Wednesday, September 27, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትፓርላማው የግሉ ዘርፍ ወደ አትሌቲክስ እንዲገባ መጋበዝ እንደሚገባው ጠቆመ

ፓርላማው የግሉ ዘርፍ ወደ አትሌቲክስ እንዲገባ መጋበዝ እንደሚገባው ጠቆመ

ቀን:

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጤና፣ የማኅበራዊ ልማት ባህልና ስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የግሉ ዘርፍ ወደ አትሌቲክስ እንዲገባ መጋበዝ እንደሚገባ አሳስቧል፡፡ ቋሚ ኮሚቴው መጋቢት 29 ቀን 2015 ዓ.ም. በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ጽሕፈት ቤት ተገኝቶ የመስክ ምልከታ ያደረገ ሲሆን በተለያዩ ጉዳዮች ላይ መክሯል፡፡

በዚህም መሠረት ፌዴሬሽኑ እየሠራ ያለውን ታዳጊና ተተኪ አትሌቶችን የማፍራት ሥራውን አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ያነሳ ሲሆን፣ ከታች ጀምሮ ፍትሐዊ በሆነ መልኩ ተተኪ አትሌቶችን ማፍራት ላይ ሁሉም ትኩረት ሰጥቶ መሥራት እንደሚገባው የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ ወ/ሮ ወርቅሰሙ ማሞ ተናግረዋል፡፡

በውይይቱ ወቅት ከተነሱ ጉዳዮች መካከል፣ ፌዴሬሽኑ ግልጽ የሆነ አሠራርና አደረጃጀት በመሥራት ዕቅዱን እያሳካ መሆኑን በጥንካሬ ተጠቅሶ፣ በቂ የመለማመጃ ቦታ አለመኖር አትሌቲክሱን እየፈተነ እንደሚገኝም ተነስቷል፡፡

በወቅቱ ለተነሱ ችግሮች መፍትሔ ለማፈላለግ ቋሚ ኮሚቴው ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እንደሚነጋገርና አስፈላጊ ድጋፎችን እንደሚያደርግ ገልጿል።

ከዚህም ባሻገር በአትሌቲክሱ የግሉ ዘርፍ እንዲሳተፍ የግንዛቤ ማስጨበጫ መስጠትና ሁሉም የበኩሉን መወጣት እንደሚገባው የቋሚ ኮሚቴው ምክትል ሰብሳቢ ከይረዲን ተዘራ (ዶ/ር) አስታውሰዋል፡፡ 

የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉና ሌሎችም የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት በኢትዮጵያ አትሌቲክስን በማስፋፋት ተተኪ አትሌቶችን በብዛትና በጥራት በማፍራት በአኅጉርና በዓለም አቀፍ መድረኮች የአገርን ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት ለማሳደግ እንደሚሠሩ ተናግረዋል፡፡

የስፖርቱ ዘርፍ በተለይ አትሌቲክሱ ለአገር ኢኮኖሚ ያለው ጠቀሜታ ትልቅ በመሆኑ በዘርፉ የተሻለ ውጤት ለማምጣት ፌዴሬሽኑ ብቻ ሳይሆን፣ ሁሉም በየደረጃው ያሉ የሚመለከታቸው አካላት ድጋፍ ማድረግ እንዳለባቸው ተነስቷል፡፡

በሌላ በኩል ቋሚ ኮሚቴው ከኢትዮጵያ ፀረ አበረታች ቅመሞች ባለሥልጣን ጋር ውይይት ያደረገ ሲሆን በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተመካክረዋል፡፡

የኢትዮጵያ ፀረ አበረታች ቅመሞች ባለሥልጣን ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ በተሰጠው ሥልጣንና ኃላፊነት የሠራቸውን ተግባራትና እያጋጠሙት ያሉ ተግዳሮቶችን ለቋሚ ኮሚቴው አቅርቧል።

ፀረ አበረታች ቅመሞችን በተመለከተ በመደበኛ ትምህርት ከአምስተኛ ክፍል ጀምሮ ላሉ ተማሪዎች እንዲሰጥና በስፖርታዊ ሥልጠናዎች ማንዋል ላይ እንዲካተት ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር መሥራቱንና 4,007 አትሌቶችን መመርመሩን ገልጿል።

ግንዛቤን ለማስፋት የአትሌቶች፣ የስፖርት ባለሙያዎችና የሚዲያ ፎረሞችን በማቋቋም እየሠራ እንደሚገኝ አስረድቷል፡፡

ባለሥልጣኑ ሥራውን በተሳለጠ መልኩ ለማከናወን የበጀት እጥረት፣ የሠራተኛ ቅጥር ክልከላ፣ የውጭ ምንዛሪ እጥረትና በኢትዮጵያ የፀረ ዶፒንግ ላቦራቶሪ አለመኖር እንቅፋት እንደሆነበት የጠቆመ ሲሆን፣ ችግሮቹ በአገር ውስጥ ብቻ ሳይሆን በዓለም አቀፉ ፀረ አበረታች ቅመሞች ተቋም (ዋዳ) ድጋፍ ጭምር የሚቀረፉ መሆናቸውን ገልጿል።

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የአማራ ክልል ወቅታዊ ሁኔታ

እሑድ ጠዋት መስከረም 13 ቀን 2016 ዓ.ም. የፋኖ ታጣቂዎች...

ብሔራዊ ባንክ ለተመረጡ አልሚዎች የውጭ አካውንት እንዲከፍቱ ለመጀመሪያ ጊዜ የፈቀደበት መመርያና ዝርዝሮቹ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪ አጠቃቀምንና ተያያዥነት ያላቸው ጉዳዮችን...

እነ ሰበብ ደርዳሪዎች!

ከሜክሲኮ ወደ ዓለም ባንክ ልንጓዝ ነው። ሾፌርና ወያላ ጎማ...