Monday, December 11, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ኪንና ባህልየመጀመርያው የጁገል ሽልማት በሹዋሊድ

የመጀመርያው የጁገል ሽልማት በሹዋሊድ

ቀን:

ከሦስት አሠርታት በላይ በቅርስ ጥበቃና ክብካቤ በመሰማራትና የግል ሙዚየም በማቋቋም በቀዳሚነት የሚጠቀሱት ሐጂ አብደላ ዓሊ ሸሪፍ የመጀመርያውን የጁገል ሽልማትን ተቀበሉ፡፡

የዘንድሮ የሹዋሊድ ሐሙስ ሚያዝያ 19 ቀን 2015 ዓ.ም. በሐረር ከተማ መከበር ሲጀምር በተዘጋጀው የጁገል ሽልማት ሥነ ሥርዓት ላይ አብደላ ዓሊ ሸሪፍ ሽልማታቸውን የተቀበሉት ከሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ኦርዲን በድሪ እጅ ነው፡፡

የሐረሪ ብዙኃን መገናኛ እንደዘገበው፣ ተሸላሚው በሐረር ከተማ በግል ተነሳሽነት የራሳቸውን ቤት በመጠቀም ሙዚየም ያቋቋሙና ልዩ ልዩ ቅርሶችን ከተለያዩ አካባቢዎች በመሰብሰብና በማስጎብኘት ሥራቸውን እያከናወኑ ይገኛሉ፡፡

የመጀመርያው የጁገል ሽልማት በሹዋሊድ | Ethiopian Reporter | ሪፖርተር
የሸሪፍ ሙዚየም ከያዛቸው ተንቀሳቃሽ ቅርሶች መካከል ጥንታዊ መጻሕፍት ይገኙበታል

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ‹‹የአገራችንን ጥንታዊና ዘመናዊ ሥልጣኔዎችን በዓለም እንዲታወቁ የላቀ አስተዋጽኦ አበርክተዋል፤›› በማለት በ2013 ዓ.ም. ‹‹የክብር ዶክትሬት ዲግሪ›› የሰጣቸው ሐጂ አብደላ ዓሊ ሸሪፍ፣ ቅርስ ማሰባሰብ የጀመሩት ቀደምት የሐረሪ ሙዚቃዎችንና ጥንታዊ በብራና ላይ የተጻፉ ጽሑፎችን በማሰባሰብ ነበር፡፡  

ለሁለት አሠርታት አካባቢ ለቅርስ ማሰባሰቢያነት፣ መጠገኛነትና ጎብኚዎች የሚስተናገዱበት የነበረው በአነስተኛ መኖሪያ ቤታቸው ሲሆን፣ ተግባራቸው ፍሬ አፍርቶ በ1991 ዓ.ም. ‹‹ሸሪፍ ሙዚየም›› በሚል መጠሪያ የግል ሙዚየም ማቋቋማቸው ገጸ ታሪካቸው ያስረዳል፡፡

ከኢትዮጵያውያን ባሻገር የውጭ አገር ዜጎችንና ቱሪስቶችን ቀልብ በመግዛቱ፣ የክልሉ መንግሥት ባለሙያው እያከናወኑት ላለው የቅርስ ማሰባሰብና ጥበቃ ተግባር ውጤታማ እንዲሆን፣ ቀድሞ ‹‹የተፈሪ መኮንን ጫጉላ ቤት›› የነበረውን ታሪካዊ ቤት ለሙዚየምነት እንዲገለገሉበት አድርጓል፡፡

የሐረሪ ብዙኃን መገናኛ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ እንደገለጸው፣ የሸሪፍ ሙዚየም የተለያዩ እምነቶች ታሪካዊ፣ ባህላዊና ሃይማኖታዊ የተለያዩ ብሔረሰቦች መገለጫ የሚሆኑ ከ13 ሺሕ በላይ ቅርሶችን አሰባስቦ የያዘ ነው፡፡

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ሃቻምና የክብር ዶክትሬቱን በሰጣቸው ወቅት አድናቆቱን ለሐጂ አብደላ ዓሊ ሸሪፍ የገለጸው፣ ‹‹ዩኒቨርሲቲው በኢትዮጵያ ባልተለመደው በግል የቅርስ ማሰባሰብና ጥበቃ ዘርፍ የተሰማሩ ‹የትውልድ አብሪ ኮከብ፣ የቅርስ ጥበቃ ጀግና› አድርጎ ይመለከታቸዋል፤›› በማለት ነበር፡፡

የሹዋሊድ የረመዳን ጾም በወጣ በሳምንቱ የሚከበር የሐረሪ ብሔረሰብ በዓል ሲሆን፣ በዋናነት ወጣቶችና ልጃገረዶች ለትዳር የሚተጫጩበት፣ ባህላዊ ጭፈራዎችና ሃይማኖታዊ ዝክር የሚከናወንት እንደሆነ ስለበዓሉ የተሠራጨው ጽሑፍ ያስረዳል፡፡

ከሚያዝያ 19 ቀን 2015 ዓ.ም. ጀምሮ ለ48 ሰዓታት በሐረር ከተማ ልዩ ስሙ አሱማይ በሪ እና አርጎባ በሪ ተብሎ በሚጠሩ ቦታዎች በዓሉ እየተከበረ መሆኑ ‹ቪዚት ሐረር› በተሰኘው ማኅበራዊ ትስስር ገጽ ተገልጿል፡፡

የክልሉ ባህል ቅርስና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ አቶ ተወለዳ አብዶሽ እንደገለጹት፣ የሹዋሊድ በዓል ሐረር በሃይማኖት፣ በታሪክ፣ በባህልና በቅርስ ያሏትን ቱባ እሴቶች ለማስተዋወቅ የሚረዳ ነው፡፡

ክብረ በዓሉ በዓለም አቀፍ የባህል ተቋም ዩኔስኮ በማይዳሰስ ባህላዊ ቅርስነት እንዲመዘገብ የተጀመረው ሥራ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ርዕሰ መስተዳድሩ ጥሪ ማቅረባቸውን ብዙኃን መገናኛው ዘግቧል፡፡

በክብረ በዓሉ የተለያዩ ብሔረሰቦች ባህላዊ ትርዒት ከመቅረቡ በተጨማሪ፣ በአጎራባች ክልሎች የሚገኙ ብሔረሰቦች ባህላዊ እሴቶችን የሚያሳይ ዓውደ ርዕይም ተከፍቷል፡፡   

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ለሰው ልጅ መብት መከበር ስናወራ 75 ዓመት ሞላን!

በገነት ዓለሙ ዓለም ስለሰብዓዊ መብቶች ሲያወራ፣ ሲምል፣ ሲገዘት፣ ሲፈጠም፣ ቃል...

ካልተማከለ የካፒታል ገበያ ወደ ዘመናዊና የተደራጀ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ

በእሱፈቃድ ተረፈ በአገራችን የካፒታል ገበያ አዋጅ መውጣትን ተከትሎ የተማከለ የሰነደ...

ለማይቀረው ምክክርና ድርድር እንዘጋጅ

በያሲን ባህሩ  የዘመናዊት ኢትዮጵያ ፖለቲካ ውዝግብ በትንሹ የአንድ ምዕተ ዓመት...

ደንብ አስከባሪዎች ደንብ ያክብሩ!

በአዲስ አበባ ከተማ ደንብ አስከባሪዎች፣ ሌሎች የፀጥታ አካላት፣ እንዲሁም...