አንበሳ ምድማዱ ላይ እንደተኛ በረሃብ ይሞታል እንጂ የውሻን ትራፊ አይበላም፡፡ በረሃብ ቸነፈርንና ችግርን ቻል፡፡ ከርካሽ ሰው ዕርዳታ በመጠየቅ ክብርህን በፍጹም በገዛ ራስህ አትጣ፡፡ መልካም ሥነ ምግባር የሌለውን ሰው እርሳው፤ እንዲሁም ዋጋ ቢስነቱን ዕወቅ፡፡ ወደ ልመና የሚያደላ ሰው በሕይወት እስካለ ድረስ ምን ጊዜም ለማኝ ነው፡፡ በቃኝ ባይ አዕምሮ ያለው ሰው ሁልጊዜ የተከበረ ነውና ስግብግብ አትሁን፡፡ የጉልበትህ ውጤት የሆነ ሆምጣጤና ጎመን ከባለሥልጣን እንጀራና ዝግን በእጅጉ ይበልጣል፡፡ በራስ መተማመን በሌለበት ቦታ አክብሮት የለም፡፡ አክብሮት በሌለበት ቦታም በራስ መተማመን ሊኖር አይችልም፡፡ (ሄንሪ ጊልስ)
- ባይለየኝ ጣሰው ‹‹የሶኖዲ ጥበቦች›› (2004)