Thursday, June 1, 2023
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

ለአገር ውስጥ ባለሀብቶች የሚደረግ አድሎአዊ አሠራር በሽርክና ኢንቨስትመንቶች ላይ መሰናክል መፍጠሩ ተገለጸ

- ማስታወቂያ -

ተዛማጅ ፅሁፎች

ለአገር ውስጥ ባለሀብቶች በክልሎችና በተዋረድ የሚደረግ አድሎአዊ አሠራር፣ በአገር ውስጥና በውጭ ባለሀብቶች በሽርክና በሚከፈቱ ኢንቨስትመንቶች ላይ መሰናክል መፍጠሩን የኢንቨስትመንት ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

የኢንቨስትመንት ኮሚሽነር ለሊሴ ነሜ እንደገለጹት፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአድሎአዊ አሠራሮች ምክንያት በፍጥነት አለመወሰን፣ ያለ ኢንቨስትመንት ፈቃድ የአክሲዮን ዝውውሮችን ማድረግና በአገር ውስጥ ባለሀብቱ ዘንድ ተደማጭነት ለመጨመርና ተዓማኒነትን ለመፍጠር ከሕግ ውጪ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች እየታዩ ነው፡፡

በኢንቨስትመንት ዘርፍ በርካታ ማነቆዎች እየተስተዋሉ መሆኑን የገለጹት ኮሚሽነሯ፣ በውጭ ምንዛሪና በብድር አሰጣጥ የባንኮች አሠራር ግልጽ አለመሆኑን፣ ኢንቨስተሮች በሕግ ማዕቀፍ የሌሉ ክፍያዎችን በክልሎች መጠየቃቸውን፣ የኢንቨስትመንት መድን አሠራር ሽፋን አለመኖር፣ በተለይም የፀጥታ ችግር ሲፈጠር ለሚከሰት ጉዳት የሚሆን ማካካሻ አለመኖርና የመሳሰሉት ክፍተቶችን ጠቅሰዋል፡፡

በመንግሥት አስፈጻሚ አካላት የማስፈጸም አቅም ማነስ፣ ቅንጅታዊ አሠራር አለመኖር፣ የግንዛቤ እጥረትና ውስብስብ የሆኑ የአሠራር ሒደቶች መኖራቸው ዋነኛ ተግዳሮቶች ተብለው በኮሚሽነሯ ተለይተዋል፡፡

የመሠረተ ልማት አለመሟላት በተለይም ለኢንቨስትመንት አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶች በቂ አለመሆን፣ የፖሊሲና ሕግ አፈጻጸም ችግር፣ የኢንቨስትመንት ደኅንነትና ጥበቃ ዕጦት የመሳሰሉ ጉዳቶችን አክለው አብራርተዋል፡፡

በሌላ በኩል የመንግሥት አካላት የግሉን ዘርፍ እንደ ሌባ በጥርጣሬ የማየት ዝንባሌ፣ አሠራርና የመፍትሔ ሒደቶች ተስፋ አስቆራጭ መሆናቸው፣ የረዘመ የቢሮክራሲ ሒደት የፈጠረው የመሰላቸትና ተስፋ የመቁረጥ ሁኔታዎች እየተፈጠሩ መሆናቸውን አክለው ገልጸዋል፡፡

በክልሎችና በታችኛው የመንግሥት መዋቅሮች በበርካታ የአገሪቱ አካባቢዎች የኢንቨስትመንት አስተሳሰብ የተዛባና የኢንቨስትመንት ጥበቃ አናሳ መሆን፣ ችግሮች ሲከሰቱ የመጀመሪያው ተጠቂ ኢንቨስትመንቱ እንዲሆን አድርገዋል ሲሉ ኮሚሽነሯ አስረድተዋል፡፡

በየክልሎች የተለያየ ዓይነት አሠራር መኖርና ወጥ የሆነ አለመሆኑ ኢንቨስተሮች ሥጋት እንዲኖራቸው ማድረጉን፣ በአመለካከትም ሆነ በግንዛቤ እጥረት ኢንቨስተሮች በርካታ ሠራተኛ ይዘውም እንዲዘጉ መደረጋቸው ኢንቨስትመንት ሊስብ የሚችል ፖሊሲ አለመኖር እንደ ችግር ተገልጸዋል፡፡

ከሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት በኋላ የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴው መነቃቃት እየታየበት ከቻይና፣ ከህንድና ከፓኪስታን ባለሀብቶች እየመጡ ስለመሆናቸው አብራርተው፣ በመሬት አቅርቦት ላይ የሚታየው የቢሮክራሲ ማነቆ፣ የሕግና የፖሊሲ ማዕቀፎች አለመሟላት በኢንቨስተሮች የሚነሱ ችግሮች መሆናቸውን አስረድተዋል፡፡

በትግራይ ክልል ኢንቨስት አድርገው የነበሩና በጦርነቱ ሳቢያ ለቀው ወጥተው ከነበሩ ባለሀብቶች የተወሰኑት ተመልሰው እየመጡ ነው ብለዋል፡፡

ኮሚሽነር ሌሊሴ ባለፉት ሰባት ወራት 2.25 ቢሊዮን ዶላር የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት መሳብ መቻሉን፣ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር 16 በመቶ ዕድገት ማሳየቱን አክለዋል፡፡  

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች