መንግሥት ከ‹‹ኦነግ ሸኔ››ጋር ያለውን ግጭት በሰላም ለመፍታት ከፍተኛ ፍላጎት እንዳለው ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ደ/ር) ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዛሬው ዕለት ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለቀረበላቸው ጥያቅ በሰጡት ምላሽ ከኦነግ ሸኔ ጋር ያለውን ግጭት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት በገዥው ብልጽግና ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበር የሚመራ ኮሚቴ መቋቋሙን ገልጸዋል።
የኦሮሚያ ክልል በቅርቡ የገለጸውም ይህንኑ የገዥው ፓርቲ ውሳኔ እንደሆነ ተናግረዋል።
ግጭቱን በሰላም ለመፍታት ከ10 በላይ ሙከራዎች መደረጋቸውን ነገር ግን በኦነግ ሸኔ በኩል ለጥያቄው ምላሽ የሚሰጠው ፖለቲካዊ አመራር ማን እንደሆነ አለመታወቁ አስቸጋሪ ሁኔታ እንደፈጠረ ተናግረዋል።