Sunday, June 4, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊጠቅላይ ሚኒስትሩ የኢሠማኮ አመራሮችን እንዲያነጋግሩ ጥያቄ ቀረበላቸው

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኢሠማኮ አመራሮችን እንዲያነጋግሩ ጥያቄ ቀረበላቸው

ቀን:

  • የሠራተኞች የደመወዝ መነሻ መጠን ከፍ እንዲልና የሚቆረጠው ግብር ዝቅ እንዲልም ጠይቋል

የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን ኢሠማኮ አንገብጋቢ ባሏቸው የሠራተኞች ጥያቄዎች ላይ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) የኮንፌዴሬሽኑን አመራሮች እንዲያነጋግሩ ጥያቄ አቀረበ፡፡

 ኮንፌዴሬሽኑ በዘንድሮው የሜይ ዴይ በዓል ላይ በአደባባይ ሊያነሳቸው የነበሩ ጥቄያዎችን በማካተት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ በጻፈው ደብዳቤ፣ እሳቸውን ማነጋገር ለሠራተኞች ጥያቄዎች ምላሽ ለማግኘት እንደሚረዳ አስታውቋል፡፡

በየጊዜው እያሻቀበ በመጣው የኑሮ ውድነት፣ የኢትዮጵያ ሠራተኞችና ቤተሰቦቻቸው መኖር የማይችሉበት ሁኔታ ውስጥ መሆናቸውን በደብዳቤው የጠቀሰው ኢሠማኮ፣ ‹‹ጠቅላይ ሚኒስትሩን ማግኘት ግድና ብቸኛው አማራጭ ሆኖ አግኝቼዋለሁ›› ብላል፡፡

ኢሠማኮ የሠራተኞች አንገብጋቢ የሚባሉ ጥያቄዎችን አስመልክቶ ከዚህ ቀደም በተለያዩ መንገዶች ለሚመለከታቸው መንግሥታዊ አካላት ጥያቄ ቢያቀርብም፣ ምላሽ ሊያገኝ አለመቻሉንም በደብዳቤው ጠቅሷል፡፡

ከዚህ ቀደም የሠራተኞች ጥያቄ የቀረበላቸው መንግሥታዊ አካላት ጥያቄውን ወደ ጎን የመግፋት አዝማሚያ እያሳዩ በመምጣታቸው፣ የኢሠማኮ አመራር ‹‹ጠቅላይ ሚኒስትሩ የአነጋግሩን›› ጥያቄ ለማቅረብ መገደዱን በደብዳቤው አስረድቷል፡፡   

ከዚህ ቀደም ተመሳሳይ ጥያቄዎች ለጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዲደርሱለት አቅርቦ እንደነበር የሚያመለክተው የኢሠማኮ ደብዳቤ፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥያቄዎቹ እንዲደርሳቸው ቢደረግ ኖሮ ያነጋግሩት ነበር›› የሚል እምነት እንዳለው ያብራራል፡፡  የዋጋ ንረት እያስከተላቸው ባሉ ጫናዎች፣ እንዲሁም በሌሎችም አንገብጋቢ ባላቸው የሠራተኞች ጥያቄዎች ላይ፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ውድ ከሆነ ጊዜያቸው ሰውተው አመራሮቹን እንዲያነጋግሯቸው የሚፈልግ መሆኑንም አስታውቋል፡፡

ኢሠማኮ የዘንድሮውን የሜይ ዴይ በዓል በአደባባይ ለማክበር የገጠመውን ችግር በተመለከተ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ በጻፈው ደብዳቤ፣ ‹‹ሜይ ዴይን ትግራይና አማራ ክልሎች የሚገኙ ሠራተኞችን ሳያካትት በአዲስ አበባ፣ በአዳማ፣ በጅማ በሐዋሳና በድሬዳዋ ቅርጫፎቻችን የሚገኙ ሠራተኞች በሰላማዊ ሠልፍ ጥያቄአችንን ለመንግሥት ለማቅረብ ቅድመ ዝግጅት አድርገን ስለተከለከልን፣ ሕገ መንግሥታዊ የመሰብሰብና ሐሳብን የመግለጽ መብቶቻችንን ተነፍገናል፤›› ብሏል፡፡ 

ወቅታዊ አንገብጋቢ ተብለው ከተያዙ ጥያቄዎች መካከል በኑሮ ውድነት ሳቢያ በሠራተኞች ላይ እየተፈጠረ ያለው ጫና አንዱ ነው፡፡ ከሠራተኞች የመደራጀት መብት ጋር በተያያዘ ያለው ችግርም የጥያቄው አካል ነው፡፡ በተለይ ከኑሮ ውድነት ጋር በተያያዘ መደረግ ይገባዋል ያለውን የመፍትሔ ሐሳብ፣ እንዲሁም መንግሥት ማስተካከል አለበት ተብሎ የሚያምንባቸውን ጥያቄዎች ለገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴም በጻፈው ደብዳቤ ላይ በዝርዝር ገልጿል፡፡

ከኑሮ ውድነት ጋር በተያያዘ ሠራተኛው እየገጠመው ያለውን ችግር ለመፍታት ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል እንዲስተካከል የሚለውን የመፍትሔ ሐሳብ አጽንኦት የሚሰጠው የኢሠማኮ ደብዳቤ፣ ታክስ የማይከፈልበት የሠራተኞች ደመወዝ መጠን አሁን ካለበት 600 ብር ከፍ እንዲል፣ በየደረጃው ካለ ደመወዝ ላይ የሚቆረጠው ግብር እንዲቀንስም ጠይቋል፡፡ ከዚህም ሌላ በአነስተኛ የምግብ ፍጆታዎች ላይ የተጣለው የተጨማሪ እሴት ታክስ እንዲነሳና ሌሎች ተያያዥ ጥያቄዎችን ሰኞ ሚያዝያ 30 ቀን 2015 ዓ.ም. ለገንዘብ ሚኒስትሩ በጻፈው ደብዳቤ አሳስቧል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

አወዛጋቢው የሕገ መንግሥት ማሻሻያ ጉዳይ

በኢትዮጵያ የሕገ መንግሥት ማሻሻል ጉዳይ ከፍተኛ የፖለቲካ ውዝግብ የሚቀሰቀስበት...

 መፍትሔ  ያላዘለው  የጎዳና  መደብሮችን  ማፍረስ

በአበበ ፍቅር ያለፉት ስድስት ዓመታት በርካቶች በግጭቶችና በመፈናቀሎች በከፍተኛ ሁኔታ...

የተናደው ከቀደምቱ አንዱ የነበረው የአዲስ አበባ ታሪካዊ ሕንፃ

ዳግማዊ አፄ ምኒልክ በ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ መናገሻ ከተማቸውን...

የአከርካሪ አጥንት ሕክምናን ከፍ ያደረገው ‘ካይሮፕራክቲክ’

በአፍሪካ ከጀርባ ሕመም ጋር በተያያዘ በርካታ ሰዎች ለከፍተኛ የአካል...