Sunday, September 24, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
- Advertisement -

ፌርማታ ፅሁፎች

ተፈጥሯዊው መምህር

ትኩስ ፅሁፎች

ችግር ተፈጥሮአዊ መምህር ነው፡፡ ችግር የታላቅ ሕይወት በር ነው፡፡ አሁን በትምህርት ቤት የምንማረው ትምህርት ሰዎች እነሱ የደረሱበትን የትምህርት ደረጃ ለመድረስ ያዘጋጀልን ፈለግ ነው፡፡ አንድ ሰው የሄደበትን ፈለግ መከተል ደግሞ የሚያደርሰው እሱ የደረሰበት ደረጃ ብቻ ነው፡፡ የተለየ ነገር ለመሥራት ችግሮችን በተለየ አንግል (አቅጣጫ) መመልከት ይኖርብናል፡፡ ስለዚህ ችግር ሲደርስብን ወይም ስንመለከት የአመለካከት አቅጣጫችን በተለየ መለኩ መሆን ይኖርበታል፡፡

 በዚህ ዓለም ትልቅ የምንላቸው ሰዎች ብዙኃኑን የተከተሉ ሳይሆን የራሳቸውን አቅጣጫ የተከተሉ ናቸው፡፡ ብዙኃኑን መከተል ተራ ሰው ከማድረግ ውጪ የትም አያደርስም፡፡ የተለየ ሰው ለመሆን የተለየ አመለካከት ሊኖረን ይገባል፡፡ የተለየ ሰው ማለት የተለየ ስም መያዝ ሳይሆን የተለየ አስተሳሰብና የራሳችን የግላችን የሆነ አቋም መያዝ ማለት ነው፡፡ ከስማችን ውጭ የተለየ መግለፅ የምንችለው ነገር ሊኖረን ይገባል፡፡

ከስማችን ውጭ የግላችን የምንለው የተለየ ልንጠራበት የምንችለው ነገር ሊኖረን ይገባል፡፡ ከሌላው ሰው የምንለየው በስማችን ብቻ መሆን የለበትም፡፡ የተለየን ሰዎች ነን ለማለት የተለየ የአስተሳሰብና የአመለካከት እውቀት ሊኖረን ይገባል፡፡ አንድ የተለየ ነገር ሊያስጠራን የሚችል ነገርም መሥራት ይኖርብናል፡፡ ሰዎች የምንለያየውና ከፍና ዝቅ ብለን የምንታየው በሥራችን ነውና፡፡ እስኪ ስለራሳችሁ አውሩ ብትባሉ ምን ያህል ደቂቃ ማውራት ትችላላችሁ? ልጆቻችሁ ስለናንተ ቢጠይቁ ደግሞ የሚያወሩት እናንተ ስለራሳችሁ ከምታወሩት ባነሰ ነው፡፡ ጠቅላላ አያውቅዋችሁም ማለት ነው፡፡ የተለየ ነገር ከሌላችሁ ማለቴ ነው፡፡

  • አብርሃም ሐዱሽ “ነገር በምሳሌ…” (2005)
- Advertisement -
- Advertisement -

ተጨማሪ ለማንበብ

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች