የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ አቡነ ማርቆስ፣ በሁለት ሊቃነ ጳጳሳት ሥርዓተ ቀብር ላይ የተናገሩት፡፡ በቅርቡ ያረፉት ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት አቡነ ባስልዮስና አቡነ አረጋዊ ሥርዓተ ቀብር መጋቢት 17 ቀን 2015 ዓ.ም. በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ሲፈጸም፣ መሰንበቻውን አዲስ አበባ ውስጥ በድንጋይ ተወግረው ስለተገደሉት አንድ አባት አስመልከተው ነው አቡነ ማርቆስ፣ በአሁኑ ሰዓት ካህን ቀድሶ ቆርቦ አቁርቦ በድንጋይ ተወግሮ በሚሞትበት ዘመን መደረሱ ምን ይባላል፣ ኧረ ኢትዮጵያውያን ምን ነካችሁ? ግን ምን እናድርግ? ኢትዮጵያ እንደዚህ ነበረች? ምነው ምሁራን ምን ነካችሁ? ይሄ ግራ የገባው ፖለቲካ ምን ይጠቅም ብላችሁ? ምናለ ዝም ባትሉ? ምነው ዶክተሮች? ምነው የሀገር ሸማግሌዎች? ምነው የሃይማኖት መሪዎች? እንደዚህ ነው? ሲሉ ጠይቀዋል።