Tuesday, May 21, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ስፖርትሠራተኞችን ያነቃቃው ዓመታዊው የስፖርት ውድድር

ሠራተኞችን ያነቃቃው ዓመታዊው የስፖርት ውድድር

ቀን:

በኢትዮጵያ ሠራተኞች ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሠማኮ) አማካይነት በየዓመቱ በሦስት የተለያዩ መድረኮች በሚካሄደው ስፖርታዊ እንቅስቃሴ በርካታ የሠራተኛ ስፖርት ማኅበራት ሲሳተፉ ከርመዋል፡፡

በተለይ በአገሪቱ የተለያዩ ተቋማት ውስጥ የሚያገለግሉ ሠራተኞች በስፖርታዊ እንቅስቃሴ እየተሳተፉ ጤናማ፣ ንቁና አምራች ዜጎች እንዲሆኑ ውድድሮችን ማሰናዳት ውጤታማ ሠራተኛ ማፍራት እንደሚያስችል ይታመናል፡፡

የሠራተኛ ማኅበር ዓመታዊ ውድድሮችን ማዘጋጀት ሠራተኛውን እርስ በርስ ከማቀራረብ አንፃር የጎላ ሚና እንዳለው በበርካቶች ዘንድ ይመሰከራል፡፡

- Advertisement -

በኢትዮጵያ ሠራተኞች ማኅበር ኮንፌዴሬሽን በሚሰናዱ ውድድሮች ላይ ተቋሞቻቸውን ወክለው በሚካፈሉ ተወዳዳሪዎች መካከል ከተቋም ጋር ያለውን መቀራረብ፣ ልምድ ማካፈል እንዲሁም ለተለያዩ ክለቦች ግብዓት የሚሆኑ ስፖርተኞች ማፍራት የቻለ ውድድር መሆኑ ይነገርለታል፡፡

በውድድሩ በሚካፈሉ ተቋማት መካከል በሚፈጠረው ፉክክር ምክንያትም ሠራተኛው የተሻለ ውጤት ይዞ ለመምጣት ሲሽቀዳደምና ለዓመታዊ ውድድሩ ዝግጅት ሲያደርግ መመልከት የተለመደ ነው፡፡

በዓመታዊው የሠራተኞች ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን ውድድር መሳተፍ ከጀመሩ አንዱ ስድስት ዓመታትን የተሻገረው የፍል ውኃ አገልግሎቶች ድርጅት ነው፡፡ ለሦስት ዓመታት ተቋርጦ በቆየውና በኢሠማኮ ከሚሰናዱ ውድድሮች አንዱ በሆነው የበጋ ወራት ውድድር በተለያዩ የስፖርት ዓይነቶች መካፈል የቻለው የፍል ውኃ አገልግሎት ድርጅት በሠራተኛው መካከል ከፍተኛ መነቃቃት መፍጠሩን የፍል ውኃ አገልግሎት ድርጅት መሠረታዊ ሠራተኞች ማኅበር ዋና ሰብሳቢ ወ/ሮ ትዕግሥት ሽፈራው ለሪፖርተር አስረድተዋል፡፡

ድርጅቱ በበጋ ወራት ውድድር ላይ በእግር ኳስ፣ በእጅ ኳስ እንዲሁም ገመድ ጉተታ ሲሳተፍ ነበር፡፡

በዚህም የሠራተኞች ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን አንግቦ ከተነሳው ዓላማ አንፃር ድርጅቱ በውድድሩ መካፈል ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ በሠራተኛው መካከል መቀራረብ እንዲፈጠር ማስቻሉንም ወ/ሮ ትዕግሥት ይናገራሉ፡፡

በአጠቃላይ ከ26 በላይ ሠራተኞች በውድድሩ ሲካፈሉ የቆዩ ሲሆን፣ ንቁ ተሳትፎ ሲያደርጉ መቆየታቸው ተገልጿል፡፡

በውድድሩ ለመካፈል ኢሰማኮ ከፍተኛ ድጋፍ ማድረጉን የሚያነሱት ዋና ሰብሳቢዋ፣ በቀጣይ ባልተሳተፉባቸው የስፖርት ዓይነቶች በስፋት ለመሳተፍ ዕቅድ እንዳላቸው ጠቁመዋል፡፡

በዚህም መሠረት ድርጅቱ በቀጣይ ውድድሮች በጠረጴዛ ቴኒስ፣ ከረምቡላ፣ አትሌቲክስ እንዲሁም በዳርት ስፖርቶች ላይ ለመሳተፍ በሰፊው ተሰናድተው ለመምጣት ዕቅድ እንዳለው ወ/ሮ ትዕግሥት ተናግረዋል፡፡

የፍል ውኃ አገልግሎቶች ድርጅት ለስፖርተኛው የተለያዩ ድጋፎች ያደረገ ሲሆን፣ በቀጣይ ተሳትፎ የተሻለ ውጤት ለማምጣትና በተለያዩ ስፖርቶች ለመካፈል ድጋፍ ማድረግ እንደሚገባ ወ/ሮ ትዕግሥት አክለዋል፡፡

የፍል ውኃ አገልግሎት ከ700 ሠራተኞች በላይ በሥሩ የሚያስተዳደር ሲሆን፣ የሳውና ስቲም ማሳጅ፣ ሻወር አገልግሎት ይሰጣል፡፡ ድርጅቱ በሆቴል፣ መኝታ፣ ምግብ፣ እንዲሁም የስብሰባ አዳራሽ አገልግሎቶች በመስጠት ረዥም ጊዜ ቆይቷል፡፡

ሠራተኛው በዓመታዊ ውድድሩ ላይ መካፈል እንዲችልና ጤናማ የሥራ ልምድ እንዲኖረው ግንዛቤ ማስጨበጥ አንደሚገባ ዋና ሰብሳቢዋ አውስተዋል፡፡

ለሦስት ዓመታት ተቋርጦ የቆየውና በኢሠማኮ ከሚሰናዱ ውድድሮች አንዱ የሆነው የበጋ ወራት ውድድር ከጥር 7 ቀን 2015 ዓ.ም. ጀምሮ በኢትዮጵያ ወጣቶች ስፖርት አካዴሚ እየተከናወነ ቆይቷል፡፡ በውድድሩ ላይ ከ40 በላይ የሠራተኛ ስፖርት ማኅበራት ተሳታፊ  እንደሆኑ የኢሠማኮ የማኅበራዊ ጉዳይ መምሪያ ኃላፊና የስፖርት ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ፍሥሐ ጽዮን ቢያድግልኝ አስታውቀዋል፡፡

እስከ ሰኔ ወር መጨረሻ ላይ በሚዘልቀው ውድድር ከተለያዩ ማኅበራት የተውጣጡ 830 ወንዶችና 246 ሴቶች በድምሩ 1,076 በአሥር የተለያዩ የስፖርት ዓይነቶች እንደሚፎካከሩ ይጠበቃል።

በአካዴሚው የሚከናወነው የሠራተኞቹ ውድድር ላይ ሠራተኞችም እርስ በርስ ልምድ የሚለዋወጡበት፣ የሚዝናኑበት መድረክ እንደሆነ የተገለጸ ሲሆን፣ ተመልካቾችም በውድድር ሥፍራዎች በመገኘት ፉክክሮችን እንዲመለከቱ ጥሪም ቀርቧል፡፡

በኮቪድ-19 ወረርሽኝ መከሰቱን ተከትሎ የጤና ሚኒስቴር ያወጣውን ክልከላና መመርያ ተከትሎ ውድድሮች ተቋርጠው ቢቆዩም፣ ሠራተኞች በያሉበት አካባቢ በማኅበረሰብ አቀፍ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች እንዲሳተፉ ሲደረግ መቆየቱን አቶ ፍሥሐ ጽዮን አብራርተዋል፡፡

እንደሳቸው ማብራሪያ ከሆነ የኢሠማኮ ስፖርት ክፍል ለስፖርታዊው ድድሮቹ የተለያዩ መመርያዎችን ከማዘጋጀት ጀምሮ ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጋር በመተባበር በርካታ አሠልጣኞች ልዩ ልዩ ሥልጠናዎችን እንዲያገኙ ሲሠራ መቆየቱንም አስረድተዋል፡፡

በዚህ ዘመን ሠራተኛው በስፖርት የሚያደርገው ተሳትፎ ለሚሠራበት ድርጅት ውጤታማነት የሚኖረውን አስተዋጽኦ የጎላ እንደሆነ አሠሪዎች እንደሚረዱት ይታመናል፡፡ በመሆኑም ስፖርቱ የሠራተኛውን አንድነትና ለጋራ ጉዳይ አብሮ የመቆም ባህሉን እንደሚያጠናክር ይነገራል፡፡

በአሠሪና ሠራተኛው መካከልም ጥሩ ግንኙነት እንዲዳብር በማድረግ ምርትና ምርታማነትን በመጨመር ለኢንዱስትሪ ሰላም መስፈን የላቀ አስተዋጽ እንደሚኖረው ተሳታፊዎች ይገልጻሉ፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

በሥጋ ላይ አላግባብ እየተጨመረ ያለውን ዋጋ መንግሥት ሊቆጣጠረው ይገባል

በአገራችን የግብይት ሥርዓት ውስጥ ኢኮኖሚያዊ ያልሆኑ ወይም ያልተገቡ የዋጋ...

ኢትዮጵያን የተባበረ ክንድ እንጂ የተናጠል ጥረት አይታደጋትም!

ኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ ከምትገኝበት ውጥንቅጥ ውስጥ የምትወጣበት ዕድል ማግኘት...

የፖለቲካ ቅኝቱ የሕዝባችንን ታሪካዊ ትስስር ለምን አያከብርም?

በንጉሥ ወዳጅነው የዓብይ አህመድ (ዶ/ር) መራሹ የ2010 ዓ.ም. የለውጥ መንግሥት...

ዛሬም ኧረ በሕግ!

በገነት ዓለሙ በዚህ በያዝነው ሚያዝያ/ግንቦት ወይም ሜይ ወር ውስጥ የተከበረው፣...