Sunday, June 4, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዝንቅበኢትዮጵያ ላይ የደረሰው ጹናሚ

በኢትዮጵያ ላይ የደረሰው ጹናሚ

ቀን:

አብዮቱ ሲጀምር የሚሆን የሚሆን የመሰለኝ መሆኑ ቀርቶ በኢትዮጵያ ላይ የደረሰ ጹናሚ ሆነ፡፡ ጹናሚ ሲመጣ፣ ሊያድኑት የሚችሉትን ያህል ይዞ እግሬ አውጪኝ መሮጥ እንጂ፣ እኔን ያልፈኛል ማለት ወይም በሰፌድ ለመመከት መሞከር የጹናሚን ጠባይና ኃይል አለማወቅ ነው፡፡ የንጉሠ ነገሥቱ አገዛዝ ብዙ መሻሻል እንደሚያስፈልገው ማንም አይክድም፡፡ ግን ጹናሚ መሬት ጭነቷ ከብዷት እንደሆን ጭነቷን ይቀንስላት ይሆናል እንጂ፣ የንጉሠ ነገሥቱን አገዛዝ ማሻሻያ አይሆንም፡፡

ጹናሚ የሚሻሻለውን ከማይሻሻለው ስለማይለይ፣ ሁሉንም ደፈቀው፡፡ ወታደሮቹና ተማሪዎቹ የሌለው ባለው ላይ እንዲዘምትበት አስተካክለው ሰጡት፡፡ መኪና ያለው፣ እኔ መኪና ሳይኖረኝ አንተ ለምን መኪና? ይኖርሃል ተባለ፡፡ ቤት ያለው፣ እኔ ቤት ሳይኖረኝ አንተ ለምን ቤት ይኖርሃል? ተባለ፡፡ ርስት ያለው፣ እኔ ርስት ሳይኖረኝ አንተ ለምን ይኖርሃል? ተባለ፡፡ የዩኒቨርሲቲ ዲግሪ ያለው፣ እኔ ዲግሪ ሳይኖረኝ አንተ ለምን ይኖርሃል? ተባለ፡፡ ቋንቋው የአስተዳደር ቋንቋ ያልሆነው የሆነውን ለምን እንዲህ ይሆናል? አለ፡፡

 ዓላማው የሌለውም እንዳለው ይኑረው መሆን ሲገባው፣ ያለውም እንደሌለው አይኑረው ወደ ማለት ተለወጠ፡፡ ደኻው ያግኝ ማለት ቀርቶ ያልደኸየው ይደኽይ ሆነ፡፡
ሳይታሰብ ተጠራቅመው የጹናሚ ኃይል የሆኑት እነዚህ “ለምኖች” ቢዘረዝሩ ንጉሡ በይበልጥ ባቀረቧቸው ባለሥልጣኖች ላይ የተነሡ ሌሎች ባለሥልጣኖች፣ የትምህርት ዕድል ያላገኙ ወጣቶች፣ ተምረው ሲጨርሱ ሥራ የማግኘት ዕድል የማይታያቸው ተማሪዎች፣ ለሀገር የተሻለ ሕይወት የሚፈልጉ ሀገርና ወገን ወዳዶች፣ የሀገር ገንጣይ ቡድኖች፣ መንግሥቱን የያዙት አማሮች ናቸው ባዮች፣ መንግሥቱን የያዙት የሸዋ አማሮች ናቸው ባዮች፣ መንግሥቱን የያዙት ክርስቲያኖች ናቸው ባዮች፣ ርስት የሌላቸው ጪሰኞች፣ ጄኔራል ያልሆኑ ወታደሮች፣ “የኮንጎ ዘመቻ አበላችን ይሰጠን” የሚሉ ወታደሮች፣ የከተማ ቦታ ፈላጊዎች፣ የቀን ሠራተኞች፣ ዩኒቨርሲቲ መግባት ሲያቅታቸው ወታደርና ፖሊስ የሆኑ ወጣቶች፣ ወዘተ. ናቸው፡፡

የግል ቂም ያለውም አብዮቱን ተጠግቶ ቂሙን ተወጣ፡፡ አብዮቱን አራማጆች ድጋፍ ያገኙ መስሏቸው የነዚህን ሁሉ ፍላጎት አጋሉት፤ ሊያቀዘቅዙት ግን እንደማይችሉ አልታያቸውም፡፡ በዚያ ጊዜ የታያቸው ድጋፍ ማግኘታቸውን እንጂ፣ የየቡድኑ ጥያቄ እንዴት እንደሚመለስ አላሰቡበትም፡፡

… በሀገራችን የሰፈነው የፍትሕ መጓደል መታረም የሚገባው መሆኑ ባይካድም፣ አብዮቱን ያቅለበልቡት የነበሩ ዋና ኃይሎች ምቀኝነትና ቅናት መሆናቸው ለማንም ገለልተኛ አስተዋይ ድብቅ አልነበረም፤…

  • ጌታቸው ኃይሌ ‹‹አንዳፍታ ላውጋችሁ፤ በግል ሕይወቴ ከደረሰውና ካጋጠመኝ›› (2006)
spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

አወዛጋቢው የሕገ መንግሥት ማሻሻያ ጉዳይ

በኢትዮጵያ የሕገ መንግሥት ማሻሻል ጉዳይ ከፍተኛ የፖለቲካ ውዝግብ የሚቀሰቀስበት...

 መፍትሔ  ያላዘለው  የጎዳና  መደብሮችን  ማፍረስ

በአበበ ፍቅር ያለፉት ስድስት ዓመታት በርካቶች በግጭቶችና በመፈናቀሎች በከፍተኛ ሁኔታ...

የተናደው ከቀደምቱ አንዱ የነበረው የአዲስ አበባ ታሪካዊ ሕንፃ

ዳግማዊ አፄ ምኒልክ በ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ መናገሻ ከተማቸውን...

የአከርካሪ አጥንት ሕክምናን ከፍ ያደረገው ‘ካይሮፕራክቲክ’

በአፍሪካ ከጀርባ ሕመም ጋር በተያያዘ በርካታ ሰዎች ለከፍተኛ የአካል...