Monday, December 11, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትትኩረት የተነፈገው እጅ ኳስና አኅጉራዊ ተሳትፎው

ትኩረት የተነፈገው እጅ ኳስና አኅጉራዊ ተሳትፎው

ቀን:

  • ብሔራዊ ቡድኑ በታንዛንያ ሁለተኛ ደረጃ ይዞ አጠናቋል

በኢትዮጵያ የስፖርት ማኅበራት ማደራጃና መተዳደሪያ ደንብ መሠረት የተቋቋሙ ከ33 በላይ ፌዴሬሽኖች እንዳሉ ይነገራል፡፡ ከእነዚህም መካከል ከአትሌቲክስና ከእግር ኳስ ፌዴሬሽን በስተቀር ሌሎቹ በአኅጉር አቀፍ ውድድሮች ያላቸው ተሳትፎ ውስን ነው፡፡

በአንፃሩ ኢትዮጵያ በምትወከልበት አኅጉራዊ ውድድሮች ንቁ ተሳትፎ ከሚያደርጉት የእግር ኳስና አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ቀጥሎ የኢትዮጵያ እጅ ኳስ ይጠቀሳል፡፡

የኢትዮጵያ እጅ ኳስ ፌዴሬሽን በአኅጉር አቀፍ ውድድሮች ንቁ ተሳትፎ በማድረግ ኢትዮጵያ ያላትን ውክልና በአግባቡ የሚጠቀም ፌዴሬሽን እንደሆነ ይነገርለታል፡፡

ፌዴሬሽኑ የኢትዮጵያ እጅ ኳስ ብሔራዊ ቡድን በሁለቱም ፆታ እንዲሁም በተለያዩ የዕድሜ ዕርከኖች በሚደረጉት ውድድሮች ንቁ ተሳትፎ ያደርጋል፡፡

በከፍተኛ የገንዘብ እጥረት እየተፈተነ እንደሚገኝ የተነገረው ፌዴሬሽኑ፣ የአየር ትኬት፣ የሆቴል እንዲሁም ለተለያዩ ወጪዎችን ፌዴሬሽኑ በሚያደርገው ጥረት አማካይነት ተሳትፎ እያደረገ እንደሚገኘ የኢትዮጵያ እጅ ኳስ ፌዴሬሽንና የምሥራቅ አፍሪካ የዞን 5 እጅ ኳስ ኮንፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ፍትሕ ወልደሰንበት (ዶ/ር) ያስረዳሉ፡፡

ፌዴሬሽኑ ባልተመቻቸ ሁኔታ ውስጥ ሆኖም በወንዶች ከ18 እና 20 ዓመት በታች፣ በሴቶች ከ18 እና ከ20 ዓመት በታች እንዲሁም በአፍሪካ የክለቦች ሻምፒዮና እየተሳተፈ ይገኛል፡፡

ከሚያዝያ 16 እስከ 22 ቀን 2015 ዓ.ም. በታንዛንያ ዳሬሰላም በተከናወነው የዞን 5 የታዳጊና የወጣቶች ውድድር የተካፈሉት የኢትዮጵያ ሴቶች ከ17 እና 19 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ሁለተኛ ደረጃን ይዞ ማጠናቀቅ ችሏል፡፡

በሻምፒዮናው ኢትዮጵያን ወክሎ ያቀናው 34 አባላት ያሉበት ልዑካን የአየር ትኬት፣ የመኝታ፣ እንዲሁም የምግብ ወጪ ብሔራዊ ፌዴሬሽን ከዓለም አቀፍ እጅ ኳስ ፌዴሬሽን ጋር በመነጋገር ወጪዎች ተሸፍኖ እንዲካፈል ማስቻሉን ፍትሕ (ዶ/ር) ለሪፖርተር አስረድተዋል፡፡

ብሔራዊ ቡድኑ በሻምፒዮናው የብር ሜዳሊያ፣ የዋንጫ እንዲሁም የሰርተፍኬት ሽልማት ማግኘት ችሏል፡፡

ብሔራዊ ቡድኑ በአፍሪካ የተለያዩ ሻምፒዮናዎች ላይ ውክልናው በማስጠበቅ በተሳትፎ የቀጠለ ሲሆን፣ አገርን እንደ መወከሉ መጠን ከመንግሥት አስፈላጊውን ትኩረት እንዳላገኘና በርካታ ችግሮችን ተቋቁሞ እየተካፈለ እንደሚገኝ ፍትሕ (ዶ/ር) ገልጸዋል፡፡

እንደ ፕሬዚዳንቱ አስተያየት ከሆነ፣ ብሔራዊ ቡድኑ የወከለው አገርን እንደመሆኑ መጠን፣ በአፍሪካ ያለውን ተሳትፎና ዕውቅና ማስቀጠል እንዲያስችል ከፍተኛ የመንግሥት ድጋፍ ያሻዋል፡፡

‹‹ብሔራዊ ቡድኑ የፌዴሬሽኑ ሳይሆን የአገር ነው፡፡ አገር ደግሞ መንግሥት ነው፡፡ መንግሥት ብሔራዊ ቡድኑ በቂ ዝግጅት እንዲያደርግ እንዲሁም በቂ የሥነ ልቦና ዝግጅት እንዲያደርግ አስፈላጊውን በጀት መመደብ አለበት፤›› በማለት ፍትሕ (ዶ/ር) ለሪፖርተር አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡

ብሔራዊ ቡድኑ በታንዛኒያ ባደረገው ተሳትፎ ከዓለም አቀፉ የእጅ ኳስ ፌዴሬሽን መሠረታዊ ወጪ ሽፋን ባሻገር የትጥቅ ድጋፉን ደግሞ ከኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ማግኘቱ ተገልጿል፡፡

‹‹በአንፃሩ ቡድኑ መለያ መቀየር ቢኖርበት አማራጭ ትጥቅ እንኳ የለውም ነበር፡፡ ብሔራዊ ቡድኑ የአገርን ሰንደቅ ዓላማ አንግቦ ከመወዳደሩ አንፃር ባይተዋር ተደርጓል፤›› በማለት ፍትሕ (ዶ/ር) ስለ ሁኔታው አክለዋል፡፡

ፌዴሬሽኑ ስፖርቱን እያስፋፋ፣ እያለማና ተወዳዳሪዎችን እያበቃ በአኅጉር አቀፍ ውድድሮች ሳይቀር ንቁ ተሳትፎ በማድረግ ኃላፊነቱ እየተወጣ እንደሚገኝ የሚገልጹት ፕሬዚዳንቱ፣ በአንፃሩ ብሔራዊ ቡድኑ አገርን ወክሎ ተሳትፎ ሲያደርግ ትኩረት መነፈጉን አግባብ አይደለም ሲሉ ፍትሕ (ዶ/ር) ያስረዳሉ፡፡ 

ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ በአኅጉር አቀፍ ውድድሮች ከሚያደርገው ንቁ ተሳትፎ ባሻገር፣ የበጀት እጥረት እየፈተነውም ቢሆን የኢትዮጵያ እጅ ኳስ ፕሪሚየር ሊግን እያከናወነ እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡

አምስት ዓመታት የተሻገረው ውድድሩ አገራቸውን በአፍሪካ መድረክ የሚወክሉ ክለቦች ማፍራት መቻሉ ተጠቅሷል፡፡

39ኛው የአፍሪካ ክለቦች እጅ ኳስ ሻምፒዮና ከሚያዝያ 30 ቀን 2015 ዓ.ም. ጀምሮ በግብፅ ካይሮ ከተማ የሚከናውን ሲሆን፣ የቂርቆስ ክፍለ ከተማ የእጅ ኳስ ክለብ በውድድሩ ይሳተፋል፡፡

በሌላ በኩል በፕሪሚየር ሊጉም ጥሩ ተሳትፎ የሚያደርጉ ክለቦች ቢኖሩም፣ ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ ዓመታዊ ውድድሮችን ለማድረግ ክልሎችን ቢጋብዝም በአቅም እጥረት ምክንያት መሳተፍ እንደማይችሉ ሲገልጹ መመልከት እየተለመደ መምጣቱን ፍትሕ (ዶ/ር) አንስተዋል፡፡

የኢትዮጵያ እጅ ኳስ ብሔራዊ ቡድን በአኅጉር አቀፍ ውድድሮች ውጤታማ ጉዞን ይዞ እንዲቀጥል እንዲሁም የኢትዮጵያ ውክልና በዓለም አቀፍ ውድድሮች እንዲጠበቅ የመንግሥት ድርሻ ከፍተኛ መሆኑን ፕሬዚዳንቱ ያሳስባሉ፡፡ ይህም ድጋፍ የክልሎችን ተሳታፊነት ጨምሮ በአኅጉር አቀፍ ደረጃ ንቁ ተሳትፎ እያደረገ የሚገኘውን ብሔራዊ ቡድን ከባይተዋርነት መጠበቅ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡  

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ለሰው ልጅ መብት መከበር ስናወራ 75 ዓመት ሞላን!

በገነት ዓለሙ ዓለም ስለሰብዓዊ መብቶች ሲያወራ፣ ሲምል፣ ሲገዘት፣ ሲፈጠም፣ ቃል...

ካልተማከለ የካፒታል ገበያ ወደ ዘመናዊና የተደራጀ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ

በእሱፈቃድ ተረፈ በአገራችን የካፒታል ገበያ አዋጅ መውጣትን ተከትሎ የተማከለ የሰነደ...

ለማይቀረው ምክክርና ድርድር እንዘጋጅ

በያሲን ባህሩ  የዘመናዊት ኢትዮጵያ ፖለቲካ ውዝግብ በትንሹ የአንድ ምዕተ ዓመት...

ደንብ አስከባሪዎች ደንብ ያክብሩ!

በአዲስ አበባ ከተማ ደንብ አስከባሪዎች፣ ሌሎች የፀጥታ አካላት፣ እንዲሁም...