Sunday, May 19, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ዜናበኬንያ ታግተው ደብዛቸው በጠፋው ኢትዮጵያዊ ምክንያት በመንግሥትና በኬንያ ላይ ክስ ተመሠረተ

በኬንያ ታግተው ደብዛቸው በጠፋው ኢትዮጵያዊ ምክንያት በመንግሥትና በኬንያ ላይ ክስ ተመሠረተ

ቀን:

በኬንያ ናይሮቢ ታግተው የደረሱበት ሳይታወቅ አንድ ዓመት ከስድስት ወራት አስቆጥረዋል በተባሉት አቶ ሳምሶን ተክለ ሚካኤል ጉዳይ የኢትዮጵያ በጠቅላይ ሚኒስቴር ጽሕፈት ቤት፣ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርና በኢትዮጵያ የኬንያ ኤምባሲ ላይ ክስ መመሥረታቸውን ባለቤታቸውና ጠበቃቸው አስታወቁ፡፡

የአቶ ሳምሶን ባለቤት ወ/ሮ ሚለን ሐለፎም፣ አቶ ሳምሶን በኬንያ ፖሊሶች ታፍነው ከተወሰዱ አንድ ዓመት ከስድስት ወራት ቢሆናቸውም፣ የሚመለከታቸው አካላት ሁሉ ስለጉዳዩ ምርመራ እያደረጉ መሆናቸውን ከመግለጽ ባሻገር፣ ያሉበትን ሁኔታ ለማሳወቅ እየተንቀሳቀሱ ያለበት ሁኔታ ቸልተኝነት ስለታየባቸው፣ ከላይ በተጠቀሱት ሦስት መንግሥታዊ ተቋማት ላይ ክስ መመሥረታቸውን ሐሙስ ሚያዚያ 12 ቀን 2015 ዓ.ም. በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ተናግረዋል፡፡

የመንግሥት ተቋማቱ ክስ የተመሠረተባቸው በአቶ ሳምሶን ጉዳይ ቸልተኝነትን በማሳየታቸው መሆኑን ያስረዱት ወ/ሮ ሚለን፣ ‹‹ኬንያና ኢትዮጵያ ባላቸው ጥሩ ግንኙነት ይህንን ችግር መቅረፍ አይከብዳቸውም፡፡ ልጆቻቸው አባታችውን እየጠበቁ ቢሆንም፣ ጉዳዩን እየተከታተሉ ያሉት ተከሳሽ ተቋማት ግን እስካሁን ምርመራ እያደረጉ መሆናቸውን ነው የሚገልጹት፤›› ሲሉ አማረዋል፡፡

- Advertisement -

‹‹አንድ ግለሰብ አንድ ዓመት ከስድስት ወራት ሲሞላው ምን እየደረሰበት እንደሆነ አለማወቅ ከባድ ነው፡፡ አንድ ሰው ሞቷል ሲባል ጥሩ ዜናም ባይሆን ቤተሰብ ቁርጡን እንዲያውቅ ይረዳል፡፡ ታስሯል ቢባል ደግሞ ሄዶ ማየት ይቻላል፤›› ያሉት ወ/ሮ ሚለን፣ ባለቤታቸው አጥፍተውም ከሆነ በሕጉ መሠረት ተጠያቂ መደረግ እንደነበረባቸው ተናግረዋል፡፡

በፌዴራል መንግሥትና በኦሮሚያ ክልል በማንኛውም ፍርድ ቤት ጠበቃና የሕግ አማካሪ የሆኑት ጠበቃ ዳባ ጩፋ (ዶ/ር) በበኩላቸው፣ ‹‹ደንበኛዬ በኬንያ በደረሰባቸው የሰብዓዊ መብት ጥሰት ከአንድ ዓመት በላይ ያለበት አይታወቅም፤›› ብለው፣ መታሰራቸው ወይም መሞታቸው አለመነገሩ አሳሳቢ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

‹‹ጉዳዩ ወደ ፍርድ ቤት የመጣበት ምክንያት እነዚህ የተከሰሱ አካላት ግዴታቸውን ባለመወጣታቸው ነው፡፡ ፍርድ ቤት በሕግ አግባብ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ማስገደድ የሚችል በመሆኑ እንደሚያስገድዳቸው እንጠብቃለን፤›› ሲሉም ጠበቃው ተናግረዋል፡፡

‹‹አቶ ሳምሶን ያለ ሥጋት ደኅንነታቸው ተጠብቆ የመኖር መብረቸውን ስለተነጠቁ ክስ መሥርተናል፤›› ያሉት ዳባ (ዶ/ር)፣ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት፣ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርና በኢትዮጵያ የኬንያ ኤምባሲ ላይ ክስ እንደመሠረቱና ምላሽ ለማግኘት ቀጠሮ እንደተሰጣቸው ጠቁመዋል፡፡

ጠበቃው ደንበኛቸው በሕገ መንግሥቱ መሠረት በሕግ የተያዙ ሰዎች መብት በ48 ሰዓታት ውስጥ ፍርድ ቤት የመቅረብና ከጠበቃ ጋር የመገናኘት መብት ተጥሷል፡፡ ወንጀል ካለ ከሕግ አግባብ ውጪ ይለቀቁ አልልም፡፡ ወንጀል ሠርተው ከሆነም ሕግ በሚፈቅደው አግባብ ወደ ፍርድ ቤት ቀርበው ጉዳያቸው ታይቶ እንዲለቀቁ ክስ መሥርተናል፤›› ብለዋል፡፡

አቶ ሳምሶን ወንጀል ለመሥራት የሚያስችላቸው ወጣ ያለ ባሕሪ እንዳላቸው ጥያቄ የቀረበላቸው ባለቤታቸው፣ ‹‹ወንጀል ሠርቶ ሊሆን ይችላል ብዬ የምሠጋበት ነገር የለም፡፡ ወንጀል ሠርቶ ቢሆን እንኳ ፍርድ ቤት ቀርቦ ፍትሕ የማግኘት መብቱ አልተጠበቀለትም፤›› ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

ጠበቃና የሕግ አማካሪው በበኩላቸው፣ ‹‹በፖሊስ ከመወሰዳቸው በፊት ‹ከወንጀል ነፃ› ተብሎ የተሰጣቸው የምስክር ወረቀት አለ፡፡ ይረዳኛል ብዬ ለፍርድ ቤት አቅርቤያለሁ፤›› ብለዋል፡፡

‹‹ለግለሰቡ እስካሁን ያሉበት ሁኔታ አለመታወቅ፣ በኬንያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ድክመት ነው፤›› በማለት ዳባ (ዶ/ር) ሲናገሩ፣ ጉዳዩን በይበልጥ መከታተል የነበረበትና መጠየቅ ያለበት ይኸው ኤምባሲ መሆን አልነበረም ወይ ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄ፣ ኤምባሲው በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሥር ስለሚገኝ ለሚኒስቴሩ ጥያቄ ማቅረባቸውን ገልጸዋል፡፡

አቶ ሳምሶን ኅዳር 10 ቀን 2014 ዓ.ም. በኬንያ ናይሮቢ በአምስት የኬንያ መለዮ በለበሱ ፖሊሶች ከመኪናቸው አስወርደው እንደወሰዷቸው፣ በወቅቱ በተሠራጨው ቪዶዮ ታይቶ እንደነበር በክሱ ተጠቅሷል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

በሥጋ ላይ አላግባብ እየተጨመረ ያለውን ዋጋ መንግሥት ሊቆጣጠረው ይገባል

በአገራችን የግብይት ሥርዓት ውስጥ ኢኮኖሚያዊ ያልሆኑ ወይም ያልተገቡ የዋጋ...

ኢትዮጵያን የተባበረ ክንድ እንጂ የተናጠል ጥረት አይታደጋትም!

ኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ ከምትገኝበት ውጥንቅጥ ውስጥ የምትወጣበት ዕድል ማግኘት...

የፖለቲካ ቅኝቱ የሕዝባችንን ታሪካዊ ትስስር ለምን አያከብርም?

በንጉሥ ወዳጅነው የዓብይ አህመድ (ዶ/ር) መራሹ የ2010 ዓ.ም. የለውጥ መንግሥት...

ዛሬም ኧረ በሕግ!

በገነት ዓለሙ በዚህ በያዝነው ሚያዝያ/ግንቦት ወይም ሜይ ወር ውስጥ የተከበረው፣...