Sunday, June 4, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
እኔ የምለዉቀዳሚው ሕዝብ ወይስ መንግሥት?

ቀዳሚው ሕዝብ ወይስ መንግሥት?

ቀን:

በአሰፋ አደፍርስ                     

ከፍጥረት መጀመሪያ እንኳ ብንመለከትና የሰውን የተፈጥሮ ታሪክ ብንከታተል የሁሉ ቀደምት የሆነው ፈጣሪያችን መጀመሪያ አዳምን፣ ቀጥሎ ሔዋንን ከግራ ጎኑ አውጥቶ እኛን አበራከተን ሲሉ ነው እስከ ዛሬ የሰማነው፣ ሰምተንም ያመንነው። ሕዝብ እየበዛ ሲመጣ አስተዳዳሪ እረኛም መኖር ስለሚገባው፣ ሰዎች መሪን በድምፃቸው መምረጥ አለባቸው፡፡ ሁሉም እንዳሻው ከሚተራመስ ይልቅ መመርያ የሚሰጥ እንዲኖር በመወሰን መሪና ተመሪ ተብሎ ተጀመረ። ያ ሁኔታ እየላቀ መጥቶ አሁን ያለንበት ደረጃ ላይ ደርሶ እየተሳሰቡ በቤተሰብ ዓይነት መቀጠሉ ተረስቶ መሪዎች አዋቂዎች፣ ተመሪዎች ደግሞ እንደ አላዋቂ የሚቆጠሩበት ሁኔታ ተፈጠረ፡፡ በተለይ ሦስተኛ ዓለም በሚባሉት አገሮች ሥር እየሰደደ በመጠናከሩ፣ የቀድሞው ሁኔታ ተለውጦ ጌታና ሎሌ የሚያስመስል የመጀመሪያ መሠረቱ ከተጣለ በርካታ መቶ ዓመታትን አስቆጥሯል።

በምዕራባዊያን በኩል ነባሩን አሠራር ከመከተል ይልቅ ለውጥ እናምጣ ብለው፣ ለለውጥ ከተዘጋጁ ወደ አንድ መቶ ዓመታት ሊያስቆጥር ነው። ግን ሦስተኛው ዓለም በሚባሉት ለውጥ ሳይኖር ብዙ ዘመናትን አስቆጥሮ ለውጥ ቢመጣም፣ በተለያዩ ምክንያቶች ወደኋላ ነው ሲንሸራተት የኖረው፡፡ እ.ኤ.አ. በ1916 ገደማ ምዕራባዊያን ሠልጥነው ስለእኩልነት ሲያወሩ፣ አገራችንም ያንን ፈር ለመከተል ቃል ገብታ እንደተባለውም ከነበረው ሁኔታ መለወጥን አሳይታለች። ምዕራባውያን ከመሪዎቹ ይልቅ አማካሪዎቻቸው የበለጠ ሚናውን የመጫወት፣ የመምከርና መስመር የማስያዝ አቅም ሲኖራቸው፣ በሦስተኛው ዓለም ግን ሁሉን ወሳኝ መሪ ነው፡፡ አማካሪዎች ግን ለስምና ለጥቅማቸው ማስከበሪያ የተሰየሙ በመሆናቸው ይህ ለምን ሆነ፣ ይህ ከሆነ አያዋጣም፣ አያዛልቀንም የሚል ቁርጠኝነት ስለሚጎድላቸው አቤት ባይ እንጂ ለሙያቸው ክብር፣ ለአገራቸው ኩራት ያልቆሙና የተሰጣቸውን ብቻ የሚከተሉ በመሆናቸው ሥራቸውንም የሚያውቁ አይመስሉም። እንዲያው መኮፈስና ታላቅ ሰዎች ነን ለማለት የተሰባሰቡ ሆነው የወር ደመወዝን ብቻ በማሰላሰል የኑሮዋቸውን ሁኔታ ለማሻሻል የተሰባሰቡ ሳያሰኛቸው አልቀረም። በምዕራባዊያን በኩል ግን አግኝቶ ራሱን ከቻለ በኋላ የዕውቀት ደረጃውን በአገልግሎት ተወዳድሮ አሸነፎ ለማሳየት ይሞክራል እንጂ፣ ለራሱና ለቅርብ ወዳጅ ዘመድ መሸጋገሪያ መንገድ አያደርገውም፡፡ ቢያደርግም ወደ መከራ አዘቅት መግቢያው ነው የሚሆነው።                                                                   

የሚገርመው ነገር ኢትዮጵያ ቀደምትና የአስተዳደርን ሥርዓት፣ ዳኝነትንና የኑሮን ደረጃ ከጌታ ልደት በፊት ጀምራ ያወቀችና ለማያውቁት ማስተማር የጀመረች አገር ነበረች፡፡ ዘመናዊ ነን ባዮች ኢትዮጵያን ከእንግሊዝ፣ ከፈረንሣይና ከሌሎች ምዕራባዊያን እንዴት ብትደፍር ነው የምታስተካክላት የሚሉኝ፣ ራሳቸውን ጠንቅቀው ሳያውቁ ወደ ምዕራብ የነጎዱ ያገሬ ልጆች ደፍረው ና እንከራከርና እንርታህ፣ ወይም እርታን ከማለት ይልቅ በተለመደው የአሉባልታ ሥልታቸው ጊዜያቸውን ሊያጠፉ ይሞክሩ ይሆናል። እኔ ግን ላስረዳቸው ዝግጁ ነኝና ይሞክሩኝ።                                                                           

የዛሬዋን ዓለም ልምራ ብላ ግራ የተጋባችው አሜሪካ እ.ኤ.አ. አፕሪል 30 ቀን 1789 ድረስ መሪ ያልነበራት ነበረች፡፡ እንግሊዝ የጦር ኃይል የሠፈረባትና የአገሬውን ነባር ሕዝብ አስለቅቃ ራሷን ያቋቋመች አገር ናት፡፡ በወቅቱ አሜሪካኖች ያንን ያህል ሰፊ አገር ከያዝንና ራሳችንን ከሾምን የአቅራቢያ ወገኖቻችንን ብቻ ሳይሆን፣ ከተለያዩ አካባቢዎች የመጣው ወታደርና ሲቪል ስላለ፣ እንዲሁም የእንግሊዝ አገዛዝ የሰለቸን ነንና ልዩ በሆነ አሠራር አዲሷን አገራችንን በልማት፣ በኢንዱስትሪና በቴክኖሎጂ ወደፊት ገፍተን ከዓለም ቀደምት እንሁን ብለው ነበር የተሳሱት።

የተሰባሰቡትም ነጮች ይሁኑ እንጂ የፈረንሣይ፣ የአይሪሽ፣ የስኮቲሽ፣ የዌልስ፣ የሆላድንድ (ኔዘርላንድና) እና የመሳሰሉት በሙሉ የዝርያቸው ቋንቋ የነበራቸው ነበሩ፡፡ ነገር ግን ለአንድ አገር፣ ለአንድ ዓላማና ግብ በመነሳታቸው ከላይ እንደጠቀስኩት ለልማትና ለኢንዱስትሪ መስፋፋት ሲዋትቱ፣ መቼም ስንዴ ውስጥ እንክርዳድ አይጠፋምና አንዱ ኃይል መለያየትን ሲሻ ሌሎቹ ደግሞ ለአንድነት ሲኳትኑ ለአንድነት የተሠለፉት ተሳካላቸው፡፡ አሜሪካን አንድ አድርገው በመጨረሻም የሰው ልጅ እኩል ነው በሚለው ፍልስፍና ወድደውም ሆነ በግድ የባሪያን ሽያጭ አስቆሙ፡፡ አሜሪካን ቀደምት የዓለም መሪ ለማድረግ ሞክረዋል፣ ነንም ብለዋል፣ ቢሉም ይገባቸዋል፡፡

ለሁሉም እኩል አገር በምትባለው አሜሪካ ሠርተውና በልፅገው፣ በማንነታቸው ቁም ሂድ ሳይባሉ የሚኖሩበት እንዲናገሩ ዕድሉን ልስጣቸው። የሰው ልጅ ምርጫው የራሱ ነው፡፡ ክብሬን ጠብቄ ልኑር ካለ እንደ አቅሙና አንደ ችሎታው ሕግን አክብሮ እስካለ ድረስ ማንም ሳይነካው ይኖራል። ይህ በሦስተኛው ዓለም የማይታሰብና ሁሌም በሥጋትና ምን ሊመጣብኝ ይሆን በሚል ሞትኩና አለሁ ብሎ የመኖሩን ሁኔታ እንኳ ሳያረጋግጥ የሚኖርበት ሁኔታ ነው።

አፍሪካ የሀብታም ልጆች ተኩራርተው፣ ተምረውና ተንደላቀው የሚኖሩበት አኅጉር ሲሆን፣ የደሃው ልጅ የዕለት ጉርሱን ለምኖ ከኖረም ይኖራል፡፡ ረሃቡና ጠኔው አንፈራፍሮት የሚሞተውም ብዙ ነው። መኖሪያ ቤት ይቅርበትና የሚተኛበት የጎዳና ዳርቻውም በቅጡ ሳያስተናግደው፣ እዚያችው አፈር ላይ እንደተንገላታ ይሞትና እንደ ውሻ ሬሳ ይጣል ይሆናል። የተጣለውን በዓይኔ ስላላየሁ በእርገጥኝነት ልናገር አልችልም፡፡ ግን የሚበላውን አጥቶ ሲራወጥና ሲለምን የመፀወትኩት ብዙ ነውና ያንን ዓይቻለሁ። ምፅዋት ደግሞ የደቂቃ እረፍት ይሰጠው ይሆናል እንጂ፣ ዘለቄታ እንደሌለው የምናውቀው ይመስለኛል። ዘላቂ መፍትሔ የመፈለግ ግዴታ አለብንና እናስብበት።

እስራኤል በ1948 ዓ.ም. እ.ኤ.አ. ነፃነቷን ስትጎናፀፍ ይህንን ነው የተነጋገሩት፡፡ አሁን ነፃነታችንን ካገኘን ንብረት የግል ብለን ለንብረት ከመሽቀዳደም ይልቅ፣ አንዱ ትንሽ አንዱ ትልቅ ሳንባባል ወገናችንን በአንድነት መርዳትና አገራችንን ራስ ማስቻል ነው፡፡ ይህንን ያላደረገ እስራኤላዊ ሊሆን አይችልም ብለው በተነጋገሩት የመግባቢያ ሐሳብ በመስማማት ትንሿና ደረቋን አገራቸውን እንዳበለፀጉ አገር አስመስለው አፈር ከሌላ አገር በማስመጣት፣ የሌላውን ወራጅ ውኃ መስመሩን በማስለወጥ ከራሳቸው ተርፈው ሌላውንም እንረዳለን አሉ፡፡

በርካታ የተፈጥሮ ሀብቶችና ወራጅ ወንዞች የሞሏት አፍሪካ  በትምህርት የላቁ፣ የተማሩ መስለው የሚንቀባረሩ ምሁራን የሞሏት አፍሪካ ሁሌ ለማኝ ሆና እርስ በርሷ ስትፋጅና ስትሻኮት ማየቱ በጣም ያስቆጫል፣ ያናድዳል፣ ያሳፍራልም፡፡                                                                                               አፍሪካውያን ወገኖቼ ሁሉ ሞልቶ ተርፎ ሌላውን ለመርዳት እየቻላችሁ እንዴት ነው ችግረኛና ተመፅዋች የሆናችሁት? የተፈጥሮ ሀብታችሁን እነኛ ጮሌዎች ወስደው መልኩን ቀይረው ሲልኩላችሁ ተቀብላችሁ ከሰማይ እንደ መጣ ተዓምር ተደንቃችሁ ሌላውንም ስታስደንቁ መታየቱ አይገርምም? መላውን ዓለም ማስተናገድ የምትችል አፍሪካ ተመፅዋች ስትሆን ማየቱ አይከብድም? አይ መማር ይህ ከሆነ ምሁርነት ምን ይረባ ይሆን? ወገን እየተሰቃየ የጥቂቶች ተደስተው መንቀባረር ካላሳፈረ ምን ያሳፍር ይሆን?

የሦስተኛን ዓለም ልማትና የዓለም መንግሥታትን የአለኝታነቸውን ሁኔታ በወፍ በረር ላመላክትና ለትዝብት ያህል እንወያይበት ብዬ ነው። መቼም የዓለም መንግሥታት ድርጅት ሲባል ለአባላቱ ሁሉ እኩል አልፎ ተርፎም ለሰው ልጆች የተፈጥሮ ነፃነት የቆሙ መሆናቸው ይነገር ይሆናል። እኔ ግን ለየት ያለ አስተያየት ነው ያለኝ።                                                                                                                                 ጊዜው እ.ኤ.አ 1960 ነበር።

“Brussels and the other Western powers, operating under cover of the United Nations, were determined to overthrow Lumumba’s nationalist government and install a neo-colonial regime, thereby putting the country at the mercy of the trusts and holding companies which had controlled it for decades. The West soon obtained its first success. In September 1960, the Congolese government and parliament which supported Lumumba were swept aside by colonel Joseph Desire Mobutu. The war against the Congolese nationalist came provisory to a head when, on 17 January 1961 LUMUMBA and two of his closest associates were assassinated in Katanga which was then being propped up by Belgian military and government personnel. Gus what, who engineered intervention in the Congo from the outset: the Eyskens government and senior United Nations officials headed by Dag Hammarskjold. We think all members of UN can be served as member equally with all other members, but as you can see the fact written by LUDO DE WITT in his book entitled.” THE ASSASSINATION OF LUMUMBA

አፍሪካን ወገኖቼ አዙሮ ማየት አቅቶን ሊሸጡን፣ የዘለዓለም ባሪያ ሊያደርጉን አጥንተው በተነሳሱት ወዳጅ መሳይ ጠላቶቻችን እግር ሥር ከመውደቅ ለመዳን እንተባበር እንጂ አንለያይ፣ አይጠቅመንም፡፡ የእነሱ ሲሳይ ለመሆን ካልሆነ በስተቀር። በእርግጥ በግል በገንዘብ ልንበለፅግ እንችል ይሆናል። ነገር ግን ከሚያዋርደን በስተቀር ትርፍ የለውማና እንሳበበት። ሁሌም እነዚያው ያሽሞነሞኑንና አስመስለው ያታለሉን የዘለዓለም መዛበቻ አያድርጉን፡፡ በገንዘብ ማታለላቸው ብቻ ሳይሆን መላው የአገሬው ሕዝብ በዚያ በድጎማቸው እንደሚገዛ ሲዛበቱ፣ ታሪክን የልጅ ልጆች ማፈሪያ ማድረግ እንዳይሆን አደራ፡፡ ግለሰቦች ከጊዜያዊ ጥቅማቸው ይልቅ መጪውን ታሪካቸውን ተገንዝበው የጥቅምን ሩጫ በመተው ለጋራ እንዲያስቡ ምክሬን ለመለገስ ወደድኩኝ።

ከአዘጋጁ፡- ጸሐፊው ግለ ሕይወታቸውንና የጉዞ ታሪካቸውን የከተቡበት ‹‹ከባቹማ እስከ ቨርጂኒያ›› በሚል ርዕስ ለአንባብያን ያቀረቡት መጽሐፍ ደራሲ ሲሆኑ፣ ጽሑፉ የእሳቸውን አመለካከት ብቻ የሚያንፀባርቅ መሆኑን እየገለጽን በኢሜይል አድራሻቸው assefadefris@gmail.com ማግኘት ይቻላል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

አወዛጋቢው የሕገ መንግሥት ማሻሻያ ጉዳይ

በኢትዮጵያ የሕገ መንግሥት ማሻሻል ጉዳይ ከፍተኛ የፖለቲካ ውዝግብ የሚቀሰቀስበት...

 መፍትሔ  ያላዘለው  የጎዳና  መደብሮችን  ማፍረስ

በአበበ ፍቅር ያለፉት ስድስት ዓመታት በርካቶች በግጭቶችና በመፈናቀሎች በከፍተኛ ሁኔታ...

የተናደው ከቀደምቱ አንዱ የነበረው የአዲስ አበባ ታሪካዊ ሕንፃ

ዳግማዊ አፄ ምኒልክ በ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ መናገሻ ከተማቸውን...

የአከርካሪ አጥንት ሕክምናን ከፍ ያደረገው ‘ካይሮፕራክቲክ’

በአፍሪካ ከጀርባ ሕመም ጋር በተያያዘ በርካታ ሰዎች ለከፍተኛ የአካል...