱ አገሮች መካከል የሚደረግን ግንኙነት ወቅቱ ከሚፈልገው አስተሳሰብ በመነጩ ዕይታዎች መሆን እንዳለበት ያብራራል፡፡

በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዘመነ መንግሥት (1923-1967) የጀመረውና ለረዥም ዓመታት የዘለቀው የኢትዮጵያና ኢንዶኔዥያ የዲፕሎማሲ ግንኙነት አሁን ላይ የአገሮቹ ዓመታዊ የንግድ ትስስር 70 ሚሊዮን ዶላር ደርሷል፡፡

በዚህ የቆየ የግንኙነት ሒደት ውስጥ አሁን ከሚታየው በመንግሥታት መካከል ከመደበኛው የዲፕሎማሲ ግንኙነት ባለፈ የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነቱን ለማጠንከር በሁለቱ አገሮች በሚገኙ ወጣቶች፣ ምሁራን፣ የንግዱ ማኅበረሰብ እንዲሁም በዩኒቨርሲቲዎች መካከል የተቀራረበ ግንኙነት መፈጠር እንዳለበት በኢትዮጵያ የኢንዶኔዥያ አምባሳደር አልቡስራ ባስኑር በነበረው የመጽሐፉ ምረቃ ፕሮግራም ባደረጉት ንግግር አስታውቀዋል፡፡

አምባሳደሩ አያይዘውም ምሁራኑ መጽሐፉን እንዲጻፍ ካነሳሳቸው ምክንያት አንዱ፣ የዚህን ዘመን ዘርፈ ብዙ ችግር ለመፍታት በተለይም ወጣቶች የመፍትሔ ዕይታቸውን በችግሩ ግዝፈት ልክ ማየት የሚችሉበት አስተሳሰብ እንዲገነቡና ራሳቸውን ብቁ እንዲያደርጉ በሚል እሳቤ ነው ብለዋል፡፡

በኢንዶኔዥያ ኤምባሲና ሐራምቤ ዩኒቨርሲቲ ትብብር የተዘጋጀው መጽሐፉ ዓለም በፍጥነት እየተቀያየረች አዳዲስ ነገሮች እየተከሰቱ በመጡበት የ21ኛው ክፍለ ዘመን ለጊዜው የሚመጥን አስተሳሰብን ማፍለቅና መተገበር ላይ ያተኮረ ሲሆን፣ በዚህ የሚለዋወጥ ዓለም ውስጥ የግለሰቦችም ይሁን የድርጅቶች እንቅስቃሴና ምልከታ ጥንቃቄ የተሞላበትና ጥራት ያለው መሆን እንዳለበት ተገልጿል፡፡

ከሁለቱ የኢንዶኔዥያ ተባባሪ ጸሐፊዎች አንዱ የሆነው ታውፋን ቴጉህ (ዶ/ር) ‹‹በዓለማችን የሚታዩ ስፍር ቁጥር የሌላቸው ችግሮችን ለመፍታት በዕውቀት ላይ የተመሠረተ የወጣቶች ፈጠራ፣ ጊዜውን የሚመጥንና ጥራት ያለው አስተሳሰብ ያስፈልጋል፤›› ብለዋል፡፡

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ መምህርና የመጽሐፉ ተባባሪ ጸሐፊ ተሻለ ብርሃኑ (ዶ/ር) በበኩላቸው፣ መጽሐፉ ራስን በአስተሳሰብና በአመለካከት የተሻለ ለማድረግ፣ ምክንያታዊና ጠያቂ በመሆን ጥንቃቄ የተሞላበት አስተሳሰብ ማለት ምን ማለት ነው የሚለውን ለመረዳት እንደሚያግዝ አስረድተዋል፡፡ አክለውም ጥራት ያለው አስተሳሰብ፣ በመረጃ የተደገፈና ጥናትን የተመረኮዘ መፍትሔን የችግሮች መፍቻ ቁልፍ አድርጎ ለመጠቀም እንደሚረዳ ተናግረዋል፡፡

የመጽሐፍ ተባባሪ አዘጋጅ የሆነው የሐራምቤ ዩኒቨርሲቲ ባለቤትና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ፈይሳ አራርሳ በፕሮግራሙ ላይ ባደረጉት ንግግር፣ የስኬቶች ሁሉ ምንጭ ጥራት ያለው ዕሳቤ መሆኑን አንስተው፣ በተቋማት ደረጃም ሆነ በግለሰቦች ዘንድ ጥራት ያለው አመለካከት ምርጫ ሳይሆን የግዴታ ጉዳይ በመሆኑ ወጣቱ ትውልድ የሚከሰቱ ችግሮችን የሚፈታበት መንገድ ሊዘይድ ይገባል ብለዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የአዛርባጃንን ብሄራዊ ቀን በአዲስ አበባ በድምቀት ተከበረ

የአዛርባጃን ኤምባሲ  የአዛርባጃንን ብሄራዊ ቀን በትላንትናው ዕለት አከበረ። ሰኞ...

የመንግሥትና የሃይማኖት ልዩነት መርህ በኢትዮጵያ

እንደ ኢትዮጵያ ባሉ አገሮች የሃይማኖት ተቋማት አዎንታዊ ሚና የጎላ...

ሐበሻ ቢራ ባለፈው በጀት ዓመት 310 ሚሊዮን ብር የተጣራ ትርፍ ማግኘቱን አስታወቀ

የአንድ አክሲዮን ሽያጭ ዋጋ 2,900 ብር እንዲሆን ተወስኗል የሐበሻ ቢራ...