Friday, June 2, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናብርሃን ባንክ ለዋና መሥሪያቤቱ ህንጻ ያሸነፈውን ዲዛይን ይፋ አደረገ

ብርሃን ባንክ ለዋና መሥሪያቤቱ ህንጻ ያሸነፈውን ዲዛይን ይፋ አደረገ

ቀን:

 ብርሃን ባንክ ለዋና መሥሪያቤቱ ህንፃ ግንባታ ዲዛይን ለማሠራት ባወጣው ዓለም አቀፍ ጨረታ አሸናፊ ሆኖ የተመሰጠውን ዲዛይን ይፋ አደረገ። ባንኩ ባወጣው ዓለም አቀፍ ጨረታ ላይ 16 ኩባንያዎች የተሳተፉ ሲሆን ተሳታፊዎቹ ካቀረቧቸው ዲዛይኖች መካከል አሸናፊ የሆነው ዲዛይን ግንቦት 2 ቀን 2015 ዓ.ም. ምሽት በተካሄደ ፕሮግራም ላይ ይፋ ተደርጓል።

በዚህም መሠረት ባንኩ በሰንጋ ተራ አካባቢ በተረከበው 5400 ካሬ ሜትር መሬት ላይ ለሚያስገነባው ህንፃ MAE ኮንሰልቲንግ ኤንድ ኢንጂነርስ በተባለው ድርጅት የቀረበው ዲዛይን አሸናፊ ሆኖ ተመርጧል። በተመረጠው ዲዛይን መሠረት የሚገነባው የባንኩ ዋና መሥሪያቤት ህንፃ ከ 51 በላይ ወለሎች እንደሚኖሩት ታውቋል። በዴጃው ኮንሰልቲንግ የተሰራው የህንፃ ዲዛይን ሁለተኛ ደረጃ አሸናፊ ሲሆን ፣ በአዲስ መብራቱ ኮንሰልቲንግ ኤንድ ኢንጂነርስ የቀረበው ዲዛይን ደግሞ ሦስተኛ ወጥቷል።

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የአዛርባጃንን ብሄራዊ ቀን በአዲስ አበባ በድምቀት ተከበረ

የአዛርባጃን ኤምባሲ  የአዛርባጃንን ብሄራዊ ቀን በትላንትናው ዕለት አከበረ። ሰኞ...

የመንግሥትና የሃይማኖት ልዩነት መርህ በኢትዮጵያ

እንደ ኢትዮጵያ ባሉ አገሮች የሃይማኖት ተቋማት አዎንታዊ ሚና የጎላ...

ሐበሻ ቢራ ባለፈው በጀት ዓመት 310 ሚሊዮን ብር የተጣራ ትርፍ ማግኘቱን አስታወቀ

የአንድ አክሲዮን ሽያጭ ዋጋ 2,900 ብር እንዲሆን ተወስኗል የሐበሻ ቢራ...