Tuesday, September 26, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊስድስት ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች ለመጨረሻው የሁዋዌ የአይሲቲ ዓመታዊ ውድድር አለፉ

ስድስት ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች ለመጨረሻው የሁዋዌ የአይሲቲ ዓመታዊ ውድድር አለፉ

ቀን:

ሁዋዌ ባዘጋጀው የኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ ውድድር ስድስት ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች በቻይና ለሚካሄደው የመጨረሻው ዓለም አቀፍ ውድድር ማለፋቸው ተገለጸ፡፡

ስድስቱ ተማሪዎች ከጎንደር ዩኒቨርሲቲ፣ ከዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ፣ ከአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲና ከአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ መሆናቸውንም ሁዋዌ አስታውቋል፡፡

የሁዋዌ ኢትዮጵያ ሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ሚስተር ሊሚንግ የ፣ የሁዋዌ የኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ ውድድር በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚገኙ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የሚወዳደሩበትና ሐሳብ የሚለዋወጡበትን መደላድል የሚፈጥር መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ከዚህ ቀደም በተደረጉ ተከታታይ ውድድሮች ያሸናፉ 15 የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የመጨረሻውን ቀጣናዊ ውድድር መጋቢት 13 ቀን 2015 ዓ.ም. ኢትዮጵያ በሚገኘው የሁዋዌ ዋና መሥሪያ ቤት ያደረጉ ሲሆን፣ ውድድሩም ስድስት ሰዓታትን የፈጀ ነበር ተብሏል፡፡

በበይነ መረብ የተደረገው ፈተናም በኔትዎርክ፣ በክላውድና በኮምፒዩቲንግ ዘርፎች እንደነበር የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊው አስታውሰዋል፡፡    

ሁዋዌ በኢትዮጵያ አይሲቲ ችሎታ (ታለንት) እና ኢኖቬሽን ሥነ ምኅዳርን ለማሳደግ ለሚያዘጋጀው ዓመታዊ የበይነ መረብ የሁዋዌ የኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ (አይሲቲ) ውድድር፣ 15 ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች ከዚህ ቀደም ማለፋቸው ይታወሳል፡፡

ከ30 በላይ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎችና ኮሌጆች የተውጣጡ ከ1,500 በላይ ተማሪዎች የመጀመርያውን የአይሲቲ ውድድር በበይነ መረብ ያደረጉ ሲሆን፣ ከእነዚህም መካከል 63 ተማሪዎች ወደ ቀጣዩ አገር አቀፍ ውድድር አልፈው ነበር፡፡

እንደ ሁዋዌ ሕዝብ ግንኙነት ክፍል መረጃ፣ ታኅሣሥ 18 ቀን 2015 ዓ.ም. 63 ተማሪዎች ሁለተኛውን አገር አቀፍ ውድድር ያደረጉ ሲሆን፣ ከእነዚህ ውስጥ 15 ተማሪዎች በቀጣይ በሚካሄደውና ኢትዮጵያ፣ ጋቦን፣ ሴኔጋል፣ ኒጀር፣ ጋምቢያ፣ ካሜሩን፣ ግብፅ፣ ሞሮኮና ቱኒዚያን ጨምሮ 20 የአፍሪካ አገሮች በሚሳተፉበት ቀጣናዊ የአይሲቲ ውድድር ላይ ተሳትፈዋል፡፡

ሁዋዌና ትምህርት ሚኒስቴር በመተባበር ባዘጋጁት አምስተኛው ዙር ዓመታዊ አገር አቀፍ ውድድር የተሳተፉት ተማሪዎች፣ ከኮምፒዩተር ኢንጂነሪንግ፣ ከኮምፒዩተር ሳይንስ፣ ከሶፍትዌር ኢንጂነሪንግ፣ ከኮሚዩኒኬሽን ኢንጂነሪንግና ከአይሲቲ ትምህርት ክፍሎች የተውጣጡ ተማሪዎች ናቸው።

የሁዋዌ አይሲቲ ዓለም አቀፍ ውድድር እ.ኤ.አ. በ2015 የተጀመረ ሲሆን፣ በስድስተኛው ዓለም አቀፍ ውድድር ከ2,000 በላይ ዩኒቨርሲቲዎችና ኮሌጆች፣ በ85 አገሮችና በሁዋዌ ቀጣናዎች የሚገኙ 150,000 ተማሪዎች የተሳተፉበት ነበር፡፡ በኢትዮጵያ ደግሞ ከ2019 ጀምሮ በየዓመቱ እየተካሄደ ይገኛል።

የሁዋዌ አይሲቲ ውድድር በዓለም አቀፍ ደረጃ በሁዋዌ አይሲቲ አካዴሚዎችና በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ውስጥ የአይሲቲ አካዴሚውን መቀላቀል ለሚፈልጉና ለተቀላቀሉ ተማሪዎች የሚዘጋጅ ነው።

ውድድሩም፣ ለዓለም አቀፍ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የሚዘጋጅ፣ የአይሲቲ ታለንት ሥነ ምኅዳር ጤናማ ዕድገትን የሚያበረታታና የኢንዱስትሪና ትምህርት ውህደትን የሚደግፍ መሆኑንም የሕዝብ ግንኙነት ክፍሉ አሳውቋል፡፡

የሁዋዌ አይሲቲ ግሎባል የመጨረሻ ውድድር አሸናፊዎች ኅዳር 02 ቀን 2015 ዓ.ም የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) በተገኙበት ዕውቅና ማግኘታቸውና የዘንድሮው ሰባተኛ ዙር ውድድር በይፋ መጀመሩ ይታወሳል፡፡

ኢትዮጵያን ጨምሮ ከ170 በላይ አገሮች ውስጥ በኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሼን ቴክኖሎጂ ዘርፍ እየሠራ የሚገኘው ሁዋዌ፣ ሰሞኑን ይፋ ባደረገው የ2022 ዓመታዊ ሪፖርት፣ 642.3 ቢሊዮን የን ማግኘቱንና ከዚህ ውስጥ 36.6 ቢሊዮን የን ማትረፉን አስታውቋል፡፡

ኢንቨስትመንቱን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ያስታወሰው ድርጅቱ፣ እ.ኤ.አ. 2022 ፈታኝ ውጫዊ ጫናዎች ያጠሉበትና ከገበያ ጋር ያልተያያዙ ችግሮች የገጠሙበት እንደነበር አስታውሷል፡፡

እ.ኤ.አ. በ1987 የተመሠረተውና በኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽንና በስማርት ቴክኖሎጂ ዘርፍ የተሠማራው ሁዋዌ፣ 207 ሺሕ ሠራተኞች ያሉት ሲሆን፣ በዓለም ከሦስት ቢሊዮን በላይ ተጠቃሚዎችን እያገለገለ መሆኑን በሪፖርቱ ጠቅሷል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የቤት ባለንብረቶች የሚከፍሉትን ዓመታዊ የንብረት ታክስ የሚተምን ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጀ

በአዋጁ መሥፈርት መሠረት የክልልና የከተማ አስተዳደሮች የንብረት ታክስ መጠን...

እንደ ንብረት ታክስ ያሉ ወጪን የሚያስከትሉ አዋጆች ከማኅበረሰብ ጋር ምክክርን ይሻሉ!

የመንግሥትን ገቢ በማሳደግ ረገድ አስተዋጽኦ እንዳላቸው የሚታመኑት የተጨማሪ እሴት...

ለዓለምም ለኢትዮጵያም ሰላም እንታገል

በበቀለ ሹሜ ያለፉት ሁለት የዓለም ጦርነቶች በአያሌው የኃያል ነን ባይ...