Monday, December 11, 2023
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

የኢትዮጵያን ይግዙ የንግድ ትርዒት ነገ ይከፈታል

ተዛማጅ ፅሁፎች

  • ከሱዳን የሚጠበቁ 50 ኩባንያዎች በተፈጠረው ጦርነት ምክንያት ቀርተዋል

የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ከ250 በላይ የአገር ውስጥና የውጭ ኩባንያዎች የሚሳተፉበት፣ የኢትዮጵያን ይግዙ፣ በኢትዮጵያ ኢንቨስት አድርጉ›› በሚል መሪ ቃል የተሰናዳው 13ኛው የንግድ ትርዒት በነገው ዕለት በይፋ እንደሚከፈት አስታወቀ፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ምክር ቤት የንግድ ትርዒቱን አስመልክቶ ትናንት በሰጠው መግለጫ፣ በዚህ የንግድ ትርዒት የቻይና፣ የአሜሪካ፣ የፓኪስታን፣ የጣልያንና የመሳሰሉ አገሮች ኩባንያዎች ተሳታፊ ይሆናሉ፡፡ እነዚህ ኩባንያዎች አይቲን ጨምሮ የተለያዩ የግብርና፣ የቤት ቁሳቁስ፣ የኢንዱስትሪና የመሳሰሉ ምርቶችን የሚያመርቱ ኩባንያዎች እንደሆኑም የንግድ ምክር ቤቱ ዋና ፀሐፊ አቶ ውቤ መንግሥቱ ተናግረዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት በጦርነት እየታመሰች ያለችው ሱዳን በዚህ የንግድ ትርዒት ላይ ለመሳተፍ ቀድማ አዎንታዊ ምላሽ የሰጠች አገር ስትሆን፣ ወደ 50 የሚጠጉ ኩባንያዎች ታሳትፋለች ተብሎ የተጠበቀ ቢሆንም፣ እስከ ትናንት ምሽት ድረስ ግን አንድም ኩባንያ ሊመጣ እንዳልቻለ ለማወቅ ተችሏል፡፡ በሱዳን የተቀሰቀሰው ጦርነት ተሳፎዋቸውን እንደማያስቀረው ባለፈው ሳምንት 14ቱ ኩባንያዎች ማረጋገጫ እስከመስጠት የደረሱ ቢሆንም፣ መጨረሻ ላይ ግን ግንኙነት በመቋረጡ እስካሁን ከሱዳን ይገባሉ የተባሉ ኩባንያዎች አለመግባታቸውን የንግድ ምክር ቤቱ መረጃ አመልክቷል፡፡

ከሱዳን ኩባንያዎች ሌላ ሌሎቹ ተሳታፊዎች እየገቡ ሲሆን፣ በተለይ በዚህ የንግድ ትርዒት ከውጭ ኩባንያዎች ተሳታፊ በመሆን በቀዳሚነት ከሚጠቀሱት ውስጥ የቻይና ሁናን ግዛት ኩባንያዎች ናቸው፡፡ ከግዛቷ ወደ ኢትዮጵያ ከመጡት ተሳታፊ ኩባንያዎች ሌላ 15 የሚሆኑ ከኢትዮጵያ ንግድ ኅብረተሰብ ጋር የቢዝነስ ግንኙነት ለመፍጠር ፍላጎት ያላቸው የኩባንያ ተወካዮች መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡

በንግድ ትርዒት ለመሳተፍና የሁለትዮሽ ግንኙነት ለመፍጠር ከሁናን ግዛት የመጡት ልዑካን በግዛቲቱ ከንቲባ ተመርተው አዲስ አበባ መግባታቸውን ዋና ፀሐፊው አቶ ውቤ ገልጸዋል፡፡ ከዚህ ቀደም የተካሄዱት 12 ንግዱ ትርዒቶች የኢትዮጵያ ምርቶች ገበያ እንዲያገኙ ያስቻሉ ከመሆኑም በላይ፣ ምርቶችን ለውጭ ኩባንያ ለማስተዋወቅ ዕድል የሰጠ እንደነበር ተገልጿል፡፡ በዘንድሮው የንግድ ትርዒትም ተመሳሳይ የገበያ ዕድሎችን ለመፍጠር ያስችላል ተብሎ ታምኗል፡፡

በንግድ ትርዒቱ ከጠቅላላ ተሳታፊዎች ውስጥ ወደ 40 በመቶ የሚሆኑት በአነስተኛና መካከለኛ ደረጃ ላይ ያሉ አምራቾች እንዲሳተፉ ዕድል የተሰጣቸው ሲሆን፣ የተወሰኑትም ኩባንያዎች ለኅብረተሰቡ ምርቶቻቸውን እንዲሸጡ የተፈቀደላቸው መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች