Monday, May 27, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ማኅበራዊከንቲባዋ ለ29 ሺሕ መምህራን የመኖርያ ቤት ጥያቄ መፍትሔ እንዲሰጡ ተጠየቁ

ከንቲባዋ ለ29 ሺሕ መምህራን የመኖርያ ቤት ጥያቄ መፍትሔ እንዲሰጡ ተጠየቁ

ቀን:

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመምህራን ማኅበር በሥሩ ከሚገኙት አባላት መካከል የ29,500 አባላቱ የመኖሪያ ቤት ችግር እንዲፈታለት፣ ከንቲባ አዳነች አቤቤን በደብዳቤ ጠየቀ፡፡

የማኅበሩ ፕሬዚዳንት አቶ ድንቃለም ቶሎሳ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ማኅበሩ ከሁለት ሳምንት በፊት ለከንቲባዋ በጻፈው ደብዳቤ፣ በአስተዳደሩ ሥር የሚገኙ መምህራን የቤት ጥያቄ እንዲፈታ ጠይቋል፡፡

የመምህራን ጥያቄ እየበረታ መምጣቱን የገለጹት ፕሬዚዳንቱ፣ ከንቲባዋ ከመምህራኑ ጋር በ2013 ዓ.ም. በነበራቸው ስብሳሰባ፣ መምህራን በማኅበር ተደራጅተው ቤት እንዲገነቡ እንደሚደረግ ቢገለጽም፣ እስካሁን ምንም ዓይነት ተስፋ ሰጪ ነገር እየታየ አይደለም ብለዋል፡፡

- Advertisement -

ማኅበሩ ለከተማዋ ከንቲባ የጻፈው ደብዳቤ ለመምህራኑ የኑሮ ውድነትን የሚያረግቡ ድጎማዎች እንዲደረጉ፣ ከንቲባዋ በመድረክ ላይ የገቡት ቃል ወደ ታች ወርዶ እንዲፈጸምና በከተማ አስተዳደሩ በተጀመሩ ልማቶች የመምህራን ጥያቄዎች እልባት እንዲያገኙ ጠይቋል፡፡

የመምህራን የደመወዝ ጥያቄ የከተማ አስተዳደሩ የችግሩን አሳሳቢነት በመረዳት ከተቻለ በልዩ ትኩረት በከተማው ደረጃ ውሳኔ ሰጥቶበት እንዲፈታ፣ ካልሆነም ደግሞ የሚመለከተው የፌዴራል ተቋም ለጉዳዩ ትኩረት በመስጠት እልባት መስጠት እንዲቻል እንዲደረግም ጥሪ ቀርቧል፡፡

ለከንቲባዋ የተላከው ደብዳቤ ለመምህራን ሁለተኛ መሥሪያ ቤታቸው የሆነው የመኖሪያ ቤት ጥያቄ፣ ግንቦት 2013 ዓ.ም. መምህራንን ባወያዩበት ወቅት ‹‹መምህራን በማኅበር ተደራጅተው ቤት እንዲገነቡ እንደሚደረግ የተገለጸ ቢሆንም፣ ነገር ግን እስካሁን በተፈለገው ርቀት ወደ ሥራ አለመገባቱን ያትታል፡፡ በዚህ የተነሳ ባለፉት ወራት ምንም ዓይነት ለውጥ አለመኖሩ መምህራንን ተጠቃሚ ከማድረግ ይልቅ፣ ጉዳዩን በተቃራኒ በጥርጣሬ እንዲያዩት አነሳሽ ምክንያት ከመሆኑም በላይ ተስፋ አስቆራጭነቱ እየሰፋ የመጣ ስለመሆኑም ደብዳቤው ያብራራል፡፡

ይህ ጉዳይ መምህራኑ ቃል የገቡልንን አልተገበሩልንም (አላስተገበሩልንም) የሚል ስሜት ፈጥሮ የመምህራንን ሞራል ያላሸቀ፣ ቤት ባላቸውና በሌላቸው መምህራን መካከል የፍትሐዊነት ጥያቄ ያስነሳ መሆኑም በደብዳቤው ተመላክቷል፡፡

መምህራን የሚያገኙት የደመወዝ መጠንና በአሁኑ ወቅት ያለው የቤት ኪራይ ዋጋ፣ በተጨማሪም የኑሮ ውድነት መምህራንን ተረጋግተው እንዳያስተምሩ ጫና እየፈጠረ በመሆኑ፣ ከንቲባዋ ለመምህራኑ በገቡት ቃል መሠረት ለጉዳዩ ልዩ ትኩረት በመስጠት፣ የመምህራን የመኖሪያ ቤት ጥያቄ ምላሽ እንዲያገኝ ‹‹አጥብቀን እንጠይቃለን›› ሲል ማኅበሩ በደብዳቤ አስታውቋል፡፡

በአሁኑ ወቅት ያለውን የኑሮ ውድነት መምህራኑ ከሚያገኙት ደመወዝና የኑሮ መደጎሚያ ጋር ተቋቁሞ መኖር ከባድ መሆኑን የሚያስረዳው ደብዳቤው፣ የከተማ አስተዳደሩ ከዚህ ቀደም ባደረገው የኑሮ መደጎሚያ ላይ ወቅቱን የሚመጥን ማሻሻያ እንዲያደርግ ጠይቋል፡፡

የመምህራን ማኅበሩ ፕሬዚዳንት መምህራኑ በአሁኑ ወቅት የኑሮ ውድነት ማረጋጊያ ድጎማ 3,000 ብር የሚሰጥ ቢሆንም፣ ገንዘቡ ከችግሩ ጋር አብሮ የማይሄድ በመሆኑ ቢያንስ በእጥፍ እንዲያድግ መምህራኑ ይፈልጋሉ ብለዋል፡፡

ለከንቲባዋ የተላከው ደብዳቤ በመምህርነት ሙያ ላይ 40 ዓመትና 18 ዓመት ያገለገሉ መምህራን በአንድ ቋት ውስጥ አንድ ዓይነት ደመወዝ ስኬል መካተታቸውን ጠቅሶ፣ ይህም አግባብነት የሌለው በመሆኑ እንደ መንግሥት አስቸኳይ እልባት ያስፈልገዋል ብሏል፡፡

ግንባታው የተጀመረው የመምህራን ሆስፒታልና ሁለገብ ማዕከል ግንባታው እንዲፋጠን፣ መንግሥት በገንዘብም ሆነ በቁሳቁስ ድጋፍ እንዲያደርግና የቴክኒክና ሙያ ማሠልጠኛ መምህራን የሥራ ላይ ዋስትና የሌላቸው በመሆኑ፣ ከሥራው ባህሪ አንፃር የሥራ ላይ ዋስትና/ኢንሹራንስ እንዲፈቀድላቸው በሚል አክሎ ጠይቋል፡፡

ማኅበሩ ደብዳቤውን ለከንቲባዋ ከላከ በኋላ ከመምህራን የቤት ጥያቄ ጋር የተጀመሩ እንቅስቃሴዎች ስለመኖራቸው ፕሬዚዳንቱ ተናግረዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የፋይናንስ ኢንዱስትሪው ለውጭ ባንኮች መከፈት አገር በቀል ባንኮችን ለምን አስፈራቸው?

የማይረጥቡ ዓሳዎች የፋይናንስ ተቋማት መሪዎች ሙግት ሲሞገት! - በአመሐ...

የምርጫ 97 ትውስታ!

በበቀለ ሹሜ      መሰናዶ ኢሕአዴግ ተሰነጣጥቆ ከመወገድ ከተረፈ በኋላ፣ አገዛዙን ከማሻሻልና...

ሸማቾች የሚሰቃዩት በዋጋ ንረት ብቻ አይደለም!

የሸማች ችግር ብዙ ነው፡፡ ሸማቾች የሚፈተኑት ባልተገባ የዋጋ ጭማሪ...

መንግሥት ከለጋሽ አካላት ሀብት ለማግኘት የጀመረውን ድርድር አጠናክሮ እንዲቀጥል ፓርላማው አሳሰበ

የሦስት ዩኒቨርሲቲዎች ፕሬዚዳንቶች በኦዲት ግኝት ከኃላፊነታቸው መነሳታቸው ተገልጿል አዲስ አበባ...