Tuesday, September 26, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትየረዥም ርቀት ከዋክብት የሚጠበቁበት የለንደን ማራቶን

የረዥም ርቀት ከዋክብት የሚጠበቁበት የለንደን ማራቶን

ቀን:

ለ43ኛ ጊዜ የሚከናወነው የለንደን ማራቶን እሑድ ሚያዝያ 15 ቀን 2015 ዓ.ም. ይካሄዳል፡፡ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት እ.ኤ.አ. ከ2019 ጀምሮ በእንግሊዝ ፀደይ ወቅት ሲከናወን የቆየ ሲሆን፣ ዘንድሮ ከሦስት ዓመታት በኋላ በመፀው ወቅት ይከናወናል፡፡

በተለምዶ ጠፍጣፋ የውድድር ቦታ እንዳለው በሚነገርለት የለንደን ማራቶን ለመሳተፍ በርካታ የረዥም ረቀት ከዋክብት ስም ይፋ ሆኗል፡፡

አዘጋጁ በዘንድሮ የለንደን ማራቶን እንደሚሳተፉ ስም ዝርዝራቸውን ይፋ ካደረጋቸው አትሌቶች መካከል በወንዶች አምስት የግል ፈጣን ሰዓት ካላቸው አትሌቶች ውስጥ አራቱ ይገኙበታል፡፡ ከእነዚህም መካከል ቀነኒሳ በቀለ፣ ኬልቪን ኪፕቶም፣ ብርሃኑ ለገሠና ሞስነት ገረመው ይገኙበታል፡፡ የኦሊምፒክ ሻምፒዮናው ቀነኒሳና በመጀመርያ የማራቶን ተሳትፎ የምንጊዜም ፈጣን ሰዓት በቫሌንሺያ ማራቶን ማስመዝገብ የቻለው ኪፕቶም ስማቸው በቀዳሚነት ተጠቅሷል፡፡

የ2022 የለንደን ማራቶን አሸናፊ አሞሳ ኪፕሪቶ በዘንድሮ ውድድር እንደሚሳተፍ ታውቋል፡፡ በኦሪገኑ የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ በወንዶች ማራቶን የወርቅ ሜዳሊያን ያስገኘው ታምራት ቶላ ሌላው የውድድሩ ድምቀት ነው፡፡

የ2022 የለንደን ማራቶን ሁለተኛ ደረጃ ይዞ ያጠናቀቀው ልዑል ገብረ ሥላሴ፣ የኒውዮርክ ማራቶን የሁለት ጊዜ አሸናፊው ጄዮፌሬይ ካሞውሮ ከፍተኛ ግምት ከተሰጣቸው አትሌቶች መካከል ይጠቀሳል፡፡ የእንግሊዙ ሞ ፋራ የለንደን የመጨረሻ ተሳትፎውን እንደሚያደርግ ተጠቁሟል፡፡

ሴቶች ከ2፡18 የግል ምርጥ ሰዓት ማስመዝገብ የቻሉ አትሌቶች፣ እንዲሁም አሥር 21፡19 የግል ምርጥ ሰዓት ያላቸው አትሌቶች እሑድ በሚከናወነው የለንደን ማራቶን እንደሚካፈሉ ታውቋል፡፡

በውድድሩ የዓለም ክብረ ወሰን ባለቤት ብሪጊድ ኮስጌይ፣ የ2020 የኦሊምፒክ ሻምፒዮናዋ ፔሪስ ጄፕቺርቺር እንዲሁም የ2022 ለንደን ማራቶን አሸናፊዋ የዓለም ዘርፍ የኋላ ይጠበቃሉ፡፡

በመርሐ ግብሩ መሠረት የ1,500 ሜትር የዓለም ክብረ ወሰን ባለቤትና በቅርቡ የጎዳና ውድድር የተቀላቀለችው ገንዘቤ ዲባባ፣ እንዲሁም የ10 ሺሕ ሜትር ፈርጧ አልማዝ አያና ለንደን ከትመዋል፡፡

የቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ በ5 ሺሕ እና 10 ሺሕ ሜትር ወርቅ ያሳካችው ኔዘርላዳዊቷ ሲፋን ሐሰን የመጀመርያ የማራቶን ተሳትፎዋን ታደርጋለች፡፡ በማራቶን ውድድር በርካታ ሻምፒዮኖች የሚወዳደሩበት የለንደን ማራቶን አሸናፊውን ለመገመት በቀላል የሚቻል አይደለም፡፡

አሸናፊ ለሚሆኑ አትሌቶች ከ313,000 ዶላር በላይ የተሰናዳ ሲሆን፣ የሁለቱም ፆታ አሸናፊዎች 55,000 ዶላር ይበረከትላቸዋል፡፡ ሽልማቱ ከአንደኛ እስከ አሥረኛ ደረጃን ይዘው የሚወጡትን ያካትታል፡፡   

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የቤት ባለንብረቶች የሚከፍሉትን ዓመታዊ የንብረት ታክስ የሚተምን ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጀ

በአዋጁ መሥፈርት መሠረት የክልልና የከተማ አስተዳደሮች የንብረት ታክስ መጠን...

እንደ ንብረት ታክስ ያሉ ወጪን የሚያስከትሉ አዋጆች ከማኅበረሰብ ጋር ምክክርን ይሻሉ!

የመንግሥትን ገቢ በማሳደግ ረገድ አስተዋጽኦ እንዳላቸው የሚታመኑት የተጨማሪ እሴት...

ለዓለምም ለኢትዮጵያም ሰላም እንታገል

በበቀለ ሹሜ ያለፉት ሁለት የዓለም ጦርነቶች በአያሌው የኃያል ነን ባይ...