Sunday, September 24, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዝንቅለአፍሪካ ችግር አፍሪካዊ መፍትሔ

ለአፍሪካ ችግር አፍሪካዊ መፍትሔ

ቀን:

የተባበረች አፍሪካን ዕውን ለማድረግ ከፖለቲካዊ ተቋሙ (የአፍሪካ ኅብረት) በተጨማሪ የሚከተሉት ስድስት አኅጉራዊ ተቋማት በፍጥነት ማቋቋም፣ የተቋቋሙም ካሉ ማጠናከር ያስፈልጋል።

  1. ለጤናው ዘርፍ በአፍሪካ ኅብረት ሥር የአፍሪካ ጤና ተቋም ማቋቋም (የአፍሪካ ሲዲሲ)፤ በኢትዮጵያ ጠንሳሽነት የአፍሪካ ሲዲሲ ተቋቁሟል፣ ዋናው ጽሕፈት ቤት አዲስ አበባ ላይ በመገንባት ላይ ይገኛል። ማጠናከር ግን ያስፈልጋል፡፡
  2. ለተፈጥሮም ሆነ ሰው ሠራሽ አደጋ፣ አኅጉራዊ ምላሽ የሚሰጥ በኅብረቱ ሥር አንድ ተቋም (African Emergency Management Agency) ያስፈልጋል። ኬንያው ለኢትዮጵያ፣ ኢትዮጵያ ለሞዛምቢክ… ቀድመው ይደርሳሉ። ችግር እንዳይፈጠር በጋራ ይሠራሉ፣ ይከላከላሉ፣
  3. ለትምህርት፣ የአፍሪካን አኅጉር የትምህርት ተቋማት ጥራትና ደረጃ መዝኖ የአፍርካ ታሪክና ሥልጣኔን ያካተተ ትምህርት የሚሰጡ ትምህርት ቤቶችን ዩኒቨርሲቲዎችን ዕውቅና የሚሰጥ ተቋም (African Union Education Commission and Accreditation Center) በኅብረቱ ሥር መቋቋም ይኖርበታል። የአፍሪካ ተቋማት ምሩቅ በአኅጉሩ ውስጥ የፈለጉት ቦታ ያለ ውጣ ውረድ መሥራት ያስችላል።
  4. ለገንዘብ፣ አፍርካዊ የገንዘብ ተቋም ወይም ባንክ (Pan African Bank) በኅብረቱ ሥር የአፍሪካ ባንክ ማቋቃም ይገባል። አፍሪካውያን ገንዘባቸውን በአፍሪካ ማስቀመጥና መበዳደር ያስችላቸዋል።
  5. ለምጣኔ ሀብት ወይም ኢኮኖሚ፣ በኅብረቱ ሥር የአፍሪካ ኢኮኖሚ ተቋም (African Union Economic Commision) መቋቋም አለበት። አንድ ገንዘብ፣ አኅጉራዊ ግብር፣ ልማትን መምራትና ማስፈጸም፣ ማስተሳሰር ያስችላል።
  6. ለሰላም፣ ለፀጥታው እንዲሁም የአፍሪካን አኅጉር ዳር ድንበር ለማስከበር። የአፍሪካ የጋራ መከላከያ ተቋም (African Defence treaty) ሊኖር ይገባል። የጋራ ጠላትን በጋራ መመከት ያስፈልጋል።

እነኚህ ስድስት ተቋማት ሲኖሩና አፍሪካዊ ሆነው ተቀርፀው ሲጠናከሩ፣ አባቶቻችን ያለሙት ህልምና ራዕይ ዕውን ይሆናል። አለበለዚያ አፍሪካ በእጅ አዙር እንደተገዛች ሀብቷ እንደተዘረፈ፣ ሰላም እንደጠፋ፣ በነፃ አውጪና አውጫጪ እንደተተራመሰች፣ ልጆቿ በስውር በባርነት ይቀጥላሉ!!!

ተነሱ ተነሱ፣ አሁንም ተነሱ

እንዳንበሳው አግሡ

ተምሳሌነቱ

የኅብረት ያንድነቱ

ከጥንት ከጥዋቱ

ነውና ልምዳችሁ፣

      የኢትዮጵያ ልጆች

የአፍሪካ ፈርጦች

ለአገር ክብር ሟቾች

ሁሉን አስተባብሩ

ማማ አፍሪካን አኩሩ

ከፍ፣ ከፍ በሉ፣ ድመቁ ተከበሩ

እንደ ኮኮብ አብሩ

የኅብሪቱ እምቢልታ ይሰማ

ከኢትዮጵያ ማማ

ዕውን ትሁን አንድ አፍሪካ

ክብሯ እማይነካ!!!!!

  • ተመባ (ጥር 24/2014)
spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የቤት ባለንብረቶች የሚከፍሉትን ዓመታዊ የንብረት ታክስ የሚተምን ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጀ

በአዋጁ መሥፈርት መሠረት የክልልና የከተማ አስተዳደሮች የንብረት ታክስ መጠን...

እንደ ንብረት ታክስ ያሉ ወጪን የሚያስከትሉ አዋጆች ከማኅበረሰብ ጋር ምክክርን ይሻሉ!

የመንግሥትን ገቢ በማሳደግ ረገድ አስተዋጽኦ እንዳላቸው የሚታመኑት የተጨማሪ እሴት...

ለዓለምም ለኢትዮጵያም ሰላም እንታገል

በበቀለ ሹሜ ያለፉት ሁለት የዓለም ጦርነቶች በአያሌው የኃያል ነን ባይ...