Tuesday, September 26, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
- Advertisement -

ፌርማታ ፅሁፎች

‹‹ክስተቱን አስታውሼዋለሁኝ! አንተን ግን አላስታወስኩህም››

ትኩስ ፅሁፎች

ወጣቱ አዛውንቱን ጠየቃቸው

“ያስታውሱኛል ጌታዬ?”

“ኧረ በጭራሽ” መለሱ ሽማግሌው

ወጣቱ የሽማግሌው የቀድሞ ተማሪ እንደነበር እና የትኛው የትምህርት አይነት እንዳስተማሩት ነገራቸው

ሽማግሌውም “ታዲያ ምን እየሰራህ ነው አሁን?” ሲሉ ጠየቁት

“አሁን አስተማሪ ነኝ ጌታዬ! አስተማሪ እንድሆን ያደረጉም ደግሞ እርስዎ ኖት”

ሽማግሌው ተገረሙ! በየትኛው የትምህርት ዘርፍ ምሳሌ ሆነውት አስተማሪ እንዲሆን ተፅእኖ እንዳሳደሩበት ጠየቁት

ወጣቱ ቀጠለ “ከእለታት በአንዱ ቀን አንደኛው የክፍል ጏደኛዬ የሚያምር ሰአት ይዞ መጣ:: እኔም ሰአቱን በጣም ወደድኩት! ወድጄውም አልቀረሁም ፈለግኩት ከዚያም ጭር ሲል ጠብቄ ከሻንጣው ውስጥ ሰረቅኩት”

“ልጁም ወዲያው ለእርስዎ ሰአቱ እንደጠፋበት አመለከተ:: ከዚያም እርስዎ ሰብስበውን ‘የዚህን ተማሪ ሰአት የሰረቀ ሰው አሁኑኑ ይመልስ’ ሲሉ አስጠነቀቁ:: እኔ ግን መመለስ አልፈለግኩም”

“ከዚያስ” ጠየቁ ሽማግሌው

“ከዚያማ የክፍሉን በር ዘግተው የሁላችንንም ኪስ ተራ በተራ እንደሚፈትሹ ነገሩን:: በተጨማሪም ሁላችንም አይናችንን እንድንጨፍን አስጠነቀቁን! ሁላችንም ጨፍነን እርስዎ ኪሳችንን መፈተሽ ጀመሩ”

“ከዚያስ?”

 

“አይናችንን ጨፍነን ሲፈትሹ እኔ ኪስ ውስጥ አገኙት ግን ፍተሻዎትን አላቆሙም:: ሁሉንም ፈትሸው ሲጨርሱ ‘አሁን አይናችሁን ክፈቱ ሰአቱ ተገኝቷል’ አሉን”

ለማንም አልነገሩብኝም

ቅጣትም አልቀጡኝም

እኔንም ጠርተው አላናገሩኝም – በቃ ዝም አሉኝ እና ሰአቱን ለተማሪው መለሱለት

“የዚያን ቀን በህይወቴ ሌባ: ዘራፊ እና መጥፎ ሰው እንደማልሆን ወሰንኩኝ!! ለማንም አሳልፈው አልሰጡኝም – ይህ ደግሞ ልቤን ለውጦት አስተማሪ ለመሆን አስወሰነኝ” ሲል ተናዘዘ

ሽማግሌው በጥሞና መስማታቸውን ቀጠሉ

“መምህር ሆይ አስታወሱኝ አሁን?” ጠየቀ ወጣቱ

“ክስተቱን አስታውሼዋለሁኝ! አንተን ግን አላስታወስኩህም ምክንያቱም ልክ እናንተ አይናችሁን እንደጨፈናችሁት ሁሉ እኔም አይኔን ጨፍኜ ነበር ስፈትሻችሁ የነበረው:: ስለዚህ ሰአቱን ማግኘቴ ላይ እንጂ ማንነት ላይ አልነበረምና ትኩረቴ አንተ መሆንህን አላወቅኩም” ብለው መለሱለት።

  • ዘመላክ እንድርያስ
- Advertisement -
- Advertisement -

ተጨማሪ ለማንበብ

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች