Tuesday, September 26, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናበቴክኖሎጂ የተደገፈ ትምህርት ለመስጠት የዲጂታል ትምህርት ስትራቴጂ እየተነደፈ መሆኑ ተገለጸ

በቴክኖሎጂ የተደገፈ ትምህርት ለመስጠት የዲጂታል ትምህርት ስትራቴጂ እየተነደፈ መሆኑ ተገለጸ

ቀን:

በአበበ ፍቅር

ትምህርትን በዲጂታል ቴክኖሎጂ ተደራሽ ለማድረግ የዲጂታል ትምህርት ስትራቴጂ እየተነደፈ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ህዋዌ ቴክኖሎጂ መጋቢት 29 ቀን 2015 ዓ.ም. በዲጂታል ትራንስፎርሜሽንና በአይሲቲ ልማት ላይ በሐያት ሪጀንስ ሆቴል ባዘጋጀው የውይይት መድረክ፣ ዲጂታል ቴክኖሎጂ የመማር ማስተማር ሒደቱን በአዳዲስ አሠራሮች እየቀየረው ይገኛል ሲሉ የአይሲቲና ዲጂታል ትምህርት ዋና ሥራ አስኪያጅ ዘላለም አሰፋ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡

ለዚህም ህዋዌ ቴክኖሎጂ በተለይም በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የአይሲቲ አካዴሚ ለመክፈት መወሰኑ ብዙ የአይሲቲ ባለሙያዎችን ለማፍራት እንደሚያስችላቸው አቶ ዘላለም ተናግረዋል፡፡

የትምህርት ዘርፉ በቴክኖሎጂ የታገዘ መሆኑ ተማሪዎች ዓለም አቀፋዊ ዕውቀትን እንዲያገኙ ከማድረጉም ባሻገር፣ ከሌሎች የዓለም ባለሙያዎች ጋር እንዲግባቡ ያደርጋቸዋል ብለዋል፡፡

ህዋዌ ቴክኖሎጂ ዘመናዊና በቴክኖሎጂ የታገዙ ክፍሎችን በመገንባት ለተማሪዎች ሳይንሳዊ ምርምር የሚያደርጉበትና ተሰጥኦዋቸውን የሚያዳብሩበትን ሁኔታ እያመቻቸ እንደሆነ፣ የህዋዌ ኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ቢዝነስ ግሩፕ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሚስተር ኮዊን ካኦ ተናግረዋል፡፡

ኩባንያው በዓለም ዙሪያ ካሉ መንግሥታትና የትምህርት ተቋማት ጋር በቅርበት በመሥራት የመማር ማስተማር ሒደቱን የሚያሻሽሉ አዳዲስ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን ለማቅረብ እየሠራ መሆኑን ሥራ አስኪያጁ አክለዋል፡፡

በሌላ በኩል ኩባንያው ለትምህርት ማዕከላት ግንባታ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ መሆኑን የተናገሩት የደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት አነጋግረኝ ጋሻው (ዶ/ር) ናቸው፡፡ በድርጅቱ በኩል ማሳያ ይሆን ዘንድ በዩኒቨርሲቲው የመረጃ ማዕከል ተገንብቶ መጠናቀቁን ተናግረዋል፡፡

ህዋዌ በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ አካዴሚ ከፍቶ ለተማሪዎች ጥገናዎችን ጭምር እያስተማረ እንደሆነ የተናገሩት ደግሞ የአርባ ምንጭ ዩንቨርሲቲ የአይሲቲ ዳይሬክተር የሆኑት መምህር ዳንኤል ታደሰ ናቸው፡፡

ከሌሎች ካምፓኒዎች የሚያገኟቸው አገልግሎቶች በጣም ውድ ከመሆናቸውም በላይ፣ በቂ አገልግሎቶችን አይሰጡም ህዋዌ ቴክኖሎጂ በአንጻሩ ቀልጣፋ አገልግሎትን ከመስጠቱም ባሻገር፣ የጥገና አገልግሎት ጭምር እንደሚሰጥ መምህር ዳንኤል ተናግረዋል፡፡

ሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች በሚባል ደረጃ የመማር ማስተማር ሒደቱን ወደ ዲጂታል ስላመጡት ቴክኖሎጂውን መጠቀም የሚበረታታና ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ተግባር ነው ብለዋል፡፡

ለአብነትም በኮቪድ 19 ወቅት ትምህርቱን ለተማሪዎች በርቀት ለማድረስ ቴክኖሎጂ የነበረው ፋይዳ ከፍተኛ ነበር ብለዋል፡፡

ይህንን ተሞክሮ በመውሰድና በማዳበር ህዋዌ ቴክኖሎጂ ያመጣቸው ቴክኖሎጂዎች የመማር ማስተማር ሒደቱን ቀላልና ምቹ ከማድረጋቸው በተጨማሪ፣ ተማሪዎች ጥሩ ዕውቀትን እንዲያገኙና ብቁ ሆነው እንዲገኙ ያስችላቸዋል ብለዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የቤት ባለንብረቶች የሚከፍሉትን ዓመታዊ የንብረት ታክስ የሚተምን ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጀ

በአዋጁ መሥፈርት መሠረት የክልልና የከተማ አስተዳደሮች የንብረት ታክስ መጠን...

እንደ ንብረት ታክስ ያሉ ወጪን የሚያስከትሉ አዋጆች ከማኅበረሰብ ጋር ምክክርን ይሻሉ!

የመንግሥትን ገቢ በማሳደግ ረገድ አስተዋጽኦ እንዳላቸው የሚታመኑት የተጨማሪ እሴት...

ለዓለምም ለኢትዮጵያም ሰላም እንታገል

በበቀለ ሹሜ ያለፉት ሁለት የዓለም ጦርነቶች በአያሌው የኃያል ነን ባይ...