አቶ ግርማ የሺጥላ፣ የብልፅግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ አባልና የአማራ ክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ፣ ከአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ጋር ባደረጉት ቆይታ የተናገሩት፡፡ ልዩ ኃይሉን መልሰን አጠናክረን እናደራጃለን የሚል ዕቅድ ይዘን ስንንቀሳቀስ፣ ልዩ ኃይሉን ለማፍረስ ‹‹መንግሥት ወሰነ የሚል የፖለቲካ ሥራ በስፋት ተሠራጨ፡፡ በዚህ ምክንያት የአማራ ክልል የሥራው ባለቤቶች ሥራው ወደ ክልሉ መጥቶ ሲጀመር በአግባቡ ውይይት ሲደረግ በመሀል ከሥራው ፈጻሚዎች መካከል ‹‹ትጥቅ እንዲያወርድ›› በሚል የመንግሥት መሪዎች ባላወቁት ምክንያት ሾልኮ ወደ ማኅበራዊ ሚዲያ ሲዘዋወር ተመለከትን፡፡ በዚህ በኩል በእጅጉ አዝነናል የሠራዊቱንም የሕዝቡንም ክብር ይነካል፡፡