Sunday, September 24, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊለአደጋ ሥጋት ተጋላጭ የሆኑ ተቋማትና ግለሰቦችን ለማስነሳት አስገዳጅ መመርያ ፀደቀ

ለአደጋ ሥጋት ተጋላጭ የሆኑ ተቋማትና ግለሰቦችን ለማስነሳት አስገዳጅ መመርያ ፀደቀ

ቀን:

በአበበ ፍቅር

ለአደጋ ሥጋት ተጋላጭ የሆኑ ተቋማቶችንና ግለሰቦችን በሕጋዊ መንገድ ለማስነሳት የሚረዳ፣ አስገዳጅ መመርያ መፅደቁን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የእሳትና አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፍሰሐ ጋረደው አስታውቋል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ በሕገወጥ መንገድ የወንዝ ዳርቻዎችን ተከትለው የሚሰፍሩ የማኅበረሰብ ክፍሎች፣ ከፍተኛ የጎርፍ አደጋ ሥጋት ተጋላጭ ስለሆኑ፣ ሁሉም በሚባል ደረጃ መነሳት አለባቸው ሲሉ መጋቢት 15 ቀን 2015 ዓ.ም. በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ተናግረዋል፡፡

ከዚህ በፊት ለአደጋ ሥጋት ተጋላጭ የሆኑ ግለሰቦችንና ተቋማትን የመጠቆም ሥራ የኮሚሽኑ እንደነበር አንስተው፣ አሁን ላይ ግን የከተማ አስተዳደሩ ተቋማትንና ግለሰቦችን የሚያስገድድ ሕግ እንዳፀደቀላቸው ተናግረዋል፡፡

ሕጉን ለማስፈጸም ዝርዝር መመርያን በመጠበቅ ላይ መሆናቸውን ዋና ኮሚሽነሩ አብራርተዋል፡፡

ከዚህ በኋላ መመርያውን ወደ ማስፈጸም ሥራ እንደሚገቡና ነገሮችን በሕግ አስገዳጅነት የመፈጸም ሁኔታ እንደሚኖር አስታውቀዋል፡፡

ከጥንቃቄ ጉድለት የተነሳ ላለፉት ስድስት ወራት በአዲስ አበበ ከተማ በተከሰቱ ድንገተኛ አደጋዎች 230 ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱን የተናገሩት ዋና ኮሚሽነሩ፣ አደጋዎቹ በእሳት ቃጠሎ፣ በጎርፍ፣ በግንባታ ሥራዎች ላይ በሚደርሱ ጉዳቶች ሲሆን በእሳት አደጋ የደረሰው አደጋ ከፍተኛውን ድርሻ ይይዛል ብለዋል፡፡

ባለፈው ሳምንት የጣለው ዝናብ መጪው ክረምት ሊከብድ እንደሚችል አመላካች ነው ብለዋል፡፡ በዚህ በመነሳትም ሁሉም የከተማዋ ነዋሪዎች ከዝናቡ ጋር ተከትሎ የሚመጣውን ጎርፍ በመከላከል አደጋን መቀነስ ይኖርበታል ብለዋል፡፡

ከሁሉም በላይ በሕገወጥ መንገድ በወንዝ ዳርቻዎች የሰፈሩ ግለሰቦች፣ ለአደጋው ተጋላጫ መሆናቸውን አሳውቀው፣ አካባቢውን እንዲለቁ ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ዮሴፍ ቤተ ክርስቲያን በሚገኘው የወንዝ ዳርቻ በርካታ ሰዎች በሕገወጥ መንገድ መስፈራቸውን ያነሱት ዋና ኮሚሽነሩ፣ ግለሰቦቹ ለከፍተኛ የጎርፍ አደጋ ተጋላጭ መሆናቸውን አውቀው ከቦታው እንዲነሱ አሳስበዋል፡፡ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ተመሳሳይ ችገር መኖሩን ተናግረዋል፡፡

በዚህ መልኩ ከከተማ አስተዳደሩ ዕውቅና ውጪ በተለያዩ ሥፍራዎች ቤት ገንብተው የሚኖሩ የማኅበረሰብ ክፍሎች መንገሥት ምንም ዓይነት ካሳ ወይም ቅያሬ ቦታ እንደማይሰጥ አስታውቀው፣ የራሳቸውን አማራጫ እንዲፈልጉ ሲሉ ኮሚሽነር ፍስሐ ተናግረዋል፡፡

የአደጋ ሥጋቱን ለመቀነስ ማንኛውም በሕገወጥ መንገድ የተሠሩ ቤቶችን ማፍረስ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡ በሕጋዊ መንገድ ሰፍረው ነገር ግን ለአደጋ ተጋላጭ ለሆኑ የኅብረተሰብ ክፍሎች ጊዜአዊ መጠለያ እየተዘጋጀላቸው እንደሆነም አብራርተዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የቤት ባለንብረቶች የሚከፍሉትን ዓመታዊ የንብረት ታክስ የሚተምን ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጀ

በአዋጁ መሥፈርት መሠረት የክልልና የከተማ አስተዳደሮች የንብረት ታክስ መጠን...

እንደ ንብረት ታክስ ያሉ ወጪን የሚያስከትሉ አዋጆች ከማኅበረሰብ ጋር ምክክርን ይሻሉ!

የመንግሥትን ገቢ በማሳደግ ረገድ አስተዋጽኦ እንዳላቸው የሚታመኑት የተጨማሪ እሴት...

ለዓለምም ለኢትዮጵያም ሰላም እንታገል

በበቀለ ሹሜ ያለፉት ሁለት የዓለም ጦርነቶች በአያሌው የኃያል ነን ባይ...