በአዲስ አበባ ከተማ ሕዝብን በማመላለስ የትራንስፖርት አገልግሎት በመስጠት በቀዳሚነት የሚጠቀሰው የአንበሳ አውቶቡስ ነው፡፡ በዘመነ ደርግ (1967 ዓ.ም.) ከመወረሱ በፊት በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ በጎ አድራጎት ድርጅት ባለቤትነት ይተዳደር ነበር፡፡ ከግማሽ ምዕት ዓመት በፊት ከነበሩት አውቶቡሶች አንዱ፣ በአራት ኪሎ ሚያዝያ 27 አደባባይ የሚገኘውን የድል ሐውልትን ሲያልፍ የሚታየው (ፎቶ) ነው፡፡ በምሥራቅ በኩል የሚታየው ሕንፃ በ1954 ዓ.ም. ሥራውን የጀመረው የጀርመን ባህል ተቋም (ጎተ) የመጀመርያው ቢሮው ሲሆን፣ በምዕራብ በኩል የሚገኘው የያኔው የትምህርትና ሥነ ጥበብ ሚኒስቴር (አሁን የትምህርት ሚኒስቴር) ሕንፃ ነው፡፡