Sunday, September 24, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
- Advertisement -

ፌርማታ ፅሁፎች

‹‹የጅብ ችኩል ቀንድ ይነክስ››

ትኩስ ፅሁፎች

አንድ ኩባንያ ገቢው ቀንሶ ከባድ ኪሳራ ላይ ከመውደቁ በፊት ሠራተኛውን መቀነስ ሲፈልግ አንዱን ጃቡሳ የሆነ ምሕረት የለሽ ጨካኝ ሰው መርጦ በኃላፊነት ይሾምና ‹‹ሰነፍ ወይም ዋልጌ ይለዋል፡፡ ያም ጃቡሳ የሆነ አሠሪ (ካቦ) ያለምንም ርኅራኄ ሴቱንም ወንዱንም ሠራተኛ በቁጥጥር ብዛት ወጥሮ በማስጨነቅ እየመዘዘ ሲያወጣ ሳለ አንድ የሌላ ካምፓኒ ሠራተኛ የሆነ ሰው ጓደኞቹን ለመጠየቅ ድንገት መጥቶ በእንግዶች መቀበያው ሳሎን ሲንጐራደድ አየው፡፡ የዚያው ኩባንያ ሠራተኛ መሰሎት ያለ ጃቡሳ አሠሪ ‹‹አንተ ስምህ ማን ነው?›› ሲለው ‹‹እከሌ እባላለሁ›› አለው፡፡ ‹‹ደመወዝህ ስንት ነው?›› ባለውም ጊዜ ‹‹2,500 ዶላር ነው›› ሲለው እዚያው ባፋጣኝ ቀደም ብሎ በተዘጋጀ የደብዳቤ ፎርም ላይ ስሙን ሞልቶ ፈርሞበት የሦስት ወር ሥራ መፈለጊያ የ7,000 ዶለር ቼክ ጽፎ ሰጠውና ‹‹ወደ ቤትህ ሂድ ከዛሬ ጀምሮ ከዚህ ኩባንያ ተሰናብተሃል›› ብሎ ሸኘው፡፡ ‹‹የጅብ ችኩል ቀንድ ይነክስ፡፡››

  • መክብብ አጥናው ‹‹ሁለገብ የአእምሮ ማዝናኛ›› (2005)
- Advertisement -
- Advertisement -

ተጨማሪ ለማንበብ

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች