Tuesday, October 3, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዝንቅ“የሰው ዘር በሙሉ . . .!”

“የሰው ዘር በሙሉ . . .!”

ቀን:

በዓለማችን ከአውሮፓ ምድር ያላቸውን ቅሪት ሰብስበው የአሜሪካንን ግምጃ ቤት ሀብት እንዲዳብር በመመኘት ታይታኒክ በምትባል መርከብ የተጓዙትን የእነ ጆን ጃኮብ ስቶርን ሀብት ባሕር ሰምጦ እንዲቀር የተንኮል ሴራው የማን እንደሆነ ስንቶቻችሁ ታውቃላችሁ?፡፡ ድሃን በውሸት ሥልጣን ላይ እናበቃለን እየተባለ ባለሀብት ተጠላ፡፡ አቆርቋዥ … ጉልተኛ … ቢሮክራት … ከበርቴ … የሚል ቅጽል እየተሰጠው የለፋበት ሀብት ለማንም አብዮተኛ ነኝ ባይ ኪስ ማደለቢያ ሆነ፡፡ ሀብት … ተነጠቀ … በመዝሙር ተደሰኮረ … ኢንተርናሲዮናል ተዘመረ፡፡ ማጭድና መዶሻ … በየቦታው ተንጠለጠለ … ማጭዱ ልማትና ሀብት አጨደ፡፡ … መዶሻው … የባለሀብትን ጭንቅላት ከመውቀር ውጪ ጠብ ያረገው አልነበረም፡፡ ዛሬ ትክክለኛውን መዝሙር ትክክለኛውን አርማ ትክክለኛ ውል ምልክት የምታዩበት ዘመን መጣ፡፡ “ትንቢቱ ይፈጸም ዘንድ ዓለምን እንዳይረሳው” ይላል የኛ መጽሐፍ፡፡ “ዓለም እንዳይረሳው የተዋጉህን የተፈታተኑህን የጠላቶችህን ምልክት በድልህ ሰዓት አታውድመው፡፡ ያየ ሁሉ ልብ ይለው ዘንድ አሻሽለህ ተጠቀም፡፡ ያን ጊዜ በአንተ ደግ ምግባር የተሸናፊ አሻራ ይታያል፡፡” እንደሚለው መጽሐፉ፣ ታዲያ አሁን ይህ አልሆነም ወይ ወገኖቼ? ሶሻሊዝም ሲጠቀምበት የነበረውን ማጭድና መዶሻ የሸቀል ኤከራችን ተከታዮች ማጭዱ እጀታውን፣ መዶሻውን አናቱን ቆርጠው እነሆ ለዩሮ ምልክትነት አደረጉት፡፡ “ተነሱ የረሃብ እስረኞች፣ ተነሱ የምድር ጐስቋሎች የሚለው፣ በስህተት ኤዠን ፖተር በተባለ ፈረንሳዊ የተጻፈው ኢንተርናሲዮናል መዝሙር፣ አሁን በትክክለኛው የሚዘመርበት ቀን መጣ፡፡

‹‹ተነሱ እናንተ ቢሊየነሮች

ተነሱ የምድራችን ዲታዎች

በብር የሰማይ መንገድ ይከፈታል

ሻል ያለ ዓለምም ይመጣል

የፍጻሜው ንግድ ነው

ተነሱ እናተ ቢሊየነሮች

የሸቀል ኤከር መንፈስ በሰባቱ ዩሮ ኖቶች ይታተማል፤

የሰው ዘር በሙሉ የባለብር ይሆናል፡፡››

ካሣሁን ከበደ ‹‹ከጃርት ወደ ዳርት›› (2000)

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ተመድንና ዓለም አቀፋዊ ሕግን ከእነ አሜሪካ አድራጊ ፈጣሪነት እናድን!

በገነት ዓለሙ በእኔ የተማሪነት፣ የመጀመርያ ደረጃ ተማሪነት ጊዜ፣ የመዝሙር ትምህርት...

የሰላም ዕጦትና የኢኮኖሚው መንገራገጭ አንድምታ

በንጉሥ ወዳጅነው ፍራንክ ቲስትልዌይት የተባሉ አሜሪካዊ ጸሐፊ ‹‹The Great Experiment...

ድህነት የሀብት ዕጦት ሳይሆን ያለውን በአግባቡ ለመጠቀም አለመቻል ነው

በአንድነት ኃይሉ ድህነት ላይ አልተግባባንም፡፡ ብንግባባ ኖሮ ትናንትም ምክንያት ዛሬም...