Friday, June 14, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ማኅበራዊከተሽከርካሪዎች መብዛት ጋር በተያያዘ የሕግ ጥሰቶች እየተበራከቱ መሆኑን ትራፊክ ማኔጅመንት ገለጸ

ከተሽከርካሪዎች መብዛት ጋር በተያያዘ የሕግ ጥሰቶች እየተበራከቱ መሆኑን ትራፊክ ማኔጅመንት ገለጸ

ቀን:

በየዕለቱ ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ ተሽከርካሪዎች ቁጥር ከፍተኛ መሆኑን ተከትሎ የትራፊክ ሕግ ጥሰቶች እየተበራከቱ መምጣታቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ ለሪፖርተር ገለጸ፡፡

የተሽከርካሪዎች ቁጥር ከፍተኛ በመሆኑ የትራፊክ ሕግ የሚጥሱና ዕርምጃ የሚወሰድባቸው አሽከርካሪዎች ቁጥር እየጨመረ መሆኑን፣ የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ብርሃኑ ኩማ ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡

‹‹የትራፊክ ሕግ ጥሰት በየጊዜው እየጨመረ ነው ያለው፡፡ ይህ የሆነበት ምክንያትም በየቀኑ የሚገባው የተሽከርካሪዎች ቁጥር ከፍተኛ በመሆኑ ነው፡፡ ወደ ኢትዮጵያ የሚገባው የተሽከርካሪዎች ቁጥር በጣም በርካታ ስለሆነ፣ እነዚህ ተሽከርካሪዎች ወደ እንቅስቃሴ ሲገቡ የጥፋት መጠኑ ይጨምራል፤›› ሲሉ አቶ ብርሃኑ ተናግረዋል፡፡

- Advertisement -

በተያዘው በጀት ዓመት በሰባት ወራት ውስጥ በአጠቃላይ የትራፊክ ሕግ ጥሰት ሲፈጽሙ የተገኙ 860,395 አሽከርካሪዎች የብር ቅጣት ዕርምጃ እንደተወሰደባቸው፣ የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተሩ ለሪፖርተር አስረድተዋል፡፡ በትራፊክ ሕግ ጥሰት የብር ቅጣት ዕርምጃ ተወስዶባቸዋል የተባሉ 860,395 አሽከርካሪዎች ቁጥር ከዓምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የዘንድሮው ከፍተኛ እንደሆነም ተገልጿል፡፡

በ2015 በጀት ዓመት በትራፊክ ሕግ ጥሰው የተገኙ አሽከርካሪዎች ቁጥር ከዓምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻፃፀር በስንት እንደሚበልጥ ከሪፖርተር ጥያቄ የቀረበላቸው አቶ ብርሃኑ፣ ቁጥሩን እንደማያስታውሱ ገልጸው፣ ‹‹በእርግጠኝነት ግን የዘንድሮው ከዓምናው የጨመረ ነው፡፡ በዘንድሮው ዓመት በየቀኑ ነው የትራፊክ ሕግ ጥሰት የሚስተዋለው፤›› ብለዋል፡፡

አሽከርካሪዎች በበኩላቸው፣ የትራፊክ ፖሊሶች፣ ‹‹በትንሹም በትልቁም ስህተት ምክንያት በመፈለግ እንደሚቀጧቸው ለሪፖርተር ቅሬታ አቅርበዋል፡፡

አሽከርካሪዎቹ ላነሱት ቅሬታ ማብራሪያ የሰጡት አቶ ብርሃኑ፣ የሕግ ጥሰት ሳይኖር የሚቀጣ ትራፊክ ፖሊስ እንደማይኖር፣ እንዲህ ዓይነት ችግር የገጠማቸው አሽከርካሪዎች መብታቸውን ለማስከበር ለሚመለከተው አካል ማሳወቅ እንደሚችሉ፣ የሕግ ጥሰት በሚፈጽሙ አሽከርካሪዎች ላይ የሚወስደውን የብር ቅጣጥ በተመለከተም፣ ‹‹እኛ ትኩረታችን ገንዘብ ላይ አይደለም፡፡ ከጥፋቱ እንዲማሩ ነው፡፡ ይህን ያህል ለምንድነው ሕግ የሚጥሱት፡፡ ይህን ያህል የሕግ ጥሰት የሚፈጽሙት ሕጉን ሳያውቁ ቀርተው ነው፣ ወይስ አውቀው፣›› ሲሉ ጠይቀው፣ ‹‹እኛ ብሩን አይደለም ትኩረት የምናደርገው፡፡ ዋናው ነገር አሽከርካሪዎች በሥርዓት ሲያሽከረክሩ ተሳፋሪው በሰላም ውሎ እንዲገባ፣ ሰው በሰላም እንዲንቀሳቀስ፣ አንድ እሽከርካሪ ቀበቶ ቢያስር፣ የትራፊክ መብራት ቢያከብር፣ የሚጠቅመው ለራሱ፣ ለአገሩና ለወገኑም ጭምር ነው፡፡ እኛ ከአሽከርካሪዎች ብር ለመልቀም አይደለም የምንቀጣው ሁሉም በሰላም ወጥቶ እንዲገባ ነው፤›› ብለዋል፡፡

አሽከርካሪዎች የደኅንነት ቀበቶ ሳያስሩ፣ ጋቢና የሚቀመጠው ተሳፋሪ ቀበቶ ሳያስርና ከጋቢናው ኋላ የሚቀመጡ ሕፃናትን የደኅንነት መጠበቂያ ሳያደርጉላቸው የተንቀሳቀሱ 45 ሺሕ አሽከርካሪዎችም በቀበቶ የሕግ ጥሰት የብር ቅጣት ዕርምጃ እንደተወሰደባቸው አቶ ብርሃኑ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

የተለያዩ ሪቫን ተሰጥቷቸው ዕቃና መልዕክት እንዲያመላልሱ ፈቃድ ከተሰጣቸው የመሥሪያ ቤት ሞተር ብስክሌቶች ውጪ፣ ሌሎች ሞተር ብስክሌቶች በከተማው መንቀሳቀሳቸው ለስርቆት መስፋፋት ምክንያት መሆኑን ተከትሎ እንዳይንቀሳቀሱ መታገዳቸውን ያስታወሱት የሞተር ብስክሌ አሽከርካሪዎች፣ ‹‹የሞተር ብስክሌት ከሚያሽከረክሩ ሰዎች መካከል በሌብነት የተሰማሩት ትንሽ ናቸው፡፡ ሁሉም በሌብነት ተሰማርቷል ማለት አይቻልም፡፡ ነገር ግን ለድፍን አራት ዓመታት በስርቆት ያልተሳተፉ አሽከርካሪዎች ሁሉ ታግደዋል፡፡ ይህ ደግሞ በኢኮኖሚያዊና በማኅበራዊ እንቅስቃሴ ከፍተኛ አሉታዊ ተፅዕኖ እያሳደረ ይገኛል፤›› ሲሉ ቅሬታቸውን ገልጸዋል፡፡

የታገዱ የሞተር ብስክሌት አሽከርካሪዎችን ቅሬታ በተመለከተም አቶ ብርሃኑ፣ ማብራሪያ የሰጡት ዕግዱ እንዳልተነሳና አስፈላጊ እንደሆነ ነው፡፡

የትራፊክ ሕግ የሚጥሱ አሽከርካሪዎች በ‹‹Point Penalty System››› መሠረት ተደራሽ ተደርገው የጥሰት መጠኑ 17 ሲደርስ መንጃ ፈቃዳቸውን የመንጠቅ ዕርምጃ እንደሚወስድ ኤጀንሲው ከሰኔ 30 ቀን 2014 ዓ.ም. ጀምሮ እንዲቆም መወሰኑን በወቅቱ ገለጾ ነበር፡፡

የመንጃ ፈቃድ ነጠቃው ቢታገድም የቅጣት ዕርምጃው ግን እንደማይቋረጥ የተገለጸ ሲሆን፣ የመንጃ ፈቃድ ነጠቃው እንዲቆም የተደረገው፣ ኤጀንሲው ሊያሻሽላቸው የሚገቡ አሠራሮች ለመፈተሽ እንደነበር በወቅቱ ተገልጿል፡፡ ይሁን እንጂ የመንጃ ፈቃድ ነጠቃ ባለመኖሩ የትራፊክ ሕግ የሚጥሱ አካላት እየተበራከቱ እንደሆነ ተመላክቷል፡፡

የ‹‹Point Penalty›› ዕርምጃ (መንጃ ፈቃድ መንጠቅ) ዕግድ ከሰኔ 30 ቀን ጀምሮ እስካሁን ድረስ እንዳልተነሳም አቶ ብርሃኑ አብራርተዋል፡፡

አዲስ አበበ ከተማ አስተዳደር ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ የሞተር ብስክሌት አሽከርካሪዎች የተገጠመላቸውን ‹‹ጂፒኤስ›› በመንቀል እያስቸገሩ መሆኑን ተከትሎ ‹‹ID›› በመስጠት ማስተካከያ ሊያደርግ መሆኑን አስታውቋል፡፡   

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ በመንግሥት የሚታወጁ ንቅናቄዎችን በተመለከተ ባለቤታቸው ለሚያነሱት ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት እየሞከሩ ነው]

እኔ ምልህ? እ... ዛሬ ደግሞ ምን ልትይ ነው? ንቅናቄዎችን አላበዙባችሁም? የምን ንቅናቄ? በመንግሥት...

የመንግሥት የ2017 ዓ.ም በጀትና የሚነሱ ጥያቄዎች

የ2017 ዓመት የመንግሥት ረቂቅ በጀት ባለፈው ሳምንት መገባደጃ ለሚኒስትሮች...

ከፖለቲካ አባልነትና ከባንክ ድርሻ ነፃ የሆኑ ቦርድ ዳይሬክተሮችን ያካተተው ብሔራዊ ባንክ ያዘጋጃቸው ረቂቅ አዋጅና መመርያዎች

የኢትዮጵያ የብሔራዊ ባንክ የፋይናንስ ተቋማትን የተመለከቱት ድንጋጌዎችንና የባንክ ማቋቋሚያ...

የልምድ ልውውጥ!

እነሆ መንገድ ከቦሌ ሜክሲኮ። አንዱ እኮ ነው፣ ‹‹እንደ ሰሞኑ...