የዓባይ ውኃ ጉዳይ ተመራማሪና የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰር ያዕቆብ አርሳኖ (ዶ/ር) ለኢፕኤ የተናገሩት፡፡ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የተጀመረበት 12ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ ቃለ ምልልስ ያደረጉት ፕሮፌሰሩ፣ የዓባይ ተፋሰስ አገሮች በውኃ ሀብቱ አብረው ሲጠቀሙ ዘላቂ መፍትሔም ሊመጣ ይችላል፡፡ ለዚህም በተቻለ መጠን ስትራቴጂ ዘርግተው ለጋራ ጥቅም በጋራ መምከር ያስፈልጋቸዋል ብለዋል፡፡
የጋራ ሕግና የጋራ አስተዳደር ደግሞ በስምምነት የሚደረግ እንጂ፣ አንዱ አገር ‹‹ይኸውላችሁ ሕግ ሠርቻለሁ፣ እናንተንም ይገዛል፤›› ብሎ ማስገደድ እንደማይችልም አክለዋል፡፡