Wednesday, September 27, 2023
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

ማሽነሪዎችን ከካተርፒላር የሚቀበለው ብቸኛው ቀርጫንሸ ግሩፕ 2.5 ቢሊዮን ገቢ ለማግኘት ማቀዱን ገለጸ

ተዛማጅ ፅሁፎች

የማሽነሪ ዕቃዎችን ከካተርፒላር ለመቀበል ሙሉ ዕውቅና አግኝቻለሁ ያለው ቀርጫንሸ ቡና ላኪ ቡድን በአንድ ዓመት ውስጥ 2.5 ቢሊዮን ገቢ ለመሰብሰብ ማቀዱን ገለጸ፡፡

ቀርጫንሸ ቡና ላኪ ቡድን ዓርብ መጋቢት 29 ቀን 2015 ዓ.ም. በስካይ ላይት ሆቴል በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ፣ ከካተርፒላር ማሽነሪዎችን ለመቀበል ብቸኛው ቡድን የመሆን ዕድል እንዳገኘ አስታውቋል፡፡

በጋዜጣዊ መግለጫው ተገኝተው ማብራሪያ የሰጡ የቀርጫንሸ ቡና ላኪ ቡድን ሥራ አስኪያጅ አቶ እስራኤል ደገፉ፣ በአንድ ዓመት ውስጥ ምን ያህል ገቢ ለማግኘት እንደታቀደ ከሪፖርተር ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ ሲሰጡ፣ ‹‹በአንድ ዓመት ውስጥ 2.5 ቢሊዮን ብር ገቢ ለመሰብሰብ አቅደናል፤›› ብለዋል፡፡

ቀርጫንሸ በኢትዮጵያ ዕውቅና ያገኘ ብቸኛው ካተርፒላር መሆኑ በጋዜጣዊ መግለጫው የተነገረ ሲሆን፣ የካተርፒላር ማሽነሪ አስመጪ በመሆን ሥራውን እያቀላጠፈ እንደሚገኝ አብራርቷል፡፡

የቀርጫንሸ ቡና ላኪ ቡድን ሥራ አስኪያጅ አቶ እስራኤል፣ ቀርጫንሸ የካተርፒላር ማሽነሪዎችን ለማምጣት ብቸኛ ሕጋዊ ፈቃድ ማግኘት የቻለው፣ የኢትዮጵያ ዓባይ ግድብን ጨምሮ በርካታ ፕሮጀክቶች በማሽነሪ ብልሽት እንደቆሙ በመገንዘብና ችግሩን ለመቅረፍ አልሞ በመነሳቱ መሆኑን ለሪፖተር ገልጸዋል፡፡

ቀርጫንሸ ኢኪውፕመንት በአገር ውስጥ ምንዛሪ የካተርፒላርን ምርቶች በማቅረብ፣ በኢትዮጵያ የሚስተዋለውን የማሽነሪ ክፍተት ለመሙላት የሚችልና ለሚያቀርባቸው ምርቶችም ሕጋዊ ዋስትና የሚሰጠው ብቸኛ ድርጅት መሆኑም በመርሐ ግብሩ ተብራርቷል፡፡

እንደ ገለጻው ከሆነ፣ ቀርጫንሸ ኢኪውፕመንት መቀመጫውን ዱባይ ካደረገውና የካተርፒላር ማሽነሪ አቅራቢዎች ከሆነው ከኡና ትራክ ጋር በመሆን፣ የካተርፒላር የግንባታና ሌሎች ማሽነሪዎችን ወደ ኢትዮጵያ ከማስገባት ባሻገር፣ ልምድ ያላቸው ባለሙያዎች በማደራጀት ማሽኖች ሲበላሹ በፍጥነት ጥገና እንዲያገኙ የማድረግ ሥራ እንደሚሠራም አቶ እስራኤል ገልጸዋል፡፡

በጋዜጣዊ መግለጫው የተገኙ የቀርጫንሸ ኢኪውፕመንት ሥራ አስኪያጅ ሚስተር አቶ ኒኮላስ መረር፣ ቀርጫንሸ ቡና ላኪ ቡድን የካተርፒላር ማሽነሪዎችን ተቀብሎ ወደ ኢትዮጵያ በማስገባት ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወት አብራርተዋል፡፡

‹‹የአገራችን ልማት እጅግ ወደኋላ የሚጎተትበት ሒደት ነው ያለው፤›› ያሉት አቶ እስራኤል፣ ‹‹እኛ ማሽነሪውን ለማስገባት የመረጥነው በዓለም አቀፍ ደረጃ ትልቁን ማሽነሪ ነው፡፡ ይህ ማሽነሪ ደግሞ ለአገራችን ዕድገት እጅግ አስፈላጊና ወሳኝ ሚና ይጫወታል፡፡ ቶሎ የሚበላሽና ቶሎ የሚሰበር አይደለም፡፡ ከተሰበረም ደግም ወይም ጥገና የሚያስፈልግበት ጊዜ ካለ በአቅራቢያው የጥገና አገልግሎት ለመስጠት እንገኛለን፡፡ ማሽነሪዎች ፕሮጀክቱ ባለበት ሳይነሱ አገልግሎት እንሰጣለን፤›› ሲሉ አብራርተዋል፡፡

በአገሪቱ የሚስተዋለው ትልቁ ችግር የውኃ መስኖ፣ የመንገድ ፕሮጀክት መሆኑን የጠቀሱት አቶ አስራኤል፣ እነዚህን ማሽነሪዎች ማስገባቱ ኢትዮጵያ ለምታደርገው የዕድገት ጎዳና ትልቅ ሚና እንደሚጫወት ተናግረዋል፡፡

ማሽነሪው የኢትዮጵያን ችግር ስንት በመቶ ይደፍናል? ተብሎ እንደታቀደ ከሪፖርተር ጥያቄ የቀረበላቸው አቶ እስራኤል፣ ‹‹በማርኬቲንግ ሼር ረገድ ካተርፒላር ከ50 በመቶ በላይ የኢትዮጵያን የማርኬት ሼር ይወስዳል፡፡ ምክንያቱም ከጥንትም ጀምሮ ይታወቃል፡፡ ኢትዮጵያ ስትጠቀምባቸው የነበሩ ማሽነሪዎች ናቸው፡፡ ከዚያ አኳያ ከጊዜ ወዲህ ደግሞ በተለያዩ ችግሮች ምክንያት ማሽነሪ ማግኘት ስላልተቻለ ሌሎች ርካሽ ማሽነሪዎችን ለማምጣት ግድ ብሎ ነበር፡፡ ሌሎች ማሽኖች ነዳጅ ይበላሉ፡፡ ካተርፒላር ማሽነሪ ግን ነዳጅ አይበላም፡፡ ይህ ትልቅ ጥቅም አለው ብለዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች