የሐረሪ ብሔረሰብ በየዓመቱ ዒድ አልፈጥር በተከበረ በሳምንቱ የሚያከብረው ሹዋሊድ ክብረ በዓልን ከሚያዝያ 19 ቀን ጀምሮ ለሦስት ቀናት በልዩ ልዩ ዝግጅቶች አክብሯል፡፡ የአከባበር መርሐ ግብሩ እንደሚሳየው በክብረ በዓሉ የተካተቱት፣ የባህል ፌስቲቫል፣ ታሪካዊ ቅርሶችና የሙዚየም ጉብኝት፣ ዓውደ ጥናትና ዓውደ ርዕይ እንዲሁም የልማት ፕሮጀክቶች ምረቃ ይገኙበታል፡፡ በሥነ በዓሉ ላይ የፌዴራልና የክልል ባለሥልጣኖች ተገኝተውበታል፡፡